-
የእባቡን ጭንቅላት መቀጥቀጥራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
3. ዮሐንስ ሰይጣን ምን እንደሚደረግ ይነግረናል?
3 ይሁን እንጂ ለሰይጣንና ለዘሮቹ የተጠበቀላቸው ነገር ምንድን ነው? ዮሐንስ እንደሚከተለው በማለት ይነግረናል:- “የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው። ሺህ ዓመትም አሰረው፣ ወደ ጥልቅም ጣለው አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።”—ራእይ 20:1-3
-
-
የእባቡን ጭንቅላት መቀጥቀጥራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
5. የጥልቁ መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስን ምን ያደርገዋል? ለምንስ?
5 ታላቁ ቀይ ዘንዶ ከሰማይ በተጣለ ጊዜ “ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ” ተብሎ ተጠርቶ ነበር። (ራእይ 12:3, 9) አሁን ደግሞ ተይዞ ወደ ጥልቁ የሚጣልበት በደረሰበት በዚህ ጊዜ ‘የቀደመው እባብ ዘንዶው፣ እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን’ በመባል ምንነቱ ሙሉ በሙሉ ተገልጾአል። ይህ ስመ ጥፉ የሆነ መዋጥን የሚወድ፣ አሳች፣ ስም አጥፊና ተቃዋሚ በሰንሰለት ታሥሮ በተዘጋውና በታሸገው ‘ጥልቅ ውስጥ’ ይጣላል። ይህም የሆነው ‘ከእንግዲህ ወዲህ አሕዛብን እንዳያስት’ ነው። ሰይጣን በጥልቁ ውስጥ ታስሮ በሚቆይበት በዚህ የሺህ ዓመት ጊዜ በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደተጣለ እሥረኛ በሰው ልጆች ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖረውም። የጥልቁ መልአክ ሰይጣንን ከጽድቅ መንግሥቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖረው ሙሉ በሙሉ ያገልለዋል። ለሰው ልጆች ታላቅ እፎይታ ይሆናል።
-
-
የእባቡን ጭንቅላት መቀጥቀጥራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
7. (ሀ) ሰይጣንና አጋንንቱ በጥልቁ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ እንዴት ባለ ሁኔታ ይኖራሉ? ይህንንስ እንዴት እናውቃለን? (ለ) ሔድስና ጥልቁ አንድ ናቸውን? (የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።)
7 ሰይጣንና አጋንንቱ በጥልቁ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ሊንቀሳቀሱና ሊሠሩ ይችላሉን? “አስቀድሞ ነበረ፣ አሁንም የለም፣ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው” የተባለለትን ባለ ሰባት ራስ ቀይ አውሬ እናስታውስ። (ራእይ 17:8) በጥልቁ ውስጥ በነበረበት ጊዜ “አሁንም የለም” ተብሎ ነበር። ከሞተ አስከሬን ባልተሻለ ሁኔታ የማይንቀሳቀስና ምንም ነገር ሊሠራ የማይችል ሆኖ ነበር። በተመሳሳይም ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል። ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው” ብሎአል። (ሮሜ 10:7) ኢየሱስ በዚያ ጥልቅ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በድን ነበር።a እንግዲያው ሰይጣንና አጋንንቱ በጥልቁ ውስጥ በሚቆዩበት የሺህ ዓመት ጊዜ ከሞት ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ከምንም ሥራና እንቅስቃሴ ታግደው ይኖራሉ ማለት ነው። ይህ ለጽድቅ ወዳዶች ሁሉ ትልቅ የምሥራች ነው።
-