የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታት
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • ኮከቦቹና መቅረዞቹ

      5. ኢየሱስ “ሰባቱን ከዋክብትና” “ሰባቱን መቅረዞች” የገለጸው እንዴት ነው?

      5 ኢየሱስ በሰባት የወርቅ መቅረዞች መካከል እንደቆመና ሰባት ከዋክብት በቀኝ እጁ እንደያዘ ዮሐንስ ተመልክቶ ነበር። (ራእይ 1:12, 13, 16) አሁን ደግሞ ኢየሱስ እንደሚከተለው በማለት ያብራራል:- “በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው። ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት [“ጉባኤዎች፣” NW] መላእክት ናቸው። ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት [“ጉባኤዎች፣” NW] ናቸው።”—ራእይ 1:20

  • አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታት
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 9. (ሀ) ሰባቱ መቅረዞች ምን ያመለክታሉ? እነዚህስ በመቅረዝ መመሰላቸው ትክክል የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ራእዩ ሐዋርያው ዮሐንስን ስለምን ነገር አሳስቦት ሊሆን ይችላል?

      9 ሰባቱ መቅረዞች ዮሐንስ የራእይን መጽሐፍ የጻፈላቸው ሰባቱ ጉባኤዎች ናቸው። እነርሱም:- ኤፌሶን፣ ሰምርኔስ፣ ጴርጋሞን፣ ትያጥሮን፣ ሰርዴስ፣ ፊልድልፍያ እና ሎዶቅያ ናቸው። ጉባኤዎች በመቅረዝ የተመሰሉት ለምንድን ነው? ክርስቲያኖች በግለሰብ ደረጃም ሆነ በአጠቃላይ በጉባኤ ደረጃ በዚህ በጨለማ በተዋጠው ዓለም ውስጥ ‘ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲታይ ማድረግ’ ስለሚኖርባቸው ነው። (ማቴዎስ 5:14-16) በተጨማሪም በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ውስጥ ከነበሩት ዕቃዎች መካከል መቅረዞች ይገኙ ነበር። ስለዚህ ጉባኤዎቹ መቅረዞች ተብለው መጠራታቸው እያንዳንዱ የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ በምሳሌያዊ ሁኔታ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” ማለትም የአምላክ መንፈስ መኖሪያ መሆኑን ለዮሐንስ ያስገነዝበዋል። (1 ቆሮንቶስ 3:16) ከዚህም በላይ የአይሁድ ቤተ መቅደስ ጥላ በሆነለት የይሖዋ ታላቅ መንፈሳዊ የቤተ መቅደስ ዝግጅት ውስጥ የቅቡዓን ጉባኤ አባሎች “የንጉሥ ካህናት” ሆነው ያገለግላሉ። ይህም ቤተ መቅደስ ይሖዋ ራሱ በሰማያዊው ቅድስተ ቅዱሳን የሚኖርበትና ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናት ሆኖ የሚያገለግልበት ነው።—1 ጴጥሮስ 2:4, 5, 9፤ ዕብራውያን 3:1፤ 6:20፤ 9:9-14, 24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ