የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • የውዳሴ መዝሙር

      14. (ሀ) አራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና 24ቱ ሽማግሌዎች ኢየሱስ የመጽሐፉን ጥቅልል በመውሰዱ ምን ተሰማቸው? (ለ) ስለ 24ቱ ሽማግሌዎች ለዮሐንስ የተሰጠው መረጃ ማንነታቸውንና ማዕረጋቸውን ያረጋገጠው እንዴት ነው?

      14 በይሖዋ ዙፋን ፊት የነበሩት የቀሩት ፍጥረታት ምን ተሰማቸው? “መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ። እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።” (ራእይ 5:8) 24ቱ ሽማግሌዎች በአምላክ ዙፋን ፊት እንደነበሩት አራት ኪሩቤላዊ ፍጥረታት የኢየሱስን ሥልጣን በመቀበል ሰገዱለት። ይሁን እንጂ በገናና ዕጣን የሞላበት ዕቃ የያዙት እነዚህ ሽማግሌዎች ብቻ ነበሩ።a አዲስ መዝሙር የዘመሩትም እነዚህ ሽማግሌዎች ብቻ ናቸው። (ራእይ 5:9) ስለዚህ በገና ይዘው አዲስ መዝሙር ከሚዘምሩት 144,000 ቅዱስ የእግዚአብሔር እሥራኤል ጋር ይመሳሰላሉ። (ገላትያ 6:16፤ ቆላስይስ 1:12፤ ራእይ 7:3-8፤ 14:1-4) ከዚህም በላይ በጥንታዊቷ እሥራኤል በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለይሖዋ ዕጣን እያጨሱ የክህነት አገልግሎት ይፈጽሙ እንደነበሩት ካህናት 24ቱ ሽማግሌዎች ሰማያዊ የክህነት አገልግሎት ሲፈጽሙ ታይተዋል። ምድራዊው የክህነት አገልግሎት ያከተመው አምላክ የሙሴን ሕግ በኢየሱስ የመከራ እንጨት ላይ ጠርቆ ከሥፍራ ባስወገደው ጊዜ ነበር። (ቆላስይስ 2:14) ከዚህ ሁሉ ምን ለመደምደም እንችላለን? እዚህ ላይ ቅቡዓኑ ድል አድራጊዎች ‘የአምላክና የክርስቶስ ካህናት በመሆን ከኢየሱስ ጋር ለሺህ ዓመት ለመግዛት’ ሹመታቸውን እንደተቀበሉ ለመመልከት እንችላለን።—ራእይ 20:6

      15. (ሀ) በጥንትዋ እስራኤል ወደ መገናኛው ድንኳን ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት መብት የነበረው ማን ብቻ ነበር? (ለ) ሊቀ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመግባቱ በፊት ዕጣን ማጨሱ የሞትና የሕይወት ጉዳይ የነበረው ለምንድን ነው?

      15 በጥንታዊቷ እሥራኤል ይሖዋ በምሳሌያዊ ሁኔታ ይገኝ ወደነበረበት ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት መብት የነበረው ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር። በሚገባበትም ጊዜ ዕጣን ካልያዘ ተቀስፎ ይሞት ነበር። የይሖዋ ሕግ እንዲህ ይል ነበር:- አሮን በይሖዋ “ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናውን ይሞላል። ከተወቀጠውም ከጣፋጭ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወስዳል። ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል። እንዳይሞትም የጢሱ ዳመና በምስክሩ ላይ ያለውን መክደኛ ይሸፍን ዘንድ በእግዚአብሔር [“በይሖዋ፣” NW] ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ያደርጋል።” (ዘሌዋውያን 16:12, 13) ሊቀ ካህናቱ ዕጣን ካላጨሰ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ፈጽሞ ሊገባ አይችልም ነበር።

      16. (ሀ) በክርስቲያናዊው ሥርዓት የጥንትዋ ምሳሌ ወደ ሆነችላት ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የሚችሉት እነማን ናቸው? (ለ) ቅቡዓን ክርስቲያኖች ‘ዕጣን ማጨስ’ የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?

      16 በክርስትና ሥርዓት ውስጥ ግን እውነተኛው ሊቀካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን 144,000ዎቹ የበታች ካህናት በሙሉ ይሖዋ ወደሚገኝበት ሰማያዊ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባሉ። (ዕብራውያን 10:19-23) እዚህ ላይ በ24 ሽማግሌዎች የተወከሉት ካህናት ዕጣን ካላጨሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ሊገቡ ፈጽሞ አይችሉም። ዕጣን ማጨስ ማለት ደግሞ ዘወትር ቀንና ሌሊት ለይሖዋ ጸሎትና ምልጃ ማቅረብ ማለት ነው።—ዕብራውያን 5:7፤ ይሁዳ 20, 21፤ ከ⁠መዝሙር 141:2 ጋር አወዳድር።

  • ‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ  86 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ