-
‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
1. ዮሐንስ በተመለከተው ራእይ አሁን ምን ነገር ተፈጸመ?
ዕጹብ ድንቅ ነው፤ የሚያስፈራ ግርማ ያለው ነው። በእሳት መቅረዞች፣ በኪሩቤሎች፣ በ24 ሽማግሌዎችና እንደ መስተዋት በጠራው ባሕር ታጅቦ የታየው የይሖዋ ዙፋን ይህን ይመስል ነበር። ይሁን እንጂ ዮሐንስ ቀጥሎ ምን ተመለከተ? ዮሐንስ የሚከተለውን በማለት በዚህ ሰማያዊ ትርዒት ማዕከላዊውን ሥፍራ ወደ ያዘው አካል እንድናተኩር ያደርገናል። “በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ። ብርቱም መልአክ:- መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹን ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ። በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም። መጽሐፉንም ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።”—ራእይ 5:1-4
-
-
‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
3 ኃያሉ መልአክ ጥቅልሉን ለመክፈት ብቃት ያለው ሰው ያገኝ ይሆንን? ኪንግደም ኢንተርሊንየር እንደሚለው ጥቅልሉ የሚገኘው በይሖዋ “ቀኝ እጅ” ነበር። ይህም ክፍት በሆነው የእጁ መዳፍ ይዞት እንደነበር ያመለክታል። ይሁን እንጂ ጥቅልሉን ተቀብሎ ለመክፈት ብቃት የሚኖረው በምድርም ሆነ በሰማይ የሚገኝ አልመሰለም። ሞተው ከምድር በታች ከሚገኙት ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች መካከል እንኳን ይህን ታላቅ ክብር ለመቀበል ብቃት ያለው አልተገኘም። ዮሐንስ በጣም አዝኖ መታየቱ አያስደንቅም። ምናልባት “ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር” ሳያውቅ ሊቀር ነው። በዘመናችንም ቢሆን የአምላክ ቅቡዓን ሕዝቦች ይሖዋ የራእይን መጽሐፍ እስኪያብራራላቸውና የዕውቀቱንና የእውነቱን ብርሃን እስኪያበራላቸው ድረስ በጉጉት ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ሕዝቦቹን ‘በታላቅ የመዳን’ ጎዳና ለመምራት ሲል ይህንን የሚፈጽምላቸው ለትንቢቱ በተወሰነው ዘመን ውስጥ ደረጃ በደረጃ ነው።—መዝሙር 43:3, 5
-