የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • ‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

      በ1919 ሁለት ተዛማጅ የሆኑ ትንቢቶች ማለትም ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ እና ‘ስለ ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገሩት ራእዮች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ የሚገልጸው ራእይ ረጅም ጊዜ (በርካታ መቶ ዘመናት) የሚሸፍን ሲሆን ይህ ጊዜ የሚያበቃው እጅግ ብዙ የሆኑ የአምላክ ሕዝቦች ወደ ሕይወት ሲመለሱ ነው። (ሕዝ. 37:2-4፤ ራእይ 11:1-3, 7-13) ስለ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገረው ትንቢት ደግሞ አጭር ጊዜ (ከ1914 መገባደጃ እስከ 1919 መጀመሪያ) የሚሸፍን ሲሆን ይህ ጊዜ የሚያበቃው ጥቂት የአምላክ አገልጋዮችን ያቀፈ ቡድን ወደ ሕይወት ሲመለስ ነው። ሁለቱም ትንቢቶች ምሳሌያዊ የሆነን ትንሣኤ የሚያመለክቱ ናቸው፤ እንዲሁም ሁለቱም ትንቢቶች ይሖዋ በ1919 ቅቡዓን አገልጋዮቹ ‘በእግራቸው እንዲቆሙ፣’ ከታላቂቱ ባቢሎን ምርኮ ነፃ እንዲወጡና መልሶ በተቋቋመው ጉባኤ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ባደረገበት ጊዜ ዘመናዊ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።—ሕዝ. 37:10

      ይሁን እንጂ በሁለቱ ትንቢቶች ፍጻሜ መካከል አንድ ወሳኝ ልዩነት እንዳለ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ የሚናገረው ትንቢት የሚተነብየው ሁሉም ቅቡዓን ቀሪዎች ወደ ሕይወት ስለመመለሳቸው ነው። ስለ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገረው ትንቢት ግን የሚተነብየው ጥቂት ቅቡዓን ቀሪዎች ማለትም በድርጅቱ ውስጥ ግንባር ቀደም ሆነው ሥራውን ይመሩ የነበሩትና “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆነው የተሾሙት ቅቡዓን ወደ ሕይወት ስለመመለሳቸው ነው።—ማቴ. 24:45፤ ራእይ 11:6a

      ከሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. እስከ 1919 የነበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች።
  • ‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
      1. 1919 መጀመሪያ

        1919፦ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ ሕያው ሆኑ፤ ይህ የሆነው በድርጅቱ ውስጥ ግንባር ቀደም ሆነው ሥራውን ይመሩ የነበሩትን ጥቂት ቅቡዓን ወንድሞች ያቀፈው ቡድን “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆኖ ሲሾም ነው

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ