-
‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
14. (ሀ) አራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና 24ቱ ሽማግሌዎች ኢየሱስ የመጽሐፉን ጥቅልል በመውሰዱ ምን ተሰማቸው? (ለ) ስለ 24ቱ ሽማግሌዎች ለዮሐንስ የተሰጠው መረጃ ማንነታቸውንና ማዕረጋቸውን ያረጋገጠው እንዴት ነው?
14 በይሖዋ ዙፋን ፊት የነበሩት የቀሩት ፍጥረታት ምን ተሰማቸው? “መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ። እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።” (ራእይ 5:8) 24ቱ ሽማግሌዎች በአምላክ ዙፋን ፊት እንደነበሩት አራት ኪሩቤላዊ ፍጥረታት የኢየሱስን ሥልጣን በመቀበል ሰገዱለት። ይሁን እንጂ በገናና ዕጣን የሞላበት ዕቃ የያዙት እነዚህ ሽማግሌዎች ብቻ ነበሩ።a አዲስ መዝሙር የዘመሩትም እነዚህ ሽማግሌዎች ብቻ ናቸው። (ራእይ 5:9) ስለዚህ በገና ይዘው አዲስ መዝሙር ከሚዘምሩት 144,000 ቅዱስ የእግዚአብሔር እሥራኤል ጋር ይመሳሰላሉ። (ገላትያ 6:16፤ ቆላስይስ 1:12፤ ራእይ 7:3-8፤ 14:1-4) ከዚህም በላይ በጥንታዊቷ እሥራኤል በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለይሖዋ ዕጣን እያጨሱ የክህነት አገልግሎት ይፈጽሙ እንደነበሩት ካህናት 24ቱ ሽማግሌዎች ሰማያዊ የክህነት አገልግሎት ሲፈጽሙ ታይተዋል። ምድራዊው የክህነት አገልግሎት ያከተመው አምላክ የሙሴን ሕግ በኢየሱስ የመከራ እንጨት ላይ ጠርቆ ከሥፍራ ባስወገደው ጊዜ ነበር። (ቆላስይስ 2:14) ከዚህ ሁሉ ምን ለመደምደም እንችላለን? እዚህ ላይ ቅቡዓኑ ድል አድራጊዎች ‘የአምላክና የክርስቶስ ካህናት በመሆን ከኢየሱስ ጋር ለሺህ ዓመት ለመግዛት’ ሹመታቸውን እንደተቀበሉ ለመመልከት እንችላለን።—ራእይ 20:6
-
-
‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
አዲስ መዝሙር
17. (ሀ) 24ቱ ሽማግሌዎች የትኛውን አዲስ መዝሙር ዘመሩ? (ለ) “አዲስ መዝሙር” የሚለው አነጋገር አብዛኛውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንን ለማመልከት ያገለግል ነበር?
17 አሁን በጣም የሚጥም ዜማ ያለው መዝሙር ተሰማ። መዝሙሩን ለበጉ የዘመሩት ካህናት ባልንጀሮቹ የሆኑት 24ቱ ሽማግሌዎች ናቸው። “መጽሐፉን ትውስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፣ ታርደሃልና፣ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ . . . እያሉ፤ አዲስ ቅኔን ይዘምራሉ።” (ራእይ 5:9) “አዲስ ቅኔ” ወይም “አዲስ መዝሙር” የሚለው ሐረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታዎች ላይ ይገኛል። አብዛኛውን ጊዜም የሚያመለክተው ይሖዋ ለሰጠው ታላቅ ማዳን እርሱን ለማወደስ የቀረበን መዝሙር ነው። (መዝሙር 96:1፤ 98:1፤ 144:9) ስለዚህ ዝማሬው ይሖዋ ስለ ፈጸመው አዲስና አስደናቂ ነገር ለመግለጽ፣ ስለ ታላቅ ስሙ አዲስ ዓይነት አድናቆት እንዳደረበት ለመናገር ስለቻለ መዝሙሩ ወይም ቅኔው አዲስ ይሆናል ማለት ነው።
18. 24ቱ ሽማግሌዎች ኢየሱስን በአዲሱ መዝሙር ያመሰገኑት ምን ስላደረገ ነበር?
18 ይሁን እንጂ እዚህ ላይ 24ቱ ሽማግሌዎች አዲስ መዝሙር የዘመሩት በይሖዋ አምላክ ፊት ሳይሆን በኢየሱስ ፊት ነው። መሠረታዊ ሥርዓቱ አልተለወጠም። በአምላክ ልጅነታቸው ስላደረገላቸው ነገሮች ኢየሱስን ያወድሱታል። በደሙ አማካኝነት ለአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ ሆኖላቸዋል። በዚህም ምክንያት የይሖዋ ልዩ ንብረት የሆነ አዲስ ሕዝብ ሊገኝ ችሎአል። (ሮሜ 2:28, 29፤ 1 ቆሮንቶስ 11:25፤ ዕብራውያን 7:18-25) የዚህ መንፈሳዊ ብሔር አባሎች የተውጣጡት ከብዙ ሥጋዊ ብሔራት ቢሆንም ኢየሱስ እንደ አንድ ሕዝብ ወይም ብሔር አድርጎ በአንድ ጉባኤ ውስጥ አድርጎአቸዋል።—ኢሳይያስ 26:2፤ 1 ጴጥሮስ 2:9, 10
19. (ሀ) ሥጋዊ እስራኤላውያን ታማኝ ባለመሆናቸው ምክንያት ምን ዓይነት በረከት ሳያገኙ ቀርተዋል? (ለ) አዲሱ የይሖዋ ሕዝብ ወይም ብሔር ምን ዓይነት በረከት አግኝቶአል?
19 ይሖዋ በጥንቱ የሙሴ ዘመን እሥራኤላውያንን በአንድ ብሔር ባደራጀበት ጊዜ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር። ለዚህም ቃል ኪዳን ታማኝ ሆነው ከኖሩ በእርሱ ፊት የካህናት መንግስት እንደሚሆኑለት ቃል ገብቶላቸው ነበር። (ዘጸአት 19:5, 6) እሥራኤላውያን ግን ታማኞች ሆነው ስላልተገኙ ይህን ቃል አልፈጸመላቸውም። ኢየሱስ መካከለኛ በሆነለት አዲስ ቃል ኪዳን አማካኝነት የተገኘው አዲስ ብሔር ግን በታማኝነት ጸንቶአል። ንጉሥና ካሕናት በመሆን ቅን ልብ ያላቸውን የሰው ዘሮች ከይሖዋ ጋር እንዲታረቁ ይረዳሉ። (ቆላስይስ 1:20) አዲሱ ዝማሬ “ . . . ለአምላካችን መንግሥትና ካሕናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ” ይላል። (ራእይ 5:10) እነዚህ 24 ሽማግሌዎች ይህን አዲስ የውዳሴ መዝሙር ከፍ ያለ ክብር ለተጎናጸፈው ለኢየሱስ ለመዘመር በመቻላቸው ምንኛ ይደሰቱ ይሆን!
-