-
ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
25. (ሀ) ዮሐንስ ወደ ዓለም መድረክ ስለ ወጣ ሌላ ምሳሌያዊ አውሬ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) የአዲሱ አውሬ ሁለት ቀንዶችና አውሬው ከምድር መውጣቱ ምን ያመለክታሉ?
25 አሁን ደግሞ አንድ ሌላ አውሬ በዓለም መድረክ ላይ ብቅ አለ። ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፣ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር። በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቁስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል። እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።” (ራእይ 13:11-13) ይህ አውሬ ሁለት ቀንዶች አሉት። ይህም የሁለት ፖለቲካዊ ኃይላት ጥምር መሆኑን ያመለክታል። በተጨማሪም ይህ አውሬ የወጣው ከባሕር ሳይሆን ከምድር እንደሆነ ተገልጾአል። ስለዚህ ቀድሞውኑ ተቋቁሞ ከነበረው ከሰይጣን ምድራዊ ሥርዓት ውስጥ የወጣ ነው። ከዚህ በፊት የነበረና በጌታ ቀን ደግሞ ግንባር ቀደም የሥራ ድርሻ የሚኖረው የዓለም ኃያል መንግሥት መሆን ይኖርበታል።
-
-
ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
27. (ሀ) ባለ ሁለት ቀንዱ አውሬ ከሰማይ እሳት እንዲወርድ ማድረጉ ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳለው ያመለክታል? (ለ) በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ለዘመናችን ባለ ሁለት ቀንድ አውሬ እንዴት ያለ አስተያየት አላቸው?
27 ይህ ባለ ሁለት ቀንድ አውሬ ታላላቅ ድንቆችን ይፈጽማል። እንዲያውም ከሰማይ እሳት እንዲወርድ ያደርጋል። (ከማቴዎስ 7:21-23 ጋር አወዳድር።) ይህ የኋለኛው ምልክት ከበኣል ነቢያት ጋር የተገዳደረውን የጥንት የአምላክ ነቢይ ኤልያስን ያስታውሰናል። ኤልያስ በይሖዋ ስም ከሰማይ እሳት ለማውረድ በቻለ ጊዜ እርሱ እውነተኛ የአምላክ ነቢይ እንደሆነና የበኣል ነቢያት ደግሞ ሐሰተኛ መሆናቸው በማያጠራጥር ሁኔታ ተረጋግጦአል። (1 ነገሥት 18:21-40) ባለ ሁለት ቀንዱ አውሬም እንደነዚህ የበኣል ነቢያት የነቢይነት ብቃትና ሹመት እንዳለው ይሰማዋል። (ራእይ 13:14, 15፤ 19:20) እንዲያውም በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች አማካኝነት የክፋት ኃይሎችን አጥፍቼአለሁ ይላል። ደግሞም አምላክ የለሽ በሚባለው ኮምኒዝም ላይ ድል እንደተቀዳጀ ይናገራል! በእርግጥም ብዙ ሰዎች ዘመናዊው ባለ ሁለት ቀንድ አውሬ የነፃነትና የኑሮ ብልጽግና ጠባቂና ተከላካይ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል።
-