-
የክርስቶስ ቤዛ የአምላክ የመዳን መንገድመጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 15
-
-
እንዴት ነው? ኢየሱስ ከመያዙ ጥቂት ቀደም ብሎ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል” በማለት ተናግሮ ነበር። (ዮሐንስ 14:23) የኢየሱስ ‘ቃል’ “ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ . . . ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” የሚለውን ተልእኮ ከዳር ለማድረስ በቅንዓት መካፈልን ያካትታል። (ማቴዎስ 28:19) በተጨማሪም ለኢየሱስ ታዛዥ መሆን ለመንፈሳዊ ወንድሞቻችን ፍቅር ማሳየትን ይጠይቃል።—ዮሐንስ 13:34, 35
21. ሚያዝያ 1 በሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ላይ መገኘት ያለብን ለምንድን ነው?
21 ለቤዛው ያለንን አድናቆት የምናሳይበት አንድ ጥሩ መንገድ በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ላይ መገኘት ሲሆን በዚህ ዓመት በዓሉ ሚያዝያ 1 ላይ ይከበራል።a ኢየሱስ በዓሉን ባቋቋመ ጊዜ ተከታዮቹን “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” በማለት አዝዟቸው ስለነበር ይህም ትእዛዝ በኢየሱስ ‘ቃል’ ውስጥ የሚካተት ነው። (ሉቃስ 22:19) በዚህ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ክንውን ላይ በመገኘትና ክርስቶስ ያዘዘውን ሁሉ በጥሞና በመከተል የኢየሱስ ቤዛ የአምላክ የሕይወት መንገድ መሆኑን ከልብ እንደምናምን እናሳያለን። በእርግጥም “መዳንም በሌላ በማንም የለም።”—ሥራ 4:12
-
-
የፍቅር መንገድ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልመጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 15
-
-
የፍቅር መንገድ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል
“የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።”—1 ቆሮንቶስ 12:31
1-3. (ሀ) ፍቅር ማሳየትን መማር አዲስ ቋንቋ ከመማር ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? (ለ) ፍቅር ማሳየትን መማር ፈታኝ የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
አንድ አዲስ ቋንቋ ለመማር ሞክረህ ታውቃለህ? አስቸጋሪ መሆኑ አሌ አይባልም! እርግጥ አንድ ትንሽ ልጅ በቋንቋው ከሚጠቀሙ ሰዎች ጋር አብሮ በመኖር ብቻ አንድን ቋንቋ መማር ይችላል። አንጎሉ የቃላቱን ድምፆችና ትርጉማቸውን ቀስ በቀስ እየቀሰመ ብዙም ሳይቆይ ራሱን በሚገባ፣ ምናልባትም በተቀላጠፈ መንገድ የመግለጽ ችሎታ ያዳብራል። ለአዋቂዎች ግን ሁኔታው የተለየ ነው። የአንድን ባዕድ ቋንቋ መሠረታዊ የሆኑ ጥቂት ሐረጎች ለማወቅ ስንል ብቻ እንኳ ቋንቋውን የሚፈታ መዝገበ ቃላት በተደጋጋሚ እንመለከታለን። በቂ ልምምድ ካደረግን በኋላ በአዲሱ ቋንቋ ማሰብ እንጀምራለን፤ ቋንቋውን መናገሩም ቀላል ይሆንልናል።
2 ለሌሎች ፍቅር ማሳየትን መማር አንድን አዲስ ቋንቋ ከመማር ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። እርግጥ ሰዎች በተፈጥሯቸው ይህ መለኮታዊ ባሕርይ በተወሰነ መጠን አላቸው። (ዘፍጥረት 1:27፤ ከ1 ዮሐንስ 4:8 ጋር አወዳድር።) ይሁንና፣ በተለይ ተፈጥሯዊ ፍቅር በተመናመነበት በዚህ ዘመን ፍቅር ማሳየትን መማር ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) አንዳንድ ጊዜ ይህ ሁኔታ በቤተሰብ መካከል ይከሰታል። አዎን፣ ብዙዎች የሚያድጉት ፍቅራዊ ቃላት እምብዛም ወይም ጭራሽ በማይሰሙበትና ሸካራ ንግግር በነገሠበት ቤተሰብ ውስጥ ነው። (ኤፌሶን 4:29-31፤ 6:4) እኛ ራሳችን በሕይወታችን ውስጥ ፍቅርን ለማጣጣም እምብዛም አጋጣሚ ያላገኘን ብንሆንም እንኳ ለሌሎች ፍቅር ማሳየትን መማር የምንችለው እንዴት ነው?
3 በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል። ጳውሎስ
-