የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በእሳት የነጠረ ወርቅ ግዛ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 2 በዛሬው ጊዜ የሎዶቅያን ፍርስራሾች ከአላሴሂር ደቡብ ምሥራቅ 88 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በዴኒዝሊ ከተማ አቅራቢያ እናገኛለን። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ሎዶቅያ በጣም ኃብታም ከተማ ነበረች። ከተማዋ አውራ ጎዳናዎች በሚገናኙበት ሥፍራ የተቆረቆረች ስለነበረች የባንክ ሥራና የንግድ ማዕከል ነበረች። በከተማይቱ ይሸጥ የነበረው የዓይን መድኃኒት በጣም እውቅ ሆኖ ስለነበረ ተጨማሪ ብልጽግና የሚያስገኝላት የገቢ ምንጭ ሆኖላት ነበር። በተጨማሪም ሎዶቅያ በጣም ጥሩ ጥራት ከነበረው ጥቁር ሱፍ ይሠራ በነበረው ውድ ልብስ ከፍተኛ ዝና አትርፋ ነበር። የከተማይቱ ዋና ችግር የውኃ እጥረት ሲሆን ይህም ችግር ቢሆን ከሩቅ ሥፍራ በቦይ አማካኝነት ይመጣ በነበረው ፍልውኃ ተቃልሎ ነበር። ስለዚህ ውኃው ወደ ከተማዋ ሲደርስ ለብ ያለ ይሆን ነበር።

  • በእሳት የነጠረ ወርቅ ግዛ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. (ሀ) ኢየሱስ በሎዶቅያ የነበረውን ጉባኤ መንፈሣዊ ሁኔታ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) በሎዶቅያ የነበሩ ክርስቲያኖች ሳይከተሉ የቀሩት የትኛውን የኢየሱስ አርዓያ ነው?

      6 ኢየሱስ ለሎዶቅያ ክርስቲያኖች ምን የሚነግራቸው መልእክት ነበረው? እነርሱን የሚያመሰግንበት ምክንያት አልነበረውም። በግልጽ የሚከተለውን ነገራቸው:- “በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ፣ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።” (ራእይ 3:15, 16) እንዲህ ዓይነት መልእክት ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቢደርስህ ምን ታደርጋለህ? ነቃ ብለህ ራስህን አትመረምርምን? የሎዶቅያ ክርስቲያኖች ቸልተኞችና ምስጋና ቢሶች በመሆን በመንፈሳዊ ፈዝዘው ስለነበረ ራሳቸውን መቀስቀስ ነበረባቸው። (ከ⁠2 ቆሮንቶስ 6:1 ጋር አወዳድር።) ክርስቲያኖች እንደመሆናቸው መጠን ምሳሌያቸው ሊሆን የሚገባው ኢየሱስ ለይሖዋና ለአገልገሎቱ እንደ እሳት የሚነድድ ቅንዓት ነበረው። (ዮሐንስ 2:17) ከዚህም በላይ ኢየሱስ በጣም በሚያተኩስ ሞቃት ቀን እንደሚጠጣ ቀዝቃዛ ውኃ ልዝብ፣ የማይጎዳ ሰውነት የሚያድስ እንደሆነ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ተገንዝበው ነበር። (ማቴዎስ 11:28, 29) የሎዶቅያ ክርስቲያኖች ግን በራድም ሞቃትም አልነበሩም። በከተማቸው መሃል ይፈስ እንደነበረው ውኃ ለብ ያሉ ሆነዋል። ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሊጥላቸውና ‘ከአፉ አውጥቶ ሊተፋቸው’ የሚገቡ ሆነዋል። እኛ ግን ዘወትር እንደ ኢየሱስ ሰዎችን የሚያረካ መንፈሳዊ ውኃ ለማዳረስ በቅንዓት እንጣር።—ማቴዎስ 9:35-38

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ