-
የይሖዋ ሥራዎች—ታላቅና ድንቅ ናቸውራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
14. ዮሐንስ ከመቅደሱ ሲወጡ የተመለከተው እነማንን ነው? ለእነርሱስ ምን ተሰጣቸው?
14 የእነዚህን ቅቡዓን ድል አድራጊዎች መዝሙር መስማታችን ተገቢ ነው። ለምን ቢባል የአምላክ ቁጣ በሞላባቸው ጽዋዎች ውስጥ የሚገኘውን ፍርድ በመላው ምድር ላይ አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ ዮሐንስ ቀጥሎ እንደሚገልጸው በእነዚህ ጽዋዎች መፍሰስ ሥራ የሚካፈሉት ሰዎች ብቻ አይደሉም። “ከዚህም በኋላ አየሁ፣ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፣ ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ። ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአብሔር ቁጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።”—ራእይ 15:5-7
-
-
የይሖዋ ሥራዎች—ታላቅና ድንቅ ናቸውራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
16. (ሀ) ሰባቱ መላእክት ለሥራቸው ሙሉ ብቃት ያላቸው መሆኑን የሚያሳየን ምንድን ነው? (ለ) ምሳሌያዊ ጽዋዎቹን በማፍሰስ ሥራ የሚካፈሉ ሌሎች ክፍሎችም እንዳሉ የሚያመለክተን ምንድን ነው?
16 እነዚህ መላእክት የተሰጣቸውን ሥራ ለመፈጸም ሙሉ ብቃት አላቸው። ብሩሕ የሆነ ንጹሕ ልብስ መልበሳቸው በይሖዋ ፊት መንፈሳዊ ንጽሕናና ቅድስና እንዳላቸው ያመለክታል። በተጨማሪም የወርቅ መታጠቂያ አድርገዋል። አንድ ሰው መታጠቂያ የሚያደርገው አንድ ዓይነት የሚሠራ ሥራ ሲኖረው ነው። (ዘሌዋውያን 8:7, 13፤ 1 ሳሙኤል 2:18፤ ሉቃስ 12:37፤ ዮሐንስ 13:4, 5) ስለዚህ መላእክቱ አንድ ዓይነት ሥራ ለመፈጸም ታጥቀዋል። ከዚህም በላይ ያደረጉት መታጠቂያ የወርቅ መታጠቂያ ነው። በጥንቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወርቅ መለኮታዊና ሰማያዊ ነገሮችን ያመለክት ነበር። (ዕብራውያን 9:4, 11, 12) ይህም ማለት እነዚህ መላእክት መሥራት የሚኖርባቸው ውድና መለኮታዊ ሥራ አላቸው ማለት ነው። በዚህ ታላቅ ሥራ የተሰማሩ ሌሎች ፍጥረታትም አሉ። ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት አንዱ ጽዋዎቹን ሰጣቸው። ይኸኛው ሕያው ፍጥረት የይሖዋን ፍርድ ለማወጅ የሚያስፈልገውን የድፍረትና የአይበገሬነት ባሕርይ የሚያመለክተውን አንበሳ የሚመስለው የመጀመሪያው ሕያው ፍጥረት ነው።—ራእይ 4:7
-