-
ተዋጊው ንጉሥ አርማጌዶን ላይ ድል ይቀዳጃልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
22. ዮሐንስ የመጨረሻውን ጦርነት ሂደት አጠቃልሎ የገለጸው እንዴት ነው?
22 ዮሐንስ የጦርነቱን የመጨረሻ ሂደት ሲያጠቃልል እንዲህ ይላል:- “በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ። አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ። የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፣ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።”—ራእይ 19:19-21
-
-
ተዋጊው ንጉሥ አርማጌዶን ላይ ድል ይቀዳጃልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
24. (ሀ) በአውሬውና በሐሰተኛው ነቢይ ላይ የሚፈጸመው የትኛው ፍርድ ነው? “በሕይወት ሳሉ” የተባለውስ እንዴት ነው? (ለ) የእሳቱ ባሕር ምሳሌያዊ ባሕር መሆን የሚኖርበት ለምንድን ነው?
24 የሰይጣንን ፖለቲካዊ ድርጅት የሚያመለክተው ከባሕር የወጣ ባለ ሰባት ራስና ባለ አሥር ቀንድ አውሬ ዳግመኛ ሊታይ በማይችልበት ሁኔታ ይጠፋል። ከእርሱም ጋር ሐሰተኛው ነቢይ ማለትም ሰባተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት አብሮት ይጠፋል። (ራእይ 13:1, 11-13፤ 16:13) “በሕይወት ሳሉ” ወይም አንድ ሆነው የአምላክን ሕዝቦች ተቃውመው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ “ወደ እሳት ባሕር” ይጣላሉ። ይሁን እንጂ ይህ ቃል በቃል የእሳት ባሕር ነውን? አውሬውም ሆነ ሐሰተኛው ነቢይ ቃል በቃል አራዊት እንዳልሆኑ ሁሉ የእሳቱም ባሕር ቃል በቃል የእሳት ባሕር አይደለም። ሙሉ በሙሉ ለመጨረሻ ጊዜ መጥፋትን፣ መመለሻ የሌለበትን ሥፍራ ያመለክታል። በኋላም ሞትና ሔድስ እንዲሁም ዲያብሎስ የሚወረወሩት ወደዚህ ሥፍራ ነው። (ራእይ 20:10, 14) ክፉዎች የዘላለም ሥቃይ የሚቀበሉበት ገሃነመ እሳት እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ምክንያቱም እንዲህ ያለ ሥፍራ መኖሩን እንኳን ይሖዋ ይጸየፈዋል።—ኤርምያስ 19:5፤ 32:35፤ 1 ዮሐንስ 4:8, 16
-