-
አምላክ ማን ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ይሖዋ ምን ይላል?
መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ከሚያመልኳቸው አማልክት መካከል ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ይሖዋ እንደሆነ ይናገራል። ለምን? የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። ይሖዋ ከማንም የበለጠ ሥልጣን ያለው ሲሆን “በመላው ምድር ላይ ልዑል” የሆነው እሱ ብቻ ነው። (መዝሙር 83:18ን አንብብ።) “ሁሉን ቻይ” ስለሆነ የፈለገውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል አለው። “ሁሉንም ነገሮች” ማለትም ጽንፈ ዓለምንም ሆነ በምድር ላይ ያለውን ሕይወት በሙሉ ‘የፈጠረው’ እሱ ነው። (ራእይ 4:8, 11) ይሖዋ ያልነበረበት ጊዜ የለም፤ ወደፊትም ለዘላለም ይኖራል። ይህም ከሌሎች የተለየ ያደርገዋል።—መዝሙር 90:2
-
-
አምላክ የሚቀበለው አምልኮለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ይሖዋ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን ሊመለክ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። (ራእይ 4:11) እሱን ብቻ መውደድ ይኖርብናል፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ቅርጻ ቅርጽ ወይም ምስል ሳንጠቀም ልናመልከው ይገባል።—ኢሳይያስ 42:8ን አንብብ።
አምልኳችን “ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው” መሆን ይኖርበታል። (ሮም 12:1) ይህም ሲባል እሱ ባወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራት አለብን ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋን የሚወዱ ሰዎች እሱ ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ያወጣውን መመሪያ ሊቀበሉና ሊታዘዙ ይገባል። በተጨማሪም ሲጋራ እንደማጨስ፣ ጫት እንደመቃም እንዲሁም ዕፆችን ወይም አልኮልን አላግባብ እንደመጠቀም ካሉ ጎጂ ልማዶች ይርቃሉ።a
-