የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እጅግ ብዙ ሰዎች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 22. ዮሐንስ ስለ እጅግ ብዙ ሰዎች ምን ተጨማሪ መረጃ አግኝቶ ነበር?

      22 ዮሐንስ በመለኮታዊው የመልእክት ማስተላለፊያ መስመር በኩል ስለዚህ እጅግ ብዙ ሰዎች ተጨማሪ መረጃ አግኝቶአል። “አለኝም [ሽማግሌው]:- እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው። ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ። ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፣ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፣ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።” —ራእይ 7:14ለ, 15

  • እጅግ ብዙ ሰዎች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 25. (ሀ) እጅግ ብዙ ሰዎች ይሖዋን “ቀንና ሌሊት በመቅደሱ” የሚያመልኩት እንዴት ነው? (ለ) ይሖዋ በእጅግ ብዙ ሰዎች ላይ ‘ድንኳኑን የሚዘረጋው’ እንዴት ነው?

      25 ከዚህም በላይ ቀናተኛ የይሖዋ አገልጋዮች ሆነዋል። “ሌሊትና ቀን በመቅደሱ ያመልኩታል።” አንተስ ከእነዚህ ራሳቸውን ለአምላክ ከወሰኑ እጅግ ብዙ ሰዎች መካከል ነህን? ከሆንክ በታላቁ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ምድራዊ አደባባይ ውስጥ ይሖዋን ዘወትር የማገልገል መብት አለህ። በዛሬው ጊዜ እጅግ ብዙ ሰዎች በቅቡዓን አመራር ሥር ሆነው አብዛኛውን የስብከት ሥራ በማከናወን ላይ ናቸው። ሥጋዊ ኃላፊነቶች ቢኖሩባቸውም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ጊዜያቸውን አብቃቅተው የሙሉ ጊዜ አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል ችለዋል። ከእነዚህ አቅኚዎች መካከል ሆንክም አልሆንክ ራስህን የወሰንክ የእጅግ ብዙ ሰዎች ክፍል ስለሆንክ በእምነትህና በሥራህ ምክንያት የአምላክ ወዳጅ ለመሆን እንደ ጻድቅ ተቆጥረህ በአምላክ ድንኳን ውስጥ እንድታድር ስለ ተጋበዝክ ደስ ሊልህ ይገባል። (መዝሙር 15:1-5፤ ያዕቆብ 2:21-26) ስለዚህ ይሖዋ በሚወዳቸው ሁሉ ላይ ድንኳኑን ይዘረጋል። ጥሩ አስተናጋጅ በመሆኑም እንግዶቹን ይጠብቃል።—ምሳሌ 18:10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ