የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጀመሪያው ወዮታ፣ አንበጦች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 13. አንበጦቹ ምን ዓይነት መልክ ነበራቸው?

      13 እነዚህ አንበጦች በጣም አስደናቂ መልክ አላቸው። ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይገልጽልናል:- “የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደተዘጋጁ ፈረሶች ነው፣ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፣ የሴቶችን ጠጉር የሚመስል ጠጉር ነበራቸው፣ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ። የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው። የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።”—ራእይ 9:7-9

  • የመጀመሪያው ወዮታ፣ አንበጦች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 15. የአንበጦቹ (ሀ) የብረት ጥሩር (ለ) እንደ ሰው ያለ ፊት (ሐ) እንደ ሴቶች ያለ ጠጉር (መ) እንደ አንበሳ ያለ ጥርስ (ሠ) የሚያሰሙት ከፍተኛ ድምፅ ምን ትርጉም አለው?

      15 በራእዩ ውስጥ አንበጦቹ የብረት ጥሩር እንዳላቸው ተገልጾአል። ይህም በምንም ነገር የማይፈርስ የጽድቅ አቋም እንዳላቸው ያመለክታል። (ኤፌሶን 6:14-18) በተጨማሪም የሰው ፊት አላቸው። ይህ ደግሞ ሰው የተፈጠረው ፍቅር በሆነው አምላክ ምሳሌ ስለሆነ የፍቅርን ባሕርይ ያመለክታል። (ዘፍጥረት 1:26፤ 1 ዮሐንስ 4:16) ፀጉራቸው እንደ ሴት ፀጉር ረዥም ነው። ይህም ንጉሣቸው ለሆነው ለጥልቁ መልአክ የሚገዙ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። ጥርሳቸውም የአንበሳ ጥርስ ይመስላል። አንበሳ ጥርሱን የሚጠቀመው ሥጋ ለመቦጨቅ ነው። የዮሐንስ ክፍል ከ1919 ጀምሮ ጠንካራ መንፈሳዊ ምግብ ለመመገብ ችሎአል። ይህ በተለይ “ከይሁዳ ነገድ የሆነውን አንበሳ” የኢየሱስ ክርስቶስን መንግሥት እውነቶች መመገብን ያመለክታል። አንበሳ ድፍረትን እንደሚያመለክት ሁሉ ይህን የሚያሳምም መልእክት አኝኮ ለማዋሃድ፣ በጽሑፎች ላይ ለማውጣትና በምድር ሁሉ ለማሰራጨት ከፍተኛ ድፍረት ጠይቆአል። እነዚህ ምሳሌያዊ አንበጦች ከፍተኛ ድምፅ እንዲሰማ አድርገው ነበር። ይህም ድምፅ “ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።” የመጀመሪያውን መቶ ዘመን ክርስቲያኖች አርዓያ ስለሚከተሉ ዝም ለማለት አይፈልጉም።—1 ቆሮንቶስ 11:7-15፤ ራእይ 5:5

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ