የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክ ቁጣ ወደ ፍጻሜ ደረሰ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. ሶስተኛው ጽዋ ሲፈስስ ምን ይሆናል? ከመልአኩና ከመሠዊያው ምን የሚሉ ቃላት ተሰምተዋል?

      6 ሦስተኛው የአምላክ ቁጣ ጽዋ እንደ ሦስተኛው የመለከት ድምፅ በውኃ ምንጮች ላይ ጉዳት የሚያስከትል ነው። “ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውኃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ። የውኃውም መልአክ:- ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ፣ ቅዱስ ሆይ፣ እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤ የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፣ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። ከመሠዊያውም:- አዎን፣ ሁሉን የምትገዛ ጌታ [“ይሖዋ፣” NW] አምላክ ሆይ፣ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”—ራእይ 16:4-7

  • የአምላክ ቁጣ ወደ ፍጻሜ ደረሰ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 10. “የውኃዎቹ መልአክ” ምን ነገር አሳውቆአል? መሰውያውስ ምን ተጨማሪ ምስክርነት ሰጠ?

      10 ይህን ጽዋ ወደ ውኃው የሚያፈስሰው “የውኃው መልአክ” ይሖዋ ጽንፈ ዓለማዊ ፈራጅና የጽድቅ ፍርዶቹ ፍጹም የሆኑ አምላክ መሆኑን አሳውቆአል። በዚህም ምክንያት ስለሰጠው ፍርድ ሲናገር “የሚገባቸው ነውና” ብሎአል። መልአኩ በዚህ ክፉ ዓለም ለብዙ ሺህ ዓመታት በሐሰት ትምህርቶችና ፍልስፍናዎች ምክንያት የተስፋፋውን ጭካኔና ደም መፋሰስ ተመልክቶ እንደነበረ አያጠራጥርም። ስለዚህ የይሖዋ የፍርድ ውሣኔ ትክክል መሆኑን ያውቅ ነበር። የአምላክ መሰዊያ እንኳን ይህ ትክክል መሆኑን ይናገራል። በ⁠ራእይ 6:9, 10 ላይ በሰማዕትነት የተገደሉት ሰዎች ነፍሳት በዚህ መሠዊያ ሥር እንዳሉ ተነግሮአል። ስለዚህ የይሖዋ ውሣኔ ፍትሐዊና ጽድቅ ስለመሆኑ መሰዊያው ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥቶአል።a በእርግጥም ይህን የሚያክል ብዙ ደም አለአግባብ የተጠቀሙና ያፈሰሱ ሰዎች ተገድደው ደም መጠጣታቸው ተገቢ ነው። ይህም ይሖዋ የሞት ፍርድ የፈረደባቸው መሆኑን ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ