የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አራት ፈረሰኞች እየጋለቡ ናቸው!
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 14. ዮሐንስ ቀጥሎ ምን ዓይነት ፈረስና ፈረሰኛ ተመለከተ? ይህስ ራእይ ምን ያመለክታል?

      14 ታዲያ ይህ “ና” የሚለው ሁለተኛ ትዕዛዝ ምላሽ ያገኘው እንዴት ነው? በዚህ መንገድ ነበር:- “ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፣ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፣ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።” (ራእይ 6:4) በእርግጥም የሚያስጨንቅ ራእይ ነው። ይህ ራእይ ጦርነትን እንደሚያመለክት ምንም አያጠራጥርም። ሆኖም ይህ ጦርነት ድል አድራጊው በይሖዋ የተሾመ ንጉሥ የሚያደርገው የጽድቅ ጦርነት ሳይሆን የማይፈለግ ደም መፋሰስና ሥቃይ የሚያስከትለው ሰው ሠራሽ የጭካኔ ጦርነት ነው። ይህ ጋላቢ ፍም በሚመስል ቀይ ፈረስ ላይ መጋለቡ እንዴት ተገቢ ነው!

      15. ከሁለተኛው ፈረስ ግልቢያ ምንም ዓይነት ተካፋይነት እንዲኖረን የማንፈልገው ለምንድን ነው?

      15 ስለ አምላክ ሕዝቦች “ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይማሩም” የሚል ትንቢት ስለተነገረ ዮሐንስ ከዚህ ፈረሰኛ ግልቢያ ምንም ዓይነት ተካፋይነት እንዲኖረው እንደማይፈልግ የታወቀ ነው። (ኢሳይያስ 2:4) ዮሐንስም ሆነ የዘመናችን የዮሐንስ ክፍል አባሎችና እጅግ ብዙ ሰዎች በዚህ ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ቢሆኑም የዚህ በደም የተበከለው ሥርዓት ክፍል አይደሉም። የጦር መሣሪያዎቻችን ከሥጋዊ ትጥቅ የተለዩና መንፈሣዊ ሲሆኑ እውነትን በትጋት ለማወጅ ‘የአምላክ ኃይል’ አላቸው።—ዮሐንስ 17:11, 14፤ 2 ቆሮንቶስ 10:3, 4

      16. የቀዩ ፈረስ ጋላቢ “ትልቅ ሠይፍ” የተሰጠው መቼና እንዴት ነበር?

      16 የነጩ ፈረስ ጋላቢ ዘውድ ከተቀበለበት ከ1914 በፊት ብዙ ጦርነቶች ተደርገው ነበር። አሁን ግን የቀዩ ፈረስ ጋላቢ “ታላቅ ሠይፍ” ተሰጥቶታል። ታዲያ ይህ ነገር ምን ያመለክታል? የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከፈነዳበት ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጆች ጦርነት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በጣም አሰቃቂና አጥፊ እየሆነ መጥቶአል። ደም እንደ ውኃ በፈሰሰባቸው ከ1914-1918 በነበሩት ዓመታት ታንኮች፣ የመርዝ ጭስ፣ አይሮፕላኖች፣ ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች፣ ትላልቅ መድፎችና አውቶማቲክ መሣሪያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ከዚያ በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን ውጊያ ላይ ውለዋል። በ28 አገሮች የውትድርና ሞያተኞች ብቻ ሳይሆኑ የየአገሮቹ ዜጎች በሙሉ በጦርነቱ እንዲካፈሉ ተገድደዋል። የጦር ጉዳተኞች መጠን እጅግ በጣም ብዙ ነበር። ከዘጠኝ ሚልዮን የሚበልጡ ወታደሮች ሲሞቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰላማውያን ሰዎች ተገድለዋል። ከዚህ ጦርነት በኋላም እንኳ ቢሆን እውነተኛ ሰላም ወደ ምድር አልተመለሰም። ይህ ጦርነት ከተደረገ ከ50 የሚበልጡ ዓመታት ካለፉ በኋላ የጀርመን ርዕሰ ብሔር የነበሩት ኮንራድ አደናወር “ከ1914 ጀምሮ ከሰው ልጆች ሕይወት አስተማማኝ ኑሮና ጸጥታ ፈጽሞ ጠፍቶአል” ብለዋል። በእርግጥም የቀዩ ወይም የዳማው ፈረስ ጋላቢ ከምድር ላይ ሰላምን እንዲወስድ ተሰጥቶታል።

      17. ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላም ቢሆን “ትልቁ ሠይፍ” ጥቅም ላይ መዋሉ ያልተቋረጠው እንዴት ነው?

      17 የቀዩ ፈረስ ጋላቢ የደም ጥማቱን በዚህ ዓይነት ከቀሰቀሰ በኋላ ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ገባ። የግድያ መሣሪያዎች ይበልጥ ተራቀቁ። በጦርነቱ ያለቁት ሰዎች ቁጥር በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ካለቁት አራት እጥፍ ሆነ። በ1945 ሁለት የአቶም ቦምቦች ጃፓን ላይ ፈነዱና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቅጽበት አለቁ። የቀዩ ፈረስ ጋላቢ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት 55 ሚልዮን ሰዎችን አጭዶአል። ይሁን እንጂ በዚህም በቃኝ አላለም። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከ20 ሚልዮን በላይ ነፍሳት ‘በረዥሙ ሠይፍ’ እንደተሰየፉ በአስተማማኝ ምንጮች ተረጋግጦአል።

      18, 19. (ሀ) ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የተፈጸመው መተራረድ የሚመሰክረው የወታደራዊ ቴክኖሎጂን ድል አድራጊነት ሳይሆን ምን ነገርን ነው? (ለ) በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ምን ዓይነት አደጋ ተደቅኖአል? ይሁን እንጂ የነጩ ፈረስ ጋላቢ ይህን ለማስወገድ ምን ያደርጋል?

      18 ታዲያ ይህን ሁሉ እልቂት የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ድል አድራጊነት ነው ልንል እንችላለንን? ከዚህ ይልቅ ምህረት የማያውቀው የቀይ ፈረስ ጋላቢ በከፍተኛ ፍጥነት በመጋለብ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው። ታዲያ ይህ ግልቢያ የሚያቆመው የት ነው? አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ታስቦበትና ሆን ተብሎ የሚደረገው የኑክሌር ጦርነት ግምት ውስጥ ሳይገባ፣ ሳይታሰብ በድንገት የኑክሌር ጦርነት ሊፈነዳ እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የነጩ ፈረስ ጋላቢ ስለዚህ ጉዳይ ያሰበው ሌላ ነገር መኖሩ ያስደስተናል።

      19 ማኅበረሰቡ በብሔራዊ ኩራትና ጥላቻ ላይ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ ምንም ጊዜ ሊፈነዳ በሚችል የኑክሌር አደጋ ላይ መቀመጡ የማይቀር ነው። ብሔራት ሊደርስባቸው በሚችለው እልቂት ተደናግጠው የኑክሌር መሣሪያዎችን ቢያጠፉም እንኳን መሣሪያዎቹን እንደገና ለመሥራት የሚያስችለው እውቀት ይኖራቸዋል። ባስፈለጋቸው ጊዜ እነዚህን ቀሳፊ የኑክሌር መሣሪያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰው ሊሠሩ ይችላሉ። ስለዚህ በተለመዱት ተራ የጦር መሣሪያዎች የተጀመረ ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፋፍሞ ከፍተኛ እልቂት ሊያስከትል ይችላል ማለት ነው። የነጩ ፈረስ ጋላቢ የቀዩን ፈረስ የእብደት ግልቢያ ለመግታት አንድ ነገር ካላደረገ በዛሬው ጊዜ ብሔራትን የዋጠው ኩራትና ጥላቻ በሰው ዘሮች ሁሉ ላይ እልቂት ሳያመጣ አይቀርም። ንጉሡ ክርስቶስ ሰይጣን በሚቆጣጠረው ዓለም ላይ የሚያገኘውን ድል እስኪፈጽምና በአምላክና በጎረቤት ፍቅር ላይ የተመሠረተ አዲስ ምድራዊ ማኅበረሰብ እስኪያቋቁም ድረስ ግልቢያውን እንደሚቀጥል እርግጠኞች እንሁን። ይህ ዓይነቱ ፍቅር በዚህ ባበደው ዘመናችን የኑክሌር ጥቃት እንዳይነሳ ይገታሉ ከሚባሉት ደካማ ዘዴዎች ሁሉ በጣም የበለጠ ሰላም የማስጠበቅ ኃይል አለው።—መዝሙር 37:9-11፤ ማርቆስ 12:29-31፤ ራእይ 21:1-5

  • አራት ፈረሰኞች እየጋለቡ ናቸው!
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ 94 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      “ከምድር ላይ ሰላምን እንዲወስድ ተሰጠው”

      ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን ወዴት እየመራቸው ነው? ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል የተባለው የቶሮንቶ ካናዳ መጽሔት ጥር 22 ቀን 1987 የዓለም አቀፍ ልማት ጥናት ማዕከል ፕሬዚደንት የሆኑትን የኢቫን ኤል ሄድን ንግግር አትሞ አውጥቶ ነበር። ከዚህም ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል:-

      “በዓለም ውስጥ ከአራት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሊቃውንት መካከል አንዱ የጦር መሣሪያዎችን በመፈልሰፍና በማሻሻል ሥራ የተሠማራ ነው። . . . በ1986 ለዚህ ሥራ የዋለው ጠቅላላ ወጪ በደቂቃ 1.5 ሚልዮን ዶላር ነበር። . . . ለዚህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ ትልቅ ትኩረት በመደረጉ ምክንያት ደህንነታችን ይበልጥ አስተማማኝ ሆኗልን? ልዕለ ኃያላን ያላቸው የኑክሌር መሣሪያ ብዛት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዓመታት በሙሉ በጦርነቱ የተካፈሉት አገሮች በሙሉ ከተጠቀሙባቸው መሣሪያዎች 6,000 ጊዜ እጥፍ ይሆናል። ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት የሚያክሉ ስድስት ሺህ ጦርነቶችን ሊያዋጋ ይችላል ማለት ነው። ከ1945 ጀምሮ ዓለም ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ያረፈችው ከሰባት ሳምንታት ለሚያንስ ጊዜ ብቻ ነው። ከ150 የሚበልጡ የእርስ በርስ ወይም የአገር አቀፍ ጦርነቶች ተደርገዋል። እነዚህም ጦርነቶች የ19.3 ሚልዮን ሰዎችን ሕይወት ቀስፈዋል። አብዛኞቹ ሰዎች የሞቱት በዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለበት አዲስ ዘመን ውስጥ በተፈለሰፉት የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ነው።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ