የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ታላቂቱ ከተማ ድምጥማጥዋ ጠፋ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 22. (ሀ) ከሰማይ የመጣው ድምፅ ምን አለ? (ለ) የአምላክ ሕዝቦች በ537 ከዘአበ እና በ1919 እዘአ በጣም ያስደሰታቸው ሁኔታ ያጋጠማቸው እንዴት ነው?

      22 ዮሐንስ ቀጥሎ የሚናገረው ቃል በጥንትዋ ባቢሎን ላይ ከተፈጸመው ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ትንቢታዊ ቃል ነው። “ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል:- ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ።” (ራእይ 18:4) በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ከሚገኙት ስለ ጥንትዋ ባቢሎን አወዳደቅ ከሚናገሩት ትንቢቶች መካከል ይሖዋ ለሕዝቦቹ “ከባቢሎን መካከል ሽሹ” ሲል የሰጠው ትዕዛዝ ይገኝበታል። (ኤርምያስ 50:8, 13) ዛሬም በተመሳሳይ በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ታላቅ ጥፋት ስለሚመጣ የአምላክ ሕዝቦች ከመካከልዋ እንዲወጡ ተመክረዋል። በ537 ከዘአበ ታማኞቹ እስራኤላውያን ከባቢሎን ለመውጣት መቻላቸው ትልቅ ደስታ አስገኝቶላቸው ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ የአምላክ ሕዝቦች በ1919 ከባቢሎናዊ ምርኮ ለመውጣት መቻላቸው ብዙ ደስታ አስገኝቶላቸዋል። (ራእይ 11:11, 12) ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎች ሽሹ የሚለውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል።

  • ታላቂቱ ከተማ ድምጥማጥዋ ጠፋ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 24. (ሀ) የአምላክ ሕዝቦች ከታላቂቱ ባቢሎን መሸሽ የሚኖርባቸው ከምን ለመዳን ነው? (ለ) ከታላቂቱ ባቢሎን ሳይሸሹ የቀሩ ሁሉ በምን ኃጢአት ተካፋዮች ይሆናሉ?

      24 በጣም ከባድ ቃላት ናቸው! ስለዚህ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ኤርምያስ በዘመኑ የነበሩ እስራኤላውያን እርምጃ እንዲወስዱ ሲያሳስብ እንደሚከተለው ብሎ ነበር:- “ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ። . . . የእግዚአብሔር [“የይሖዋ፣” NW] በቀል ጊዜ ነውና። እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና። ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከልዋ ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር [“ከይሖዋ፣” NW] ጽኑ ቁጣ ራሳችሁን አድኑ።” (ኤርምያስ 51:6, 45) ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ ከሰማይ የመጣው ድምፅ የአምላክ ሕዝቦች ከመቅሰፍትዋ እንዳይቀበሉ ከታላቂቱ ባቢሎን ሸሽተው መውጣት እንደሚኖርባቸው ያስጠነቅቃል። ይሖዋ በዚህ ዓለም ላይ፣ በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ጭምር የሚያወርደው መቅሰፍት መሰል ፍርድ በአሁኑ ጊዜ በመታወጅ ላይ ነው። (ራእይ 8:1 እስከ 9:21፤ 16:1-21) የአምላክ ሕዝቦች በሐሰት ሃይማኖት ላይ የሚደርሰው መቅሰፍት እንዳይደርስባቸውና ከታላቂቱ ባቢሎን ጋር እንዳይሞቱ ከፈለጉ ራሳቸውን ከሐሰት ሃይማኖት መለየት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በላይ በዚህች ድርጅት ውስጥ መቆየታቸው በኃጢአትዋ ተካፋዮች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ልክ እንደርስዋ በመንፈሳዊ ምንዝርና “በምድር የታረዱ ሁሉ ደም” ተጠያቂዎች ያደርጋቸዋል።—ራእይ 18:24፤ ከ⁠ኤፌሶን 5:11⁠ና ከ⁠1 ጢሞቴዎስ 5:22 ጋር አወዳድር።

      25. የአምላክ ሕዝቦች ከጥንትዋ ባቢሎን የወጡት እንዴት ነበር?

      25 ይሁን እንጂ የአምላክ ሕዝቦች ከታላቂቱ ባቢሎን የሚወጡት እንዴት ነው? በጥንትዋ ባቢሎን የነበሩት አይሁዶች ከባቢሎን ከተማ ወጥተው እስከ ተስፋይቱ ምድር ድረስ የእግር ጉዞ ማድረግ ነበረባቸው። ይሁን እንጂ ከጉዞው የበለጠ ነገር ያስፈልግ ነበር። ኢሳይያስ ለእስራኤላውያን በትንቢታዊ አነጋገር እንዲህ ብሎ ነበር:- “እናንተ የእግዚአብሔር [“የይሖዋ፣” NW] ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፣ እልፍ በሉ፣ እልፍ በሉ፣ ከዚያ ውጡ፣ ርኩስን ነገር አትንኩ። ከመካከልዋ ውጡ፣ ንጹሐን ሁኑ።” (ኢሳይያስ 52:11) አዎ፣ ለይሖዋ የሚያቀርቡትን አምልኮ ሊያረክሱባቸው የሚችሉትን ርኩስ የባቢሎን ሃይማኖት ልማዶች መተው ነበረባቸው።

      26. የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ‘ከመካከልዋ ውጡ፣ እርኩስንም አትንኩ’ የሚለውን ቃል የታዘዙት እንዴት ነው?

      26 ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ እንደሚከተለው በማለት የኢሳይያስን ቃል ጠቅሶ ነበር:- “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ። ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? . . . ስለዚህም ጌታ [“ይሖዋ፣” NW]:- ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፣ ርኩስንም አትንኩ ይላል።” የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ይህንን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከቆሮንቶስ ከተማ መውጣት አላስፈለጋቸውም ነበር። ይሁን እንጂ ከሐሰት ሃይማኖት የረከሱ ቤተ መቅደሶች መራቅና እነዚያ የጥንት ጣዖት አምላኪዎች ይፈጽሙ ከነበረው እርኩስ ተግባራት ራሳቸውን መለየት ነበረባቸው። ንጹሕ ሕዝቦች ሆነው ይሖዋን ሊያገለግሉ የሚችሉት ይህን ቢያደርጉ ብቻ ነው።—2 ቆሮንቶስ 6:14-17፤ 1 ዮሐንስ 3:3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ