-
ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
ወደ ሰማይ የሚሄዱት ምን ያህል ሰዎች ናቸው?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ 144,000 ሰዎች ትንሣኤ አግኝተው ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ይናገራል። (ራእይ 7:4) በራእይ 14:1-3 ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ “በጉ በጽዮን ተራራ ላይ [ቆሞ]” እንዳየ እንዲሁም ‘ከእሱ ጋር 144,000ዎቹ’ እንደነበሩ ተገልጿል። በዚህ ራእይ ላይ “በጉ” ትንሣኤ ያገኘውን ኢየሱስን ያመለክታል። (ዮሐንስ 1:29፤ 1 ጴጥሮስ 1:19) ‘የጽዮን ተራራ’ የሚለው አገላለጽ ደግሞ ኢየሱስና ከእሱ ጋር በሰማይ ላይ የሚገዙት 144,000 ሰዎች ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ ያመለክታል።—መዝሙር 2:6፤ ዕብራውያን 12:22
በአምላክ መንግሥት ውስጥ ከክርስቶስ ጋር እንዲገዙ ‘የተጠሩትና የተመረጡት’ ሰዎች “ትንሽ መንጋ” ተብለው ተጠርተዋል። (ራእይ 17:14፤ ሉቃስ 12:32) ይህም የእነዚህ ሰዎች ቁጥር፣ ከኢየሱስ በጎች አጠቃላይ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ እንደሚሆን ያሳያል።—ዮሐንስ 10:16
-
-
ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
የተሳሳተ አመለካከት፦ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው 144,000 የሚለው ቁጥር ቃል በቃል የሚወሰድ ሳይሆን ምሳሌያዊ ነው።
እውነታው፦ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ምሳሌያዊ ትርጉም ያላቸው ቁጥሮች የሚገኙ ቢሆንም አንዳንዶቹ ቁጥሮች ግን ቃል በቃል የሚወሰዱ ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ የራእይ መጽሐፍ ስለ “12ቱ የበጉ ሐዋርያት 12 ስሞች” ይናገራል። (ራእይ 21:14) በተመሳሳይም 144,000 የሚለው ቁጥር ቃል በቃል ሊወሰድ ይገባል ብለን እንድንደመድም የሚያደርጉንን ማስረጃዎች እንመልከት።
ራእይ 7:4 ‘የታተሙት [ማለትም ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ማረጋገጫ የተሰጣቸው] ሰዎች ቁጥር 144,000’ እንደሆነ ይናገራል። በዚሁ ምዕራፍ ውስጥ “አንድም ሰው ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሕዝብ” ተብሎ የተጠራ ሌላ ቡድን ተጠቅሷል። “እጅግ ብዙ ሕዝብ” የተባሉትንም አምላክ ከጥፋት ያድናቸዋል። (ራእይ 7:9, 10) እንግዲያው 144,000 የሚለው ቁጥር፣ ይህ ነው የማይባል ብዛት ያለውን የሰዎች ቡድን የሚያመለክት ምሳሌያዊ ቁጥር ከሆነ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ንጽጽር ትርጉም አልባ ይሆናል።a
በተጨማሪም 144,000ዎቹ “እንደ በኩራት ሆነው ከሰዎች መካከል [እንደተዋጁ]” ተገልጿል። (ራእይ 14:4) “በኩራት” የሚለው አገላለጽ ሌሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ጥቂት ሰዎችን ያመለክታል። ይህ ቃል በሰማይ ከክርስቶስ ጋር ሆነው፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ቁጥራቸው ያልተወሰነ ተገዥዎችን የሚያስተዳድሩትን ነገሥታት የሚያመለክት ተስማሚ መግለጫ ነው።—ራእይ 5:10
-