የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጀመሪያው ወዮታ፣ አንበጦች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 9. አንበጦቹ ምን የውጊያ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል?

      9 እነዚህ አንበጦች የተሰጣቸው የጦርነት መመሪያ ምን ነበር? ዮሐንስ ይነግረናል። “የእግዚአብሔር ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆን ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተባለላቸው። አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም። እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው። በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፣ አያገኙትምም። ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።”—ራእይ 9:4-6

  • የመጀመሪያው ወዮታ፣ አንበጦች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 11. (ሀ) አንበጦቹ የአምላክን ጠላቶች ለምን ያህል ጊዜ እንዲጎዱ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል? ይህስ አጭር ጊዜ ያልሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ሥቃዩ ምን ያህል ከባድ ነው?

      11 ሥቃዩ የሚቆየው ለአምስት ወራት ነው። ታዲያ ይህ አጭር ጊዜ አይደለምን? ቃል በቃል ለአንበጣ አጭር ጊዜ አይደለም። አምስት ወር የአንድ አንበጣ አማካይ ዕድሜ ነው። ስለዚህ ዘመናዊዎቹ አንበጦች የአምላክን ጠላቶች የሚነድፉት በሕይወት በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ ነው። ከዚህም በላይ ሥቃዩ በጣም ከባድ ስለሆነ ሰዎች ሞትን እስከመምረጥ ይደርሳሉ። እውነት ነው፣ አንበጦቹ ከነደፉአቸው ሰዎች መካከል ራሳቸውን ለመግደል የሞከሩ እንዳሉ የሚያረጋገጥ ማስረጃ የለንም። ቢሆንም የአነጋገሩ ዘይቤ እንደ ጊንጥ ንክሻ የሚያሳምመው ሥቃይ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንድንረዳ ያስችለናል። ይህም ሁኔታ ኤርምያስ አስቀድሞ ከተመለከተው ባቢሎናውያን ወራሪዎች በሚበታትኑአቸው ከሃዲ እሥራኤላውያን ላይ ካደረሱት ሥቃይ ጋር የሚመሳሰል ነው። እነዚህ እስራኤላውያን ከመኖር ሞትን መርጠው ነበር።—ኤርምያስ 8:3፤ በተጨማሪም መክብብ 4:2, 3ን ተመልከት።

      12. አንበጦቹ የሕዝበ ክርስትናን ሃይማኖታዊ መሪዎች በመንፈሣዊ መንገድ እንዲያሠቃዩአቸው እንጂ እንዳይገድሏቸው ሥልጣን የተሰጣቸው ለምንድን ነው?

      12 እነዚህን ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ እንዲያሠቃዩአቸው እንጂ እንዳይገድሉአቸው ሥልጣን የተሰጣቸው ለምንድን ነው? ይህ መቅሰፍት የሕዝበ ክርስትናን ውሸታምነትና ውድቀትዋን የሚያጋልጥ የመጀመሪያ ወዮታ ነው። መንፈሳዊው በድንነትዋ ግን የሚጋለጠው ቆየት ብሎ ማለትም የጌታ ቀን እየገፋ ሲሄድና ሞት መሰሉ መንፈሳዊ ሁኔታዋ ሙሉ በሙሉ ሲታወቅ ነው። ይህም የሚፈጸመው ከሰዎች ሲሶው በሚገደሉበት በሁለተኛው ወዮታ ጊዜ ነው።—ራእይ 1:10፤ 9:12, 18፤ 11:14

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ