የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቲያናዊ መለያችን እንዳይጠፋ እንጠንቀቅ
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | የካቲት 15
    • 4. ኢየሱስ ማንነታችንን በግልጽ የሚያሳውቀው ክርስቲያናዊ መለያ እንዳይጠፋብን መጠንቀቃችን አስፈላጊ መሆኑን ያጎላው እንዴት ነው?

      4 ይሁን እንጂ ራሳችንን የወሰንን የይሖዋ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን ወጣትም ሆን አረጋዊ ሁላችንም ክርስቲያናዊ መለያችን እንዲበላሽ ከፈቀድን ከባድ ኪሳራ እንደሚደርስብን እናውቃለን። ስለ ክርስቲያናዊ መለያችን ያለን ትክክለኛ አመለካከት መመሥረት የሚገባው ይሖዋ ባወጣው መሥፈርትና እርሱ ለእኛ ባለው ፈቃድ ላይ ብቻ ነው። ደግሞም የተፈጠርነው በእርሱ መልክ ነው። (ዘፍጥረት 1:26፤ ሚክያስ 6:8) መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያናዊ መለያችንን ሰዎች ሁሉ በግልጽ ከሚያዩት ልብስ ጋር ያመሳስለዋል። ኢየሱስ ያለንበትን ዘመን በሚመለከት “እነሆ፤ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ዕራቊቱን እንዳይሆን ኀፍረቱም እንዳይታይ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው” በማለት አስጠንቅቋል።a (ራእይ 16:15) በልብስ የተመሰሉትን ክርስቲያናዊ ባሕርያችንንና የሥነ ምግባር መሥፈርቶቻችንን አውልቀን የሰይጣን ዓለም በራሱ መልክ እንዲቀርጸን አንፈልግም። እንደዚያ ከሆነ ግን ‘ልብሳችንን’ እናጣለን። እንዲህ ያለው ሁኔታ የኋላ ኋላ የሚያስቆጭና ለውርደት የሚዳርግ ነው።

  • ክርስቲያናዊ መለያችን እንዳይጠፋ እንጠንቀቅ
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | የካቲት 15
    • a እነዚህ ቃላት ኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ አለቃው ያሉበትን ኃላፊነቶች በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጠቁሙ ሊሆኑ ይችላሉ። አለቃው ሌሊት ላይ ቤተ መቅደሱ ውስጥ እየተዘዋወረ ሌዋውያን ጠባቂዎች በተመደቡበት ቦታ ነቅተው ይጠብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ ይመለከታል። አንድ ጠባቂ ተኝቶ ከተገኘ በበትር ይመታል፤ እንዲሁም እፍረት እንዲከናነብ ሲባል ልብሱ እንዲቃጠል ይደረግ ይሆናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ