የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ሰማያዊ ዙፋን ክብርና ግርማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • መብረቅ፣ ድምፅና ነጎድጓድ

      12. ዮሐንስ ከዚህ ቀጥሎ ምን ነገር ተመለከተ? ምንስ ሰማ? ‘መብረቁ፣ ነጎድጓዱና ድምፁ’ ምን ነገር ያስታውሰናል?

      12 ዮሐንስ ቀጥሎ የተመለከተውና የሰማው ነገር ምንድን ነው? “ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጎድጓድም ይወጣል።” (ራእይ 4:5ሀ) የይሖዋ ሰማያዊ ኃይል ከሚገለጥባቸው አስደናቂ የሆኑ መንገዶች ጋር የሚስማማ ሌላ አስፈሪ መግለጫ ነበር። ለምሳሌ ያህል ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በወረደ ጊዜ የሆነውን ነገር ሙሴ እንዲህ ሲል ጽፎአል:- “በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጎድጓድ መብረቅ፣ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ በተራራው ላይ ሆነ። . . . የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ፣ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።”—ዘጸአት 19:16-19

      13. ከይሖዋ ዙፋን የሚወጣው መብረቅ ምን ያመለክታል?

      13 ይሖዋ በጌታ ቀን ኃይሉንና መገኘቱን የገለጸው በከፍተኛ ሁኔታ ነበር። ዮሐንስ የተመለከተው ምልክቶችን ስለነበረ ይሖዋ የተገለጠው ቃል በቃል በእውነተኛ መብረቅ አልነበረም። ታዲያ መብረቁ የምን ምሳሌ ነው? የመብረቅ ብልጭታ ብርሃን ሊሰጥ ቢችልም ሰውንም ሊገድል ይችላል። ስለዚህ ይህ ከይሖዋ ዙፋን የወጣው መብረቅ የዕውቀትን ብርሃን፣ እንዲሁም እሳታማ የሆነውን የፍርድ መልእክቱን ያመለክታል።—ከ⁠መዝሙር 18:14፤ ከመዝሙር 144:5, 6፤ ከ⁠ማቴዎስ 4:14-17⁠ና ከማቴዎስ 24:27 ጋር አወዳድር።

      14. በዘመናችን ድምፅ የተሰማው እንዴት ነው?

      14 ድምፁስ የምን ምሳሌ ነው? ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በወረደበት ጊዜ አንድ ድምፅ ሙሴን አነጋግሮት ነበር። (ዘጸአት 19:19) በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን ትዕዛዞችና አዋጆች የተናገሩት ከሰማይ የወጡ ድምፆች ነበሩ። (ራእይ 4:1፤ 10:4, 8፤ 11:12፤ 12:10፤ 14:13፤ 16:1, 17፤ 18:4፤ 19:5፤ 21:3) በዛሬው ጊዜም ይሖዋ ለሕዝቦቹ ትዕዛዝና አዋጅ በመስጠት ለመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ያላቸውን የመረዳት ችሎታ አብርቶላቸዋል። ብርሃን ሰጪ የሆኑ አዳዲስ እውቀቶች ብዙ ጊዜ በዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ የተገለጹ ሲሆን በኋላም እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ታውጀዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ በታማኝነት ምሥራቹን ይሰብኩ ስለነበሩ ሰዎች ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር:- “በእውነት ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።”—ሮሜ 10:18

      15. በዚህ የጌታ ቀን ክፍል ከይሖዋ ዙፋን የወጣው እንዴት ያለ የነጎድጓድ ድምፅ ነው?

      15 ብዙውን ጊዜ ከብልጭታ በኋላ ነጎድጓድ ይከተላል። ዳዊት ነጎድጓድ ‘የይሖዋ ድምፅ እንደሆነ’ ተናግሮአል። (መዝሙር 29:3, 4 NW) ይሖዋ ለዳዊት ቆሞ ከጠላቶቹ ጋር በተዋጋለት ጊዜ ከይሖዋ ዘንድ ነጎድጓድ እንደወጣ ተነግሮ ነበር። (2 ሳሙኤል 22:14፤ መዝሙር 18:13) ይሖዋ “እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር” በሚያደርግበት ጊዜ ድምፁ እንደ ነጎድጓድ እንደሚሰማ ኤሊሁ ለኢዮብ ነግሮታል። (ኢዮብ 37:4, 5) በዚህ በአሁኑ የጌታ ቀን ክፍል ውስጥ ይሖዋ በጠላቶቹ ላይ ስለሚያደርጋቸው ታላላቅ ነገሮች በማስጠንቀቅ እንደ ነጎድጓድ ያለ ድምፅ አሰምቶአል። ይህ ምሳሌያዊ የነጎድጓድ ድምፅ በምድር ዙሪያ አስተጋብቶአል። ይህን ነጎድጓዳማ አዋጅ ሰምተህና የራስህንም ድምፅ በመጨመር ይበልጥ እንዲያስተጋባ ረድተህ ከሆነ በጣም ደስተኛ ነህ።—ኢሳይያስ 50:4, 5፤ 61:1, 2

      የእሳት መብራቶችና የብርጭቆ ባሕር

      16. ‘ሰባቱ የእሳት መቅረዞች’ ምን ያመለክታሉ?

      16 ዮሐንስ ቀጥሎ ምን ተመለከተ? የሚከተለውን ተመልክቶአል:- “በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ።” (ራእይ 4:5ለ, 6ሀ) የሰባቱን መብራቶች ትርጉም ዮሐንስ ራሱ “እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው” በማለት ነግሮናል። ሰባት ቁጥር የሚያመለክተው መለኮታዊ ሙላትን ነው። ስለዚህ ሰባቱ መብራቶች መንፈስ ቅዱስ የእውቀት ብርሃን ሲሰጥ በሙሉ ኃይል መሥራቱን ያመለክታሉ። የዮሐንስ ክፍል ይህ የእውቀት ብርሃን የተሰጠው ብርሃኑን ለምድር መንፈሳዊ ረሀብተኞች ከማስተላለፍ መብት ጋር ስለሆነ በጣም አመስጋኝ ነው። በየዓመቱ በመቶ ሚልዮን የሚቆጠሩ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ቅጂዎች 150 በሚያህሉ ቋንቋዎች ይህን ብርሃን ስለሚያንጸባርቁ ምንኛ አመስጋኞች መሆን ይገባናል!—መዝሙር 43:3

  • የይሖዋ ሰማያዊ ዙፋን ክብርና ግርማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ  78 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ