የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክ እስራኤሎችን ማተም
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. መላእክቱ አራቱን ነፋሳት ገትተው እንዲይዙ የሚያዝዘው ማን ነው? ይህስ ለምን ነገር ጊዜ ያስገኛል?

      6 ዮሐንስ በመቀጠል አንዳንዶች ለመዳን እንዴት ምልክት እንደሚደረግባቸው ይገልጻል። እንዲህ ይላል:- “የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፣ ምድርንና ባሕርንም ሊጎዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጉዱ አላቸው።”—ራእይ 7:2, 3

  • የአምላክ እስራኤሎችን ማተም
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 8. የማተሙ ሥራ ምንድን ነው? የተጀመረውስ መቼ ነው?

      8 ይህ ማኅተም ምንድን ነው? እነዚህ የአምላክ ባሮችስ እነማን ናቸው? የማተሙ ሥራ የተጀመረው የመጀመሪያዎቹ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ በተቀቡበት የጰንጠቆስጤ ዕለት በ33 እዘአ ነው። በኋላም አምላክ ‘አሕዛብን ሁሉ’ መጥራትና መቀባት ጀመረ። (ሮሜ 3:29፤ ሥራ 2:1-4, 14, 32, 33፤ 15:14) ሐዋርያው ጳውሎስ ቅቡዓን ክርስቲያኖች የክርስቶስ ንብረት ለመሆናቸው ዋስትና እንዳላቸው ከገለጸ በኋላ “ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን” አምላክ እንደሆነ ጽፎአል። (2 ቆሮንቶስ 1:21, 22፤ ከራእይ 14:1 ጋር አወዳድር።) ስለዚህ እነዚህ ባሪያዎች የአምላክ መንፈሳዊ ልጆች የመሆን መብት ሲሰጣቸው ሰማያዊ ውርሻቸውን ከመቀበላቸው በፊት ልጅነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት፣ ማኅተም ወይም ዋስትና ይቀበላሉ። (2 ቆሮንቶስ 5:1, 5፤ ኤፌሶን 1:10, 11) ይህ ከሆነ በኋላ እንደሚከተለው ለማለት ይችላሉ:- “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፣ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”—ሮሜ 8:15-17

      9. (ሀ) በመንፈስ ከተወለዱት የአምላክ ልጆች ቀሪዎች ምን ዓይነት ጽናት ይፈለጋል? (ለ) የቅቡዓን ፈተና የሚቀጥለው እስከ መቼ ድረስ ነው?

      9 “አብረን መከራ ብንቀበል”፤ ይህ አነጋገር ምን ማለት ነው? ቅቡዓን ክርስቲያኖች የሕይወትን አክሊል እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ በታማኝነት መጽናት ይኖርባቸዋል። (ራእይ 2:10) ‘አንድ ጊዜ የዳነ ለሁልጊዜ ድኖአል’ እንደሚባለው አይደለም። (ማቴዎስ 10:22፤ ሉቃስ 13:24) ከዚህ ይልቅ “መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ” ተብለው ተመክረዋል። በመጨረሻም እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ” ለማለት መቻል ይኖርባቸዋል። (2 ጴጥሮስ 1:10, 11፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:7, 8) ስለዚህ በዚህ ምድር ላይ የቀሩት በመንፈስ የተወለዱ የአምላክ ልጆች ኢየሱስና ኢየሱስን የተከተሉት መላእክት የተፈተኑና የታመኑ “የአምላካችን ባሪያዎች” መሆናቸውን በማረጋገጥ ‘በግንባራቸው ላይ’ የማይፋቅ ማኅተም እስኪያትሙላቸው ድረስ ፈተናውና ብጠራው መቀጠል ይኖርበታል። በዚያ ጊዜ የሚደረገው ማኅተም ዘላለማዊ ምልክት ይሆናል። አራቱ የመከራ ነፋሳት በሚለቀቁበት ጊዜ ከመንፈሣዊ እስራኤላውያን መካከል በሥጋ በምድር ላይ በሕይወት የሚቀሩ ቢኖሩም እንኳን የመጨረሻውን ማኅተም ይቀበላሉ። (ማቴዎስ 24:13፤ ራእይ 19:7) የአባሎቹ ቁጥር ይሟላል።—ሮሜ 11:25, 26

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ