-
የአምላክ መንግሥት ተወለደ!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
2. (ሀ) ዮሐንስ ምን ታላቅ ምልክት ተመለከተ? (ለ) የታላቁ ምልክት ትርጉም የተገለጸው መቼ ነው?
2 አሁን ዮሐንስ ታላቅ ምልክት አየ። ይህ ምልክት የአምላክን ሕዝቦች ትኩረት የሚስብ ነው። በጣም አስደናቂ የሆነ ትንቢታዊ ራእይ የሚያስተዋውቅ ሲሆን የዚህም ራእይ ትርጉም በመጋቢት 1, 1925 መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ “የብሔር መወለድ” በሚል ርዕሰ ትምህርትና በ1926 ደግሞ ነፃ መውጣት በተባለው መጽሐፍ ተብራርቶ ነበር። ይህ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ያስቻለው ደማቅ ብርሃን በይሖዋ ሥራ እድገት ላይ ታሪካዊ የሆነ ምዕራፍ ከፍቶአል። ስለዚህ ዮሐንስ ድራማውን ሲገልጽልን እናዳምጥ:- “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፣ ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፣ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።”—ራእይ 12:1, 2
-
-
የአምላክ መንግሥት ተወለደ!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
6. (ሀ) ዮሐንስ የተመለከታት ሴት ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ከእግሮችዋ በታች ጨረቃ ያላትና የከዋክብት አክሊል የደፋች መሆንዋ ምን ያመለክታል? (ለ) የእርጉዝዋ ሴት በምጥ መያዝ የምን ምሳሌ ነው?
6 ይህች ሴት ፀሐይን እንደተጎናጸፈችና ከእግርዋም በታች ጨረቃ እንዳለ ዮሐንስ ተመልክቶአል። በዚህ ላይ አክሊል የሆኑላትን ከዋክብት ስንጨምር ሙሉ በሙሉ በሰማያዊ ብርሃናት ተከብባለች ማለት ነው። የአምላክ ሞገስ በቀንዋና በሌሊትዋ ላይ ያበራላታል። ይህ ሁሉ ዕፁብ ድንቅ ለሆነው ለይሖዋ ሰማያዊ ድርጅት የሚስማማ ምልክት ነው። በተጨማሪም ምጥ የጀመራት ነፍሰ ጡር ሴት ነበረች። መለኮታዊ እርዳታ እንዲሰጣት መጮኋ የምትወልድበት ጊዜ መድረሱን ያመለክታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምጥ አንድ ትልቅ ውጤት ለማስገኘት የሚያስፈልገውን አድካሚ ሥራ ያመለክታል። (ከመዝሙር 90:2፤ ከምሳሌ 25:23 [NW] እና ከኢሳይያስ 66:7, 8 ጋር አወዳድር።) የይሖዋ ሰማያዊት ድርጅት ለዚህ ታሪካዊ የሆነ የመውለጃ ጊዜ ስትዘጋጅ የምጥ ጣር ይዞአት እንደነበረ አያጠራጥርም።
-