የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በቅርቡ መፈጸም ያለባቸው ነገሮች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • የሐሳብ መገናኛ መስመር

      5. ራእዩ በመጀመሪያ ለዮሐንስ ከዚያም ለጉባኤዎች የደረሰው እንዴት ነው?

      5 ራእይ 1:1ለ, 2 እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ። እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።” ስለዚህ ዮሐንስ በመንፈስ አነሳሽነት የተነገረውን መልእክት የተቀበለው መልእክተኛ ሆኖ በተላከ አንድ መልአክ አማካኝነት ነበረ። ከዚያም በመጽሐፍ ጥቅልል ጽፎ በዘመኑ ለነበሩት ጉባኤዎች አስተላለፈው። ይህን መጽሐፍ በዛሬው ጊዜ ለሚገኙት 100,000 ገደማ ለሚሆኑ የተባበሩ የአምላክ አገልጋዮች ጉባኤዎች ማበረታቻ እንዲሆን አምላክ ተጠብቆ እንዲቆይ በማድረጉ ልንደሰት ይገባናል።

      6. ኢየሱስ በዛሬው ዘመን ለባሮቹ መንፈሣዊ ምግብ የሚያቀርብበትን መስመር ለይቶ ያሳወቀው እንዴት ነው?

      6 አምላክ በዮሐንስ ዘመን የራእይን መልእክት ያስተላለፈበት መገናኛ መስመር ነበረው። ዮሐንስም የዚህ መስመር ምድራዊ ክፍል ነበር። ዛሬም ቢሆን አምላክ ‘ለባሪያዎቹ’ መንፈሣዊ ምግብ የሚሰጥበት መስመር አለው። ኢየሱስ ስለ ሥርዓቱ የፍፃሜ ዘመን በተናገረው ታላቅ ትንቢት ላይ የዚህ መስመር ምድራዊ ክፍል “ምግባቸውን በጊዜው እንዲሰጥ ጌታው በቤተሰዎቹ ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ” እንደሆነ ገልጾአል። (ማቴዎስ 24:3, 45-47) ይህንን የዮሐንስ ክፍል የትንቢቱን ትርጉም ለመፍታት አምላክ ይጠቀምበታል።

      7. (ሀ) በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ምልክቶች እንዴት ሊነኩን ይገባል? (ለ) ከዮሐንስ ክፍል አባሎች መካከል አንዳንዶቹ በራእይ ትንቢቶች ፍጻሜ ለምን ያህል ጊዜ ተካፍለዋል?

      7 ኢየሱስ ራእዩን ያሳየው ‘በምልክቶች’ ወይም በምሳሌዎች እንደሆነ ዮሐንስ ጽፎአል። ምልክቶቹ አስደናቂዎች ሲሆኑ ለመመርመርም የሚያጓጉ ናቸው። ታላላቅ ድርጊቶችን የሚያመለክቱ ስለሆኑ ትንቢቱንና ትርጉሙን ለሰዎች እንድናሳውቅ ሊቀሰቅሱንና ቅንዓታችንን ሊያነሳሱ ይገባል። የራእይ መጽሐፍ ልብን የሚመስጡ ብዙ ትዕይንቶችን ይገልጽልናል። በእነዚህ ትዕይንቶች በሙሉ ዮሐንስ በተመልካችነት ወይም በተሳታፊነት ተካፍሎአል። እነዚህን ራእዮች በመፈጸሙ ሥራ ለብዙ አሥርተ ዓመታት የተካፈሉት የዮሐንስ ክፍል አባሎች ለሌሎች ለማብራራት እንዲችሉ የአምላክ መንፈስ የራእዮቹን ትርጉም ስለፈታላቸው በጣም ተደስተዋል።

  • በቅርቡ መፈጸም ያለባቸው ነገሮች
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 9. (ሀ) የዮሐንስ ክፍል እንደ ዮሐንስ ያለ ምን ዝንባሌ አሳይቶአል? (ለ) ዮሐንስ ደስተኛ ለመሆን የምንችልበትን መንገድ ያመለከተን እንዴት ነው?

      9 አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጠውን መልእክት ዮሐንስ በታማኝነት መስክሮአል። ‘ያየውን ሁሉ’ በዝርዝር ገልጾአል። የዮሐንስ ክፍልም ትንቢቱን ሙሉ በሙሉ ለመረዳትና አስፈላጊዎቹን ነጥቦች ለአምላክ ሕዝቦች ለማሳወቅ እንዲችል የአምላክንና የኢየሱስ ክርስቶስን እርዳታና አመራር ከልብ ፈልጎአል። ዮሐንስ ለቅቡዓን ጉባኤዎች ጥቅም (አምላክ ከታላቁ መከራ በሕይወት ጠብቆ ለሚያሳልፋቸው ብሔራት አቀፍ እጅግ ብዙ ሰዎች ጭምር) የሚከተለውን ጽፎአል:- “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፣ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን [“ደስተኞች፣” NW] ናቸው።”—ራእይ 1:3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ