የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እንዳትታለል ተጠንቀቅ
    መጠበቂያ ግንብ—2004 | የካቲት 15
    • 5. በዚህ የመጨረሻ ዘመን ሰይጣን የማታለል ድርጊቱን ይበልጥ አጠናክሮ የገፋበት እንዴት ነው? ዋነኛ ዒላማው ያደረገውስ እነማንን ነው?

      5 በዚህ የመጨረሻ ዘመን ሰይጣን የማታለል ድርጊቱን ይበልጥ አጠናክሮ ገፍቶበታል። ከሰማይ ወደ ምድር የተወረወረ ከመሆኑም በላይ የቀረው ጊዜ አጭር እንደሆነ ስለሚያውቅ እጅግ ‘ተቆጥቷል።’ የተቻለውን ያህል ብዙ ሰዎችን ይዞ ለመጥፋት ቆርጦ ስለተነሳ ‘ዓለሙን ሁሉ በማሳት’ ላይ ይገኛል። (ራእይ 12:9, 12) ሰይጣን ሰዎችን የሚያታልለው እንዲሁ አልፎ አልፎ ብቻ አይደለም። የሰው ልጆችን ከማሳት የቦዘነበት ጊዜ የለም።a የማያምኑ ሰዎችን ልቦና ለማሳወርና ወደ አምላክ እንዳይቀርቡ ለማድረግ ያሉትን የማታለያ ዘዴዎች ሁሉ ይጠቀማል። (2 ቆሮንቶስ 4:4) ይህ የወጣለት አታላይ በተለይ አምላክን “በመንፈስና በእውነት” የሚያመልኩትን ለመዋጥ ቆርጦ ተነስቷል። (ዮሐንስ 4:24፤ 1 ጴጥሮስ 5:8) ሰይጣን ‘ማንኛውንም ሰው ከአምላክ እንዲርቅ ማድረግ እችላለሁ’ ብሎ በተዘዋዋሪ መንገድ እንደተከራከረ አትዘንጋ። (ኢዮብ 1:9-12) ሰዎችን ‘ለመሸንገል’ ወይም ለማታለል የሚጠቀምባቸው አንዳንድ ዘዴዎች ምን እንደሆኑና በእነዚህ የተንኮል ዘዴዎች እንዳንታለል እንዴት መጠንቀቅ እንደምንችል እስቲ እንመልከት።—ኤፌሶን 6:11

  • እንዳትታለል ተጠንቀቅ
    መጠበቂያ ግንብ—2004 | የካቲት 15
    • a አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደሚገልጸው በራእይ 12:9 ላይ “የሚያስተው” ተብሎ የተተረጎመው ግስ “ቀጣይ የሆነን ልማዳዊ ድርጊት ያመለክታል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ