-
የራእይ መጽሐፍ፣ የአምላክን ጠላቶች የሚመለከት ምን ሐሳብ ይዟል?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ግንቦት
-
-
የአምላክ ጠላቶች ማንነት ታወቀ
ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ
‘ከባሕር የወጣ’ አውሬ ሲሆን ሰባት ራሶች፣ አሥር ቀንዶችና አሥር ዘውዶች አሉት። (ራእይ 13:1-4) በታሪክ ዘመናት ውስጥ የሰው ልጆችን ሲያስተዳድሩ የቆዩ የፖለቲካ ኃይሎችን በሙሉ ያመለክታል። ሰባቱ ራሶች በአምላክ ሕዝቦች ላይ የጎላ ተጽዕኖ የነበራቸውን ሰባት የዓለም ኃይሎች ያመለክታሉ (ከአንቀጽ 6-8ን ተመልከት)
6. በራእይ 13:1-4 ላይ የተገለጸው ባለ ሰባት ራስ አውሬ ምን ያመለክታል?
6 ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ ማን ነው? (ራእይ 13:1-4ን አንብብ።) ይህ አውሬ በጥቅሉ ሲታይ ነብር ይመስላል፤ እግሮቹ ግን የድብ፣ አፉ ደግሞ የአንበሳ አፍ ነው፤ አሥር ቀንዶችም አሉት። እነዚህን ገጽታዎች በሙሉ በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ የተገለጹት አራት አራዊት ላይም እናያቸዋለን። በራእይ መጽሐፍ ላይ ግን እነዚህ ገጽታዎች በሙሉ የሚታዩት በአንድ አውሬ ላይ እንጂ በአራት የተለያዩ አራዊት ላይ አይደለም። ይህ አውሬ አንድን መንግሥት ወይም የዓለም ኃይል ብቻ የሚያመለክት አይደለም። አውሬው “በነገድ፣ በሕዝብ፣ በቋንቋና በብሔር ሁሉ ላይ ሥልጣን” እንዳለው ተገልጿል። ስለዚህ አንድን መንግሥት ብቻ ሊያመለክት አይችልም። (ራእይ 13:7) እንግዲያው ይህ አውሬ የሚያመለክተው እስከ ዛሬ የሰው ልጆችን ሲያስተዳድሩ የቆዩ ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች መሆን አለበት።b—መክ. 8:9
-
-
የራእይ መጽሐፍ፣ የአምላክን ጠላቶች የሚመለከት ምን ሐሳብ ይዟል?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ግንቦት
-
-
b ባለ ሰባት ራሱ አውሬ ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች እንደሚያመለክት የሚጠቁመው ሌላው ነገር “አሥር ቀንዶች” ያሉት መሆኑ ነው። አሥር ቁጥር ብዙውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሙላትን ለማመልከት ይሠራበታል።
-