-
“የሰላሙን መስፍን” አርማጌዶን ከፊቱ ይጠብቀዋል“የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
-
-
ብሔራት ወደ አርማጌዶን እየተሰበሰቡ ነው
15. (ሀ) እንግዲያው አርማጌዶን ምን ዓይነት ቦታ ነው? (ለ) ብሔራትን በአርማጌዶን ወደሚሆነው ጦርነት የሚያስከትታቸው ርኩስ ፕሮፓጋንዳ አንዱ ምንጩ ምንድን ነው?
15 ስለዚህ መጊዶ ወሳኝ ጦርነቶች የተካሄዱበት ቦታ ነበር። በዚህም መሠረት አርማጌዶንም በራእይ 16:13, 14 ላይ በተገለጹት ቀስቃሽ ኃይሎች ገፋፊነት በዛሬው ጊዜ የሚገኙት ሁሉም ዓለማዊ ብሔራት የሚሰለፉበት የጦር ሜዳ ይሆናል ቢባል ምክንያታዊ ነው። ብሔራትን ለጦር የሚያስከትቱት “በመንፈስ አነሳሽነት የሚነገሩት ቃላት” የሚያመለክቱት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተገለጸው ርኩስ ከሆነው ጓጉንቸር ጋር የሚመሳሰለውንና በአሁኑ ጊዜ እንደ ጓጉንቸር ድምፅ የሚነገረውን ርኩስ ፕሮፓጋንዳ ነው። እንደዚህ ላለው ርኩስ የሆነ ፕሮፓጋንዳ አንዱ ምንጭ ታላቁ ‘ቀይ ዘንዶ’ ነው። ራእይ 12:1–9 ይህ “ዘንዶ” ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሆነ አድርጎ ይገልጸዋል።
-
-
“የሰላሙን መስፍን” አርማጌዶን ከፊቱ ይጠብቀዋል“የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
-
-
17. ‘ከአውሬው’ የሚወጣው ጓጉንቸር መሰል ፕሮፓጋንዳ ውጤቱ ምንድን ነው?
17 እንደዚህ ያለው የዓለም የፖለቲካ ሥርዓት የራሱ የሆነ ልዩ ፕሮፓጋንዳ አለው። እንደ ጓጕንቸር ጩኸት የሚያስተጋባው ይህ ፕሮፓጋንዳ “ከዘንዶው አፍ” ከሚመጣው አጋንንታዊ ቃል ጋር ተዳምሮ “ነገሥታትን” ይኸውም የዓለምን የፖለቲካ ኃይሎች በአርማጌዶን ላይ ወደሚካሄደው “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ ወደሚደረገው ጦርነት” ለማስከተት ያገለግላል።
18. (ሀ) ሐርማጌዶን የሚለው ስም ምንን ያመለክታል? (ለ) ተራራ ምንን ሊያመለክት ይችላል?
18 እንግዲያው አርማጌዶን ወሳኝ የሆነ ጦርነት የሚከናወንበትን የዓለም ሁኔታ ያመለክታል። የፖለቲካ ገዥዎች በአንድ ላይ በመሆን የአምላክን ፈቃድ ወደ መቃወም የሚደርሱበትንና በዚህም ምክንያት አምላክ በዓላማው መሠረት መልሶ የማጥቃት ርምጃ የሚወስድበትን የዓለምን ጉዳዮች የመጨረሻ ከፍተኛ ሁኔታ ያመለክታል። ስለዚህም የወደፊቱ ሁኔታ የሚወሰነው ይህ ፍልሚያ በሚያስከትላቸው ውጤቶች ይሆናል። መጊዶ ይገኝበት በነበረው መልክዓ ምድራዊ ቦታው ላይ ምንም ተራራ አልነበረም። ይሁን እንጂ ተራራ በዚያ በሚሰበሰቡት በሁሉም ወታደራዊ ኃይሎች በቀላሉ ከሩቅ ሊታይ የሚችለውን አንድ ጐላ ያለ የመሰብሰቢያ ቦታ ሊያመለክት ይችላል።
19, 20. በአርማጌዶን የይሖዋ ሰማያዊ ኃይሎች የጦር አዛዥ የሚጠቀምበት የጦር ስልት ምን ይሆናል? ከምንስ ውጤት ጋር?
19 የይሖዋ ተዋጊ ኃይሎች ጦር አዛዥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለአያሌ ዓመታት የዓለም ገዥዎችና የተዋጊ ኃይሎቻቸው ወደ አርማጌዶን እየገሰገሱ በመሰብሰብ ላይ መሆናቸውን ተመልክቷል። ሆኖም እርሱ በነጠላ አንድን የተለየ ንጉሥና ወታደራዊ ኃይሎቹን ለይቶ አንድ በአንድ ለመምታትና በዚህም የጠላትን ኃይሎች በትንሽ በትንሹ ለመጨረስ አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ ግን በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡና የጦር ኃይላቸውን አስተባብረው የመጨረሻው ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል እንዲኖራቸው በቂ ጊዜ ፈቅዶላቸዋል። ድፍረት የተሞላበት ዓላማው ሁሉንም በአንድ ጊዜ ለመምታት ነው!
-