የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ሰማያዊ ዙፋን ክብርና ግርማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • ይሖዋ የሚገኝበት አንጸባራቂ ሁኔታ

      4. (ሀ) የዮሐንስ ራእይ ለቅቡዓን ክርስቲያኖች ምን ትርጉም አለው? (ለ) በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ላላቸውስ ምን ትርጉም አለው?

      4 ዮሐንስ ምን ነገር ተመለከተ? የተመለከተውንና ያጋጠመውን አስደናቂ ሁኔታ ሲነግረን እናዳምጥ:- “ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ እነሆም፣ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ።” (ራእይ 4:2) ዮሐንስ ከመቅጽበት በአምላክ አንቀሳቃሽ ኃይል አማካኝነት ወደ ይሖዋ ዙፋን በመንፈስ ተወሰደ። ዮሐንስ ምን ያህል ተደስቶ ይሆን! እርሱና ሌሎች ቅቡዓን ክርስቲያኖች ‘ሕያው ተስፋ፣ የማይጠፋ፣ እድፈትም የሌለበት፣ የማያልፍ ርስት’ በተጠበቀላቸው በሰማይ ያለውን አስደናቂ ትርዒት እንዲመለከት ተደረገ። (1 ጴጥሮስ 1:3-5፤ ፊልጵስዩስ 3:20) በምድር ላይ ለዘላለም ለመኖር ተስፋ ለሚያደርጉ ሰዎችም ቢሆን የዮሐንስ ራእይ ጥልቅ ትርጉም አለው። ይሖዋ የሚገኝበትን ሥፍራ ክብርና ግርማ እንዲሁም ይሖዋ በአሕዛብ ላይ በሚፈርድበትና በኋላም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሚጠቀምበትን የሰማያዊ አገዛዝ መዋቅር እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል። በእውነትም ይሖዋ በጣም ታላቅ የሆነ የድርጅት አምላክ ነው።

      5. ዮሐንስ የተመለከተው የቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ ምሳሌ የሆነው ለየትኛው እውነተኛ ነገር ነው?

      5 ዮሐንስ በሰማይ የተመለከተው ነገር በምድረ በዳ ከነበረው ድንኳን ጋር በአብዛኛው ይመሳሰላል። ይህን ድንኳን እሥራኤላውያን እውነተኛ አምልኮ የሚፈጽሙበት ቤተ መቅደስ እንዲሆናቸው የሠሩት ከ1,600 ዓመታት በፊት ነበር። በዚህ ድንኳን ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የቃል ኪዳኑ ታቦት ይገኝ ነበር። ይሖዋ ይናገር የነበረው ከንጹሕ ወርቅ ከተሰራው ከታቦቱ መክደኛ በላይ ነበር። (ዘጸአት 25:17-22፤ ዕብራውያን 9:5) ስለዚህ የታቦቱ መክደኛ የይሖዋ ዙፋን ምሳሌ ሆኖ አገልግሎአል። አሁን ደግሞ ዮሐንስ ይህ ነገር ምሳሌ የሆነለትን እውነተኛ ነገር ተመለከተ። የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዢ የሆነው ጌታ ይሖዋ በጣም ከፍተኛ በሆነው ሰማያዊ ዙፋኑ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፎ ተቀምጦአል።

  • የይሖዋ ሰማያዊ ዙፋን ክብርና ግርማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ  75 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ