የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁለቱን ምሥክሮች እንደገና ሕያው ማድረግ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 23. (ሀ) ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ሁለቱ ምሥክሮች ምን ሆኑ? ይህስ ጠላቶቻቸው ምን እንዲሰማቸው አደረገ? (ለ) ራእይ 11:11, 12 እና ይሖዋ በሸለቆ ውስጥ በነበሩት ደረቅ አጥንቶች ላይ እፍ ስለ ማለቱ የሚናገረው የሕዝቅኤል ትንቢት ዘመናዊ ፍጻሜያቸውን ያገኙት መቼ ነው?

      23 ታላላቅ ጋዜጦችም የአምላክን ሕዝቦች በመንቀፍ ከቀሳውስት ጋር ተባብረዋል። አንድ ጋዜጣ “ያለቀለት ምሥጢር አለቀለት!” ብሎ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ አባባል ነበር። ሁለቱ ምሥክሮች እንደሞቱ አልቀሩም። እንዲህ እናነባለን:- “ከሦስቱ ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ፣ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው። በሰማይም:- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።” (ራእይ 11:11, 12) ስለዚህ ሕዝቅኤል በራእይ ተመልክቶት በነበረው ሸለቆ ውስጥ የነበሩት አጽሞች ያጋጠማቸውን የመሰለ ሁኔታ አጋጠማቸው። በእነዚህ ደረቅ አጽሞች ላይ ይሖዋ እፍ አለባቸውና ሕያው ሆኑ። ይህም የሆነው የእስራኤል ብሔር በባቢሎን ለ70 ዓመት በግዞት ከቆየ በኋላ እንደገና የሚወለድ መሆኑን ለማመልከት ነበር። (ሕዝቅኤል 37:1-14) እነዚህ የሕዝቅኤልና የራእይ ሁለት ትንቢቶች ዘመናዊ ፍጻሜያቸውን ያገኙት ይሖዋ ‘ሞተው’ የነበሩትን ምሥክሮቹን አዲስ ሕይወትና ኃይል ሰጥቶ ባስነሳበት በ1919 ነበር።

  • ሁለቱን ምሥክሮች እንደገና ሕያው ማድረግ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 25. (ሀ) ሁለቱ ምሥክሮች “ወደዚህ ውጡ” የተባሉት መቼ ነበር? ይህስ የተፈጸመው እንዴት ነው? (ለ) የሁለቱ ምሥክሮች ወደ ሕይወት መመለስ በታላቂቱ ከተማ ላይ እንዴት ያለ ድንጋጤ አመጣ?

      25 ሕዝበ ክርስትና በ1918 አግኝታ የነበረውን ድል ለማግኘት በተደጋጋሚ ሞክራ ነበር። ረብሻ በማነሳሳት፣ ሕጎችን በማጣመም፣ በማሳሰርና በማስገደልም ጭምር የተቻላትን ሁሉ አደረገች። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ አልተሳካላትም። ከ1919 በኋላ የሁለቱ ምሥክሮች መንፈሳዊ ግዛት በሕዝበ ክርስትና ሊደፈር በማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ። ይሖዋ በዚህ ዓመት ለሕዝቦቹ “ወደዚህ ውጡ” አላቸው። እነርሱም ትዕዛዙን ተቀብለው ጠላቶቻቸው ሊመለከቱት እንጂ መንካት ወደማይችሉበት ከፍተኛ መንፈሳዊ ደረጃ ላይ ወጡ። በዚህ ዓይነት እንደገና መቋቋማቸው በታላቂቱ ከተማ ላይ ስላስከተለው ድንጋጤ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይገልጽልናል:- “በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፣ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፣ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፣ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፣ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።” (ራእይ 11:13) በሃይማኖት ዓለም ውስጥ ታላቅ መናወጥ ሆኖ ነበር። እነዚህ ሕያው የተደረጉ ክርስቲያኖች ሥራቸውን ማከናወን በጀመሩ ጊዜ ተቋቁመው የኖሩት ሃይማኖቶች መሪዎች የቆሙበት መሬት ከሥራቸው የከዳቸው መስሎ ነበር። የከተማቸው አንድ አሥረኛና ምሳሌያዊ 7,000 ሰዎች በነገሩ በጣም ስለተነኩ እንደተገደሉ ተነግሮአል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ