-
ስመ ጥፉ በሆነችው አመንዝራ ላይ መፍረድራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
25. (ሀ) አስጸያፊ ነገር የሞላበት የወርቅ ጽዋ የምን ምሳሌ ነው? (ለ) ምሳሌያዊቱ ጋለሞታ ሰክራ የነበረው በምን መንገድ ነው?
25 አሁን ደግሞ ጋለሞታዋ በእጅዋ የያዘችውን እንመልከት። ዮሐንስ ይህን ሲመለከት በድንጋጤ አፉን ሳይከፍት አይቀርም። “በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኩሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ” ይዛ ነበር። ይህ ጽዋ አሕዛብን ሁሉ ያሰከረችበትን ‘የዝሙትዋን የወይን ጠጅ’ የያዘ ነበር። (ራእይ 14:8፤ 17:4) ጽዋው ከውጩ ያማረና ውድ ይመስላል፣ በውስጡ የያዘው ግን የሚያስጸይፍና እርኩስ ነገር ነው። (ከማቴዎስ 23:25, 26 ጋር አወዳድር።) ታላቋ ጋለሞታ ብሔራትን ለማሳትና በቁጥጥርዋ ሥር ለማስገባት የተጠቀመችባቸውን ውሸቶችና የቆሸሹ ድርጊቶች በሙሉ ይዞአል። ከዚህ በላይ የሚዘገንነውና የሚያስጸይፈው ደግሞ ጋለሞታይቱ ራስዋ በአምላክ አገልጋዮች ደም ሰክራ መታየትዋ ነው። እንዲያውም ወደፊት እንደምናነበው “በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም” ተገኝቶባታል። (ራእይ 18:24) በጣም ከባድ የሆነ የደም ዕዳ አለባት።
26. ታላቂቱ ባቢሎን የደም ዕዳ እንዳለባት የሚያረጋግጥ ምን ማስረጃ አለ?
26 ባለፉት መቶ ዘመናት ሁሉ የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ብዙ የደም ጎርፍ አፍስሳለች። ለምሳሌ ያህል “የቡድሃን ቅዱስ ስም” የሚጠሩ ጦረኛ መነኮሳት በመካከለኛው ዘመን በጃፓን አገር በኪዮቶ የሚገኙ ቤተ መቅደሶችን የጦርነት ምሽጎች በማድረግ እርስ በርሳቸው ተገዳድለዋል። በጣም ብዙ ደም በመፍሰሱ ምክንያት መንገዶች ቀለማቸው ተለውጦ ቀይ ሆነው ነበር። በ20ኛው መቶ ዘመን የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ከየአገሮቻቸው ጦር ሠራዊቶች ጋር ተሰልፈው እርስ በርስ ተራርደዋል። በዚህም ምክንያት እጅግ ቢያንስ አንድ መቶ ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎቸ ሞተዋል። በጥቅምት ወር 1987 የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ኒክሰን እንዲህ ብለው ነበር:- “በታሪክ ዘመናት ሁሉ ከፍተኛ ደም የፈሰሰው በዚህ በ20ኛው መቶ ዘመን ነው። ይህ መቶ ዘመን ከመጀመሩ በፊት በተደረጉት ጦርነቶች ከሞቱት ሰዎች ቁጥሩ በጣም ብዙ የሆነ ሕዝብ በዚህች መቶ ዘመን በተደረጉ ጦርነቶች ተገድለዋል።” የዓለም ሃይማኖቶች በዚህ ሁሉ ደም መፋሰስ በመካፈላቸው አምላክ ይፈርድባቸዋል። ይሖዋ “ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆችን” ይጠላል። (ምሳሌ 6:16, 17) ከዚህ ቀደም ሲል ዮሐንስ ከመሠዊያው ሥር “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” የሚለውን ጩኸት ሰምቶ ነበር። (ራእይ 6:10) ይህ ጥያቄ የሚመለስበት ጊዜ ሲደርስ የጋለሞታዎችና የምድር እርኩሰት ሁሉ እናት የሆነችው ታላቂቱ ባቢሎን የሚገባትን ብድራት ትቀበላለች።
-
-
አንድ አስገራሚ ምሥጢር ተፈታራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
1. (ሀ) ዮሐንስ ታላቂቱን ጋለሞታና የተቀመጠችበትን አስፈሪ አውሬ በተመለከተ ጊዜ ምን ተሰማው? ለምንስ? (ለ) የዮሐንስ ክፍል የትንቢታዊው ራእይ ፍጻሜ የሆኑ ነገሮች መፈጸማቸውን ሲመለከት ምን ተሰማው?
ዮሐንስ ታላቂቱን ጋለሞታና የተቀመጠችበትን ግዙፍ አውሬ ሲመለከት ምን ተሰማው? ዮሐንስ ራሱ ይነግረናል:- “ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ” (ራእይ 17:6ለ) ተራ የሆነ የሰው አእምሮ እንዲህ ያለውን ትዕይንት ከራሱ ግምት ሊያፈልቅ አይችልም። በአንድ ምድረ በዳ ውስጥ በስካር የደነዘዘች አመንዝራ ሴት በሚያስጠላ ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣለች። (ራእይ 17:3) የዮሐንስ ክፍልም እንዲሁ የትንቢታዊውን ራእይ ፍጻሜ ሲመለከት እጅግ ይደነቃል። የዓለም ሰዎች ይህን ሊያዩ ቢችሉ ኖሮ በጣም ተደንቀው ‘የማይታመን ነገር ነው!’ ይሉ ነበር። የዓለም ገዥዎችም ‘የማይታሰብ ነገር ነው!’ በማለት አድናቆታቸውን ያስተጋቡ ነበር። ይሁን እንጂ ራእዩ በዘመናችን በአስገራሚ ሁኔታ እውነት ሆኖአል። የአምላክ ሕዝቦች በራእዩ አፈጻጸም ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። ይህም ራእዩ ወደ ከፍተኛ ፍጻሜው እንደሚደርስ ማረጋገጫ ይሆንላቸዋል።
-