-
‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሐምሌ 15
-
-
16, 17. የበጉ ሠርግ በሰማይ ከመከናወኑ በፊት ምን መፈጸም አለበት?
16 ሁሉም የ144,000 አባላት በሰማይ ከተሰበሰቡ በኋላ ለበጉ ሠርግ የመጨረሻው ዝግጅት መጀመር ይችላል። (ራእይ 19:9) ይህ አስደሳች ሥነ ሥርዓት ከመካሄዱ በፊት ግን አንድ ሌላ ነገር ይፈጸማል። ቀሪዎቹ የ144,000 አባላት ወደ ሰማይ ከመወሰዳቸው ትንሽ ቀደም ብሎ ጎግ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝር አስታውስ። (ሕዝ. 38:16) ታዲያ ይህ ጥቃት ምን ያስከትላል? በምድር ላይ ያሉት የአምላክ ሕዝቦች ለጥቃት የተጋለጡ ይመስላሉ። እነዚህ የአምላክ ሕዝቦች በንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የተሰጠውን መመሪያ ይታዘዛሉ፦ “እናንተ ይህን ጦርነት መዋጋት አያስፈልጋችሁም። ቦታ ቦታችሁን ይዛችሁ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚወስደውን የማዳን እርምጃ ተመልከቱ። ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።” (2 ዜና 20:17) በሰማይ ግን ሁኔታው ከዚህ የተለየ ነው። ራእይ 17:14 ቅቡዓን በሙሉ ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ የአምላክ ሕዝቦች ጠላቶች ስለሚያደርጉት ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ከበጉ ጋር ይዋጋሉ፤ ሆኖም በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ ድል ይነሳቸዋል። ከእሱ ጋር ያሉት የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ድል ያደርጋሉ።” ኢየሱስ በሰማይ ካሉት 144,000 ተባባሪ ገዢዎቹ ጋር በመሆን በምድር ላይ ያሉትን የአምላክ ሕዝቦች ይታደጋል።
17 ይህን ተከትሎ የሚነሳው የአርማጌዶን ጦርነት የይሖዋ ቅዱስ ስም እንዲከበር ያደርጋል። (ራእይ 16:16) በፍየል የተመሰሉት ሰዎች በሙሉ በዚያ ወቅት “ወደ ዘላለም ጥፋት” ይሄዳሉ። በመጨረሻም ማንኛውም ዓይነት ክፋት ከምድር ላይ ይወገዳል፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም የታላቁን መከራ የመጨረሻ ምዕራፍ በሕይወት ያልፋሉ። ዝግጅቱ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ በራእይ መጽሐፍ መደምደሚያ ላይ እንደተገለጸው የበጉ ሠርግ ይከናወናል። (ራእይ 21:1-4)d ከጥፋቱ ተርፈው በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ የአምላክን ሞገስ የሚያገኙ ከመሆኑም ሌላ የእሱን ፍቅር የሚያሳዩ የተትረፈረፉ በረከቶችን ያጣጥማሉ። ይህ እንዴት ያለ አስደሳች ሠርግ ይሆናል! በእርግጥም በታላቅ ጉጉት የምንጠባበቀው ቀን አይደለም?—2 ጴጥሮስ 3:13ን አንብብ።
-