የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቶስ ለጉባኤዎቹ የላከው መልእክት
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ግንቦት 15
    • 7, 8. በኤፌሶን የነበረው ጉባኤ ምን ከባድ ድክመት ነበረበት? እኛስ ተመሳሳይ ሁኔታ ቢያጋጥመን ምን ማድረግ እንችላለን?

      7 ይሁንና በኤፌሶን የነበሩት ክርስቲያኖች አንድ ከባድ ድክመት ነበረባቸው። ኢየሱስ “የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና” ብሏቸዋል። የጉባኤው አባላት ለይሖዋ የነበራቸውን የቀደመውን ፍቅራቸውን እንደገና ማቀጣጠል አስፈልጓቸዋል። (ማርቆስ 12:​28-30፤ ኤፌሶን 2:​4፤ 5:​1, 2) እኛም ብንሆን ለአምላክ የነበረን የቀድሞ ፍቅራችን እንዳይጠፋ መጠንቀቅ ይኖርብናል። (3 ዮሐንስ 3) ቁሳዊ ሃብት ወይም ተድላ የማሳደድ ምኞትን የመሳሰሉ ነገሮች በሕይወታችን ውስጥ ከፍተኛ ቦታ መያዝ ቢጀምሩስ? (1 ጢሞቴዎስ 4:​8፤ 6:​9, 10) ከሆነ እንዲህ ያሉትን ዝንባሌዎች አስወግደን ለይሖዋ ጥልቅ ፍቅር ለማዳበርና እርሱና ልጁ ላደረጉልን ነገሮች የአመስጋኝነት መንፈስ ለማሳየት የሚያስችለንን መለኮታዊ እርዳታ እንድናገኝ አጥብቀን መጸለይ ይኖርብናል።​—⁠1 ዮሐንስ 4:​10, 16

  • ክርስቶስ ለጉባኤዎቹ የላከው መልእክት
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ግንቦት 15
    • 11. ሌሎች ለይሖዋ ያላቸውን ፍቅር እንዲያሳድጉ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

      11 የኤፌሶን ክርስቲያኖች የቀድሞ ፍቅራቸውን አጥተው ነበር። ዛሬም በአንድ ጉባኤ ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ ቢፈጠርስ? የይሖዋ ፍቅር ስለተንጸባረቀባቸው መንገዶች በመናገር ሌሎች ለይሖዋ ያላቸውን ፍቅር እንዲያሳድጉ በግለሰብ ደረጃ አስተዋጽኦ ማበርከት ይቻላል። አምላክ በውድ ልጁ በኩል ቤዛዊ ዝግጅት በማድረግ ላሳየን ፍቅር አመስጋኝነታችንን መግለጽ እንችላለን። (ዮሐንስ 3:​16፤ ሮሜ 5:​8) በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ ስንሰጥና ክፍል ስናቀርብ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር የሚስማማ ከሆነ ስለ ይሖዋ ፍቅር መጥቀሳችን ተገቢ ነው። በክርስቲያናዊ አገልግሎት ስንካፈል የይሖዋን ስም በማወደስ ለእርሱ ያለንን ፍቅር እናሳያለን። (መዝሙር 145:​10-13) በእርግጥም አንድ ጉባኤ የቀድሞ ፍቅሩን መልሶ እንዲያቀጣጥል ወይም እንዲያጠናክር በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንችላለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ