-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
16. (ሀ) የሕዝበ ክርስትና መሪዎች የተለየ ጥላቻ የሚያሳዩት ለእነማን ነው? (ለ) በመካከለኛው ዘመን በሕዝበ ክርስትና ውስጥ ምን ሆኖ ነበር? (ሐ) የፕሮቴስታንት ዓመፅ ወይም ተሐድሶ የሕዝበ ክርስትናን የክህደት መንገድ ለውጦት ነበርን?
16 የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊም ሆኑ ዓለማዊ መሪዎች የአምላክ መንጋ እረኞች ነን እያሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ለሚያበረታታ ወይም ከቅዱሳን ጽሑፎች የማይስማሙ ድርጊቶቻቸውን ለሚያጋልጥባቸው ማንኛውም ሰው ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው አሳይተዋል። ጆን ሁስና የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሆነው ዊልያም ታይንደል ከባድ ስደት ደርሶባቸው በሰማዕትነት ሞተዋል። ፍጹም በሆነ ጨለማ በተዋጠው የመካከለኛ ዘመን ዲያብሎሳዊው የካቶሊክ ኢንኩዚሽን ስለተጀመረ የክህደቱ አገዛዝ ጣሪያ ደርሶ ነበር። የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥልጣን ወይም ትምህርት የተቃወመ ማንኛውም ሰው ምህረት በሌለው ሁኔታ ይታፈን ነበር። መናፍቃን ናቸው የሚባሉ ሰዎች እየተሠቃዩ ይገደሉ ነበር ወይም በእንጨት ላይ ታስረው ይቃጠሉ ነበር። ሰይጣን በዚህ መንገድ የአምላክ ሴት መሰል ድርጅት አባል የሆነ ማንኛውም እውነተኛ ዘር ፈጥኖ እንዲጨፈለቅ የተቻለውን ሁሉ ያደርግ ነበር። የፕሮቴስታንቶች ዓመፅ ወይም ተሐድሶ ከተጀመረ በኋላም (ከ1517 ጀምሮ) ብዙዎቹ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ተመሳሳይ የጭቆና መንፈስ አሳይተዋል። እነርሱም ለአምላክና ለክርስቶስ ታማኝ ለመሆን የጣሩትን ሰዎች በሰማዕትነት በመግደል በራሳቸው ላይ የደም ዕዳ ከምረዋል። በእውነትም “የቅዱሳን ደም” በብዛት ፈስሶአል።—ራእይ 16:6፤ ከማቴዎስ 23:33-36 ጋር አወዳድር።
-
-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
[በገጽ 31 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖት መጽሐፍ ቅዱስን የተረጎሙትን፣ ያነበቡትን ወይም በእጃቸው የተገኘባቸውን በማሳደድና በመግደል ከባድ የደም ዕዳ ተሸክማለች
-