የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 2. ሰይጣንና አጋንንቱ እነማን ናቸው?

      አንዳንድ መላእክት ለይሖዋ ታማኝ ሆነው አልቀጠሉም። በአምላክ ላይ ያመፀው የመጀመሪያው መልአክ “መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው ዲያብሎስና ሰይጣን” ነው። (ራእይ 12:9) ሰይጣን በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ መግዛት ስለፈለገ አዳምና ሔዋን በኋላም ሌሎች መላእክት ጭምር አብረውት እንዲያምፁ አደረገ። እነዚህ ዓመፀኛ መላእክት አጋንንት ተብለው ይጠራሉ። ይሖዋ ከሰማይ ወደ ምድር ያባረራቸው ሲሆን ወደፊት ጥፋት ይጠብቃቸዋል።—ራእይ 12:9, 12⁠ን አንብብ።

      3. ሰይጣንና አጋንንቱ ሊያታልሉን የሚሞክሩት እንዴት ነው?

      ሰይጣንና አጋንንቱ፣ በአጋንንታዊ ወይም በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ብዙዎችን ለማታለል ይሞክራሉ፤ አጋንንታዊ ወይም መናፍስታዊ ድርጊት የሚባለው ከመናፍስት ጋር ለመገናኘት የሚደረገው ጥረት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንድ ሰዎች ጠንቋዮችን፣ “አዋቂ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎችን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችንና ምትሃታዊ ኃይል አላቸው የሚባሉ ሰዎችን ያማክራሉ። ሌሎች ደግሞ ከመናፍስት ጋር ንክኪ ያላቸው የሕክምና አማራጮችን ይጠቀማሉ። የሞቱ ሰዎችን ማነጋገር ይቻላል ብለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ። ይሖዋ ግን “ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ” በማለት አስጠንቅቆናል። (ዘሌዋውያን 19:31) ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠን ሰይጣንና አጋንንቱ ከሚያሳድሩት ተጽዕኖ ጥበቃ ሊያደርግልን ስለሚፈልግ ነው። የአምላክ ጠላት የሆኑት እነዚህ ክፉ መናፍስት በእኛ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይፈልጋሉ።

  • የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 2. በዓለም ላይ ከሚከናወኑት ነገሮችና ሰዎች ከሚያሳዩት ባሕርይ ጋር በተያያዘ ከ1914 አንስቶ ምን ለውጥ ታይቷል?

      የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን ‘የመገኘትህና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት ምንድን ነው?’ በማለት ጠይቀውት ነበር። (ማቴዎስ 24:3) ኢየሱስ ለጥያቄያቸው መልስ ሲሰጥ፣ እሱ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ መግዛት ከጀመረ በኋላ የሚከናወኑ በርካታ ነገሮችን ነግሯቸዋል። ከነገራቸው ነገሮች መካከል ጦርነት፣ የምግብ እጥረትና የምድር ነውጥ ይገኙበታል። (ማቴዎስ 24:7⁠ን አንብብ።) መጽሐፍ ቅዱስ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ሰዎች ከሚያሳዩት ባሕርይ የተነሳ ‘ለመቋቋም የሚያስቸግር ዘመን’ እንደሚመጣም አስቀድሞ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) በትንቢቶቹ ላይ የተጠቀሱት ነገሮች፣ በተለይ ከ1914 ወዲህ ጉልህ በሆነ መንገድ መታየት ጀምረዋል።

      3. የአምላክ መንግሥት መግዛት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የዓለም ሁኔታ ይህን ያህል የተባባሰው ለምንድን ነው?

      ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ ብዙም ሳይቆይ በሰይጣንና በአጋንንቱ ላይ በሰማይ ጦርነት ከፈተ። ሰይጣን በጦርነቱ ተሸነፈ። መጽሐፍ ቅዱስ ከዚያ በኋላ ስለሆነው ነገር ሲናገር ‘ሰይጣን ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ’ ይላል። (ራእይ 12:9, 10, 12) ሰይጣን መጥፋቱ እንደማይቀር ስለሚያውቅ በጣም ተቆጥቷል። በመላው ምድር ላይ ሥቃይና መከራ እያደረሰ ያለው በዚህ ምክንያት ነው። ከዚህ አንጻር፣ የዓለም ሁኔታ ይህን ያህል የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ ምንም አያስገርምም! የአምላክ መንግሥት እነዚህን ሁሉ ችግሮች ያስወግዳል።

  • የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 5. ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል

      ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል (1:10)

      ኢየሱስ እሱ ንጉሥ ከሆነ በኋላ በዓለም ላይ የሚታዩትን ሁኔታዎች አስቀድሞ ተናግሯል። ሉቃስ 21:9-11⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • እዚህ ጥቅስ ላይ ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል አንተ ያየኸው ወይም የሰማኸው የትኞቹን ነው?

      ሐዋርያው ጳውሎስ የሰው ልጆች አገዛዝ ከመደምደሙ በፊት ባሉት ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ሰዎች ምን ዓይነት ባሕርይ እንደሚኖራቸው ገልጿል። ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:1-5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በዛሬው ጊዜ ሰዎች የትኞቹን ባሕርያት ሲያንጸባርቁ ተመልክተሃል?

      በመጨረሻዎቹ ቀናት በዓለም ላይ የሚታየውን ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች፦ 1. አንድ ወታደራዊ መሪ መድረክ ላይ ቆሞ እጁን ወደ ላይ እያነሳ ሲጮኽ 2. ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ የፈራረሱ ሕንፃዎች 3. ወታደራዊ አውሮፕላኖች 4. የፊት ማስክ ያደረጉ ሰዎች መንገድ ላይ ሲጓዙ 5. ኒው ዮርክ ውስጥ መንታዎቹ ሕንፃዎች በሽብር ጥቃት ምክንያት በእሳት ሲጋዩ 6. ዕፅ የሚወስድ ሰው 7. ሚስቱ ላይ እየጮኸና ለመማታት እየሞከረ ያለ ባል 8. የተለያዩ ዕፆችና የአልኮል መጠጦች 9. ዘመን አመጣሽ ልብሶችን የለበሱና ጌጣጌጥ ያደረጉ ሴቶች ፎቶ ሲነሱ 11. አንድ ረብሸኛ ቦምብ ሲወረውር
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ