የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገል
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 2 ቅዱሳን ሰማያት በሰይጣንና በአጋንንቱ መታወካቸው ቀርቶአል። እነዚህ ክፉ መናፍስት ከሰማይ ተባርረው በምድር አካባቢ ብቻ ተወስነዋል። በዚህ ዘመን የመናፍስትነት ሥራ በጣም የተስፋፋው በዚህ ምክንያት እንደሆነ አያጠራጥርም። ተንኮለኛው እባብ አሁንም ብልሹ የሆነ መንፈሳዊ ድርጅት አለው። ይሁን እንጂ የሰው ልጆችን ለማሳት የሚገለገልበት የሚታይ ድርጅት ይኖረው ይሆንን? ዮሐንስ ይነግረናል:- “አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፣ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፣ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ። ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፣ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፣ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።”—ራእይ 13:1, 2

      3. (ሀ) ነቢዩ ዳንኤል የትኞቹን የሚያስፈሩ አራዊት በራእይ ተመልክቶ ነበር? (ለ) በ⁠ዳንኤል 7 ላይ የተገለጹት ግዙፍ አራዊት ምን ያመለክቱ ነበር?

      3 ይህ የሚያስፈራ አውሬ ምንድን ነው? መልሱን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ይነግረናል። ባቢሎን በ539 ከዘአበ ከመውደቋ በፊት ዳንኤል የተባለው አይሁዳዊ ነቢይ ስለ አስፈሪ አራዊት ራእይ ተመልክቶ ነበር። በ⁠ዳንኤል 7:2-8 ላይ አራት አራዊት ከባሕር ሲወጡ እንደተመለከተ፣ የመጀመሪያው አንበሳ፣ ሁለተኛው ድብ፣ ሦስተኛው ደግሞ ነብር ይመስል እንደነበረና “እነሆም የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች . . . አሥር ቀንዶች” ያሏት አራተኛ አውሬ እንደተመለከተ ገልጾአል። ይህም ዮሐንስ በ96 እዘአ ገደማ ካየው አውሬ ጋር የሚያስደንቅ ተመሳሳይነት አለው። ያም አውሬ የአንበሳ፣ የድብና የነብር መልክ ነበረው። በተጨማሪም አሥር ቀንዶች ነበሩት። ዳንኤል ያያቸው ታላላቅ አውሬዎች ምንድን ናቸው? ዳንኤል “እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሱ አራት ነገሥታት ናቸው” በማለት ይገልጽልናል። (ዳንኤል 7:17) አዎ፣ እነዚህ አራዊት የ“ነገሥታት” ወይም የፖለቲካዊ ኃይላት ምሳሌ ናቸው።

  • ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገል
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 8. የእንግሊዝና የአሜሪካ ጥምር የዓለም ኃይል በአውሬ መመሰሉ ሊያስደነግጠን የማይገባው ለምንድን ነው?

      8 የሰው ልጆችን የሚያስተዳድሩትን የፖለቲካ ባለሥልጣናት በአውሬ መመሰል የሚያስደነግጥ ነገር አይደለምን? የይሖዋ ምሥክሮች ድርጅታዊና ግለሰባዊ ሕልውና በየፍርድ ቤቶች አጠያያቂ በነበረበት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ያቀርቡባቸው ከነበሩት ክሶች አንዱ ይህ ነበር። ይሁን እንጂ እስቲ ቆም ብለን እናስብ! ብሔራት ራሳቸው አራዊትን ወይም እንስሳትን ብሔራዊ ምልክታቸው አድርገው ይጠቀሙ የለምን? ለምሳሌ ያህል ብሪታንያ አንበሳን፣ አሜሪካ ንሥርን እንዲሁም ቻይና ዘንዶን ብሔራዊ ምስል አድርገው ይጠቀማሉ። ታዲያ የመጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ደራሲ አራዊትን የዓለም ኃያል መንግሥታት ምሳሌ አድርጎ ቢጠቀም ምን የሚነቀፍበት ምክንያት አለ?

      9. (ሀ) አንድ ሰው ሰይጣን ለአውሬው ታላቅ ሥልጣን እንደሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ መግለጹን መቃወም የማይገባው ለምንድን ነው? (ለ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰይጣን እንዴት ተገልጾአል? በመንግሥታትስ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

      9 ከዚህም በላይ አንዳንዶች ለአውሬው ታላቅ ሥልጣን የሰጠው ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ መናገሩን የሚቃወሙት ለምንድን ነው? ይህን የተናገረው አምላክ ነው። ብሔራት ደግሞ በአምላክ ፊት በእንስራ ውስጥ እንዳለ የውኃ ጠብታ ወይም እንደ አቧራ ቅንጣት ናቸው። እነዚህ ብሔራት የአምላክ ትንቢታዊ ቃል ስለ እነርሱ በሚናገረው ቃል ቅር ከመሰኘትና ከማኩረፍ ይልቅ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ቢጣጣሩ ይሻላቸዋል። (ኢሳይያስ 40:15, 17፤ መዝሙር 2:10-12) ሰይጣን የተኮነኑ ነፍሳትን ሩቅ በሚገኝ የሲኦል እሳት ለማሠቃየት የተመደበ አፈ ታሪክ የወለደው ፍጥረት አይደለም። እንዲህ ያለ የሥቃይ ቦታ የለም። ከዚህ ይልቅ ሰይጣን “የብርሃን መልአክ” እንደሚመስል በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተገልጾአል። በጠቅላላው የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ግፊት የሚያደርግ ታላቅ አታላይ ነው።—2 ቆሮንቶስ 11:3, 14, 15፤ ኤፌሶን 6:11-18

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ