-
ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ ሁንለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ሉቃስ 4:8ን እና ራእይ 18:4, 5ን አንብቡ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ስሜ አሁንም በሐሰት ሃይማኖት አባላት ስም ዝርዝር ውስጥ ይገኛል?
ከሌላ ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያለው ድርጅት አባል ነኝ?
የምሠራው ሥራ በሆነ መንገድ ለሐሰት ሃይማኖት ድጋፍ የሚሰጥ ነው?
በሕይወቴ ውስጥ ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ሊያነካኩኝ የሚችሉ ሌሎች አቅጣጫዎች ይኖሩ ይሆን?
ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል ለአንዱም እንኳ ‘አዎ’ የሚል መልስ ከሰጠሁ ምን ለውጥ ማድረግ ይኖርብኛል?
በማንኛውም ሁኔታ ሥር ሕሊናህን የማይረብሽና ለይሖዋ ያለህን ታማኝነት የሚያሳይ ውሳኔ አድርግ።
አንድ ሃይማኖት ለሚያከናውነው የበጎ አድራጎት ሥራ ገንዘብ እንድታዋጣ ብትጠየቅ ምን ታደርጋለህ?
አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ለእውነት ጥብቅና መቆም እንድችል ከሃዲዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ምን እንደሚሉ ማወቅ አለብኝ።”
-