የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክ እስራኤሎችን ማተም
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • አራቱ ነፋሳት

      3. (ሀ) ዮሐንስ የተመለከተው መላእክት የሚያከናውኑትን የትኛውን ልዩ አገልግሎት ነው? (ለ) ‘አራቱ ነፋሳት’ የምን ምሳሌ ናቸው?

      3 ይሖዋ ይህን ቁጣውን ከመግለጹ በፊት የሰማይ መላእክት ልዩ የሆነ አገልግሎት ይፈጽማሉ። ይህንን አገልግሎታቸውን ዮሐንስ በራእይ ተመልክቶአል። “ከዚህም በኋላ በአራቱ በምድር ማዕዘን ቆመው አራት መላእክት አየሁ። እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።” (ራእይ 7:1) ይህ ነገር ዛሬ ለእኛ ምን ትርጉም አለው? እነዚህ አራት ነፋሳት ክፉ በሆነው ምድራዊ ኅብረተሰብ ላይ፣ እንደ ባሕር በሚናወጠው ክፉ የሰው ዘር ላይ፣ እንዲሁም በምድር ሕዝቦች ድጋፍና እርዳታ በሚንቀሳቀሱት ዛፍ መሰል ገዥዎች ላይ የሚወርደውን የጥፋት ፍርድ በጥሩ ሁኔታ የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው።—ኢሳይያስ 57:20፤ መዝሙር 37:35, 36

      4. (ሀ) አራቱ መላእክት ምን ያመለክታሉ? (ለ) አራቱ ነፋሳት መለቀቃቸው በሰይጣን ምድራዊ ድርጅት ላይ ምን ውጤት ያስከትላል?

      4 እነዚህ አራት መላእክት የጥፋቱን ፍርድ እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ አግደው እንዲያቆዩ ይሖዋ የሚጠቀምባቸውን አራት የመላእክት ክፍሎች የሚወክሉ መሆናቸው ምንም አያጠራጥርም። መላእክቱ አግደውት የነበረውን የመለኮታዊ ቁጣ ነፋስ በአንድ ጊዜ ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምሥራቅና ከምዕራብ ሲለቁ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጥፋት ይደርሳል። ይሖዋ በአራቱ ነፋሳት አማካኝነት የኤላም ሰዎችን በበታተነበት ጊዜ የደረሰውን ሁኔታ የሚመስል ቢሆንም ከዚያ በጣም የበለጠና የከፋ ይሆናል። (ኤርምያስ 49:36-38) ይሖዋ አሞናውያንን ካጠፋበት “አውሎ ነፋስ” የበለጠ ከፍተኛ ጥፋት የሚያስከትል ይሆናል። (አሞጽ 1:13-15) ይሖዋ ሉዓላዊነቱን ለዘላለም በሚያረጋግጥበት የቁጣ ቀን ጸንቶ ለመቆም የሚችል አንድም የሰይጣን ድርጅት ክፍል አይኖርም።—መዝሙር 83:15, 18፤ ኢሳይያስ 29:5, 6

      5. የኤርምያስ ትንቢት የአምላክ ፍርድ መላውን ምድር የሚያጠቃልል መሆኑን እንድንረዳ የሚያስችለን እንዴት ነው?

      5 የአምላክ ፍርድ መላውን ምድር የሚያጠፋ እንደሚሆን እርግጠኛ ለመሆን እንችላለንን? አሁንም ነቢዩ ኤርምያስ የሚለውን እናዳምጥ። “እነሆ፣ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፣ ጽኑም አውሎ ነፋስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል። በዚያም ቀን የእግዚአብሔር [“የይሖዋ፣” NW] ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ።” (ኤርምያስ 25:32, 33) ይህች ዓለም በጨለማ የምትዋጠው ይህ “ጽኑ አውሎ ነፋስ” በሚመጣበት ጊዜ ነው። የዚህ ዓለም ገዥዎች ተጠራርገው ይጠፋሉ። (ራእይ 6:12-14) ይሁን እንጂ የወደፊቱ ሁኔታ ለሁሉ ሰው የጨለመ አይሆንም። ታዲያ አራቱ ነፋሳት ታግደው እንዲቆዩ የተደረገው ለማን ሲባል ነው?

      የአምላክ ባሮች መታተም

      6. መላእክቱ አራቱን ነፋሳት ገትተው እንዲይዙ የሚያዝዘው ማን ነው? ይህስ ለምን ነገር ጊዜ ያስገኛል?

      6 ዮሐንስ በመቀጠል አንዳንዶች ለመዳን እንዴት ምልክት እንደሚደረግባቸው ይገልጻል። እንዲህ ይላል:- “የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፣ ምድርንና ባሕርንም ሊጎዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጉዱ አላቸው።”—ራእይ 7:2, 3

      7. አምስተኛው መልአክ ማን ነው? ማንነቱን እንድናውቅ የሚረዳን የትኛው ማስረጃ ነው?

      7 ይህ አምስተኛ መልአክ ስሙ ማን እንደሆን ባይገለጽም ከፍ ያለ ክብር የተቀዳጀው ጌታ ኢየሱስ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን በቂ ማስረጃ አለን። ኢየሱስ የመላእክት አለቃ በመሆኑ እዚህ ላይ በተጠቀሱት መላእክት ላይ ሥልጣን እንዳለው ተመልክቶአል። (1 ተሰሎንቄ 4:16፤ ይሁዳ 9) ይህ መልአክ የፍርድ ቅጣት ለማስፈጸም “ከፀሐይ መውጫ” እንደሚመጡት ነገሥታት፣ እንደ ይሖዋና እንደ ክርስቶስ፣ እንዲሁም የጥንትዋን ባቢሎን ለማዋረድ እንደ መጡት እንደ ዳርዮስና እንደ ቂሮስ ከምሥራቅ ይወጣል። (ራእይ 16:12፤ ኢሳይያስ 45:1፤ ኤርምያስ 51:11፤ ዳንኤል 5:31) በተጨማሪም ይህ መልአክ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን የማተም ሥራ ስለተሰጠው ኢየሱስን ይመስላል። (ኤፌሶን 1:13, 14) ከዚህም በላይ ነፋሳቱ በሚለቀቁበት ጊዜ በአሕዛብ ላይ ፍርድ የሚያስፈጽመውን ሰማያዊ ሠራዊት የሚመራው ኢየሱስ ነው። (ራእይ 19:11-16) ስለዚህ የአምላክ ባሪያዎች ታትመው እስኪያልቁ ድረስ የሰይጣን ምድራዊ ድርጅት ጥፋት እንዲዘገይ የሚያዝዘው ኢየሱስ ነው ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ነው።

  • የአምላክ እስራኤሎችን ማተም
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ  114 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ