የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 3
    • የነጩ ፈረስ ጋላቢ

      ራእዩ እንዲህ በማለት ይጀምራል፦ “እኔም አየሁ፣ እነሆ ነጭ ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እሱም ድል እያደረገ ወጣ፤ ድሉንም ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ገሰገሰ።”—ራእይ 6:2

      የነጩ ፈረስ ጋላቢ ማን ነው? የዚህን ጥያቄ መልስ ከዚሁ ከራእይ መጽሐፍ ላይ ማግኘት እንችላለን፤ የራእይ መጽሐፍ በሌላ ጥቅስ ላይ ይህ ጋላቢ “የአምላክ ቃል” እንደሆነ ይናገራል። (ራእይ 19:11-13) ቃል የሚለው ማዕረግ የተሰጠው የአምላክ ቃል አቀባይ ሆኖ ለሚያገለግለው ለኢየሱስ ነው። (ዮሐንስ 1:1, 14) በተጨማሪም “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” እንዲሁም “ታማኝና እውነተኛ” ተብሎ ተጠርቷል። (ራእይ 19:11, 16) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ኢየሱስ ተዋጊ ንጉሥ ነው፤ የተሰጠውን ሥልጣን ደግሞ ተገቢ ባልሆነ ወይም ጨቋኝ በሆነ መንገድ አይጠቀምበትም። ሆኖም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

      ኢየሱስ ድል እንዲያደርግ ሥልጣን የሰጠው ማን ነው? (ራእይ 6:2) ነቢዩ ዳንኤል “የሰው ልጅ የሚመስል” ተብሎ የተገለጸው መሲሕ ‘ከዘመናት በፊት የነበረው’ ከተባለው ከይሖዋ አምላክa “የገዢነት ሥልጣን፣ ክብርና መንግሥት” ሲቀበል በራእይ ተመልክቷል። (ዳንኤል 7:13, 14) ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው የመግዛትና ፍርድ የማስፈጸም ሥልጣንም ሆነ መብት ለኢየሱስ የሰጠው ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አብዛኛውን ጊዜ ነጭ ቀለምን ጽድቅን ለማመልከት ይጠቀምበታል፤ በመሆኑም ነጩ ፈረስ የአምላክ ልጅ በጽድቅ የሚያከናውነውን ጦርነት የሚያመለክት ተስማሚ ምሳሌ ነው።—ራእይ 3:4፤ 7:9, 13, 14

      ፈረሰኞቹ መጋለብ የጀመሩት መቼ ነው? የመጀመሪያው ጋላቢ ማለትም ኢየሱስ መጋለብ የጀመረው አክሊል ሲሰጠው መሆኑን ልብ በል። (ራእይ 6:2) ታዲያ ኢየሱስ በሰማይ ላይ ንጉሥ ሆኖ አክሊሉን የተቀበለው መቼ ነው? ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ባረገበት ወቅት ነው? አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ ሥልጣን እስኪሰጠው ድረስ የተወሰነ ጊዜ መጠበቅ አስፈልጎታል። (ዕብራውያን 10:12, 13) ኢየሱስ ለተከታዮቹ ይህ ጊዜ ተጠናቆ በሰማይ ላይ መግዛት የሚጀምረው መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ምልክት ሰጥቷቸዋል። መግዛት በሚጀምርበት ጊዜ በዓለም ላይ ያሉ ሁኔታዎች መባባስ እንደሚጀምሩ ይኸውም ጦርነት፣ የምግብ እጥረት እንዲሁም ቸነፈር እንደሚከሰት ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:3, 7፤ ሉቃስ 21:10, 11) በ1914 አንደኛው የዓለም ጦርነት ከፈነዳ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ በማለት የሚጠራው በመከራ የተሞላ ጊዜ እንደጀመረ ግልጽ ሆነ።—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

      ታዲያ ኢየሱስ በ1914 አክሊል ከተሰጠው በኋላ ሁኔታዎች ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሱ የሄዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ኢየሱስ በወቅቱ መግዛት የጀመረው በምድር ሳይሆን በሰማይ ላይ ነው። በዚያን ጊዜ በሰማይ ላይ ጦርነት ተነሳ፤ ሚካኤል ተብሎ የተጠራው አዲሱ ንጉሥ ኢየሱስ፣ ሰይጣንንና አጋንንቱን ወደ ምድር ወረወራቸው። (ራእይ 12:7-9, 12) ወደ ምድር የተጣለው ሰይጣን የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ስላወቀ ከዚያ ጊዜ አንስቶ በታላቅ ቁጣ ተሞልቷል። አምላክ በቅርቡ በሰይጣን ላይ እርምጃ በመውሰድ በምድር ላይ ፈቃዱን ያስፈጽማል። (ማቴዎስ 6:10) አሁን ደግሞ ቀሪዎቹ ሦስት ፈረሰኞች፣ የምንኖረው በመከራ በተሞሉት ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ውስጥ እንደሆነ የሚያረጋግጡት እንዴት እንደሆነ እንመልከት። ኢየሱስን ከሚያመለክተው ከመጀመሪያው ፈረሰኛ በተለየ መልኩ ቀሪዎቹ ሦስት ፈረሰኞች በመላው የሰው ልጅ ማኅበረሰብ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ ሁኔታዎችን ያመለክታሉ።

  • አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 3
    • በነጭ ፈረስ የሚጋልበው ኢየሱስ ድል ሲቀዳጅ ምድር ገነት ትሆናለች

      ራእይ 6:1, 2

      ነጩ ፈረስ

      ጋላቢው ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታል። በ1914 መግዛት ጀምሯል፤ በቅርቡ ድሉን ሙሉ በሙሉ የሚያጠናቅቅ ሲሆን መከራን ከምድር ገጽ ያስወግዳል።

  • አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 3
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ