የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ትዳራችሁ የሰመረ እንዲሆን ይረዳል
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መስከረም 15
    • መጽሐፍ ቅዱስ ትዳራችሁ የሰመረ እንዲሆን ይረዳል

      ትዳር የሚለው ቃል ለአንዳንዶች ደስ የሚል ስሜት በውስጣቸው ይፈጥርባቸዋል። ሌሎች ግን ገና ቃሉን ሲሰሙ ያንገሸግሻቸዋል። አንዲት ሚስት እንዲህ በማለት ምሬቷን ገልጻለች:- “በአካል አብረን ብንኖርም በመንፈስ ግን የተፋታን ይመስለኛል። ችላ እንደተባልኩና ብቻዬን እንደተተውኩ ሆኖ ይሰማኛል።”

      በአንድ ወቅት ለመዋደድና አንዳቸው ሌላውን ለመንከባከብ ቃል የተጋቡ ሰዎች እንዲህ እንዲራራቁ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? አንደኛው ምክንያት ትዳር ስለሚያስከትለው ኃላፊነት ቀድሞውኑ ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ ነው። አንድ የሕክምና መጽሔት አዘጋጅ “ወደ ትዳር ዓለም የምንገባው ምንም እውቀቱ ሳይኖረን ነው” በማለት ተናግረዋል።

      በዩናይትድ ስቴትስ፣ ኒው ጀርሲ ግዛት በረትገርስ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት ብሔራዊ የጋብቻ ፕሮጀክት ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በዛሬው ጊዜ ስለ ትዳር በቂ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። የፕሮጀክቱ ኃላፊ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “ጥናቱ ከተደረገባቸው መካከል ብዙዎቹ በተፋቱ ወይም ደስታ የራቀው ትዳር ባላቸው ወላጆች ያደጉ ናቸው። ያልሰመረ ትዳር ምን እንደሚመስል ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስኬታማ የሆነ ትዳር ምን ሊመስል እንደሚችል ግን በእርግጠኝነት መናገር አይችሉም። እንዲያውም አንዳንዶቹ የሰመረ ትዳር ምን ይመስላል ቢባሉ ‘እንደወላጆቼ ትዳር ያልሆነ’ ከማለት ሌላ ብዙም የሚሉት የላቸውም።”

      ክርስቲያኖች በትዳራቸው ውስጥ ችግር አያጋጥማቸውም ሊባል ይቻላል? በፍጹም። እንዲያውም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች “መፋታትን አትሻ” የሚል ቀጥተኛ ምክር ተሰጥቷቸው ነበር። (1 ቆሮንቶስ 7:27) ፍጹም ባልሆኑ ሰዎች የተመሠረተ ትዳር ሳንካ ሊገጥመው እንደሚችል የታወቀ ነው። የትዳር ጓደኛሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የጋብቻ ሰንሰለታቸውን ማጠናከር ይችላሉ።

      መጽሐፍ ቅዱስ የጋብቻ መመሪያ መጽሐፍ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ቢሆንም የጋብቻን ዝግጅት ያቋቋመው አምላክ በመንፈሱ አነሳሽነት ያስጻፈው በመሆኑ በውስጡ የሚገኙት መመሪያዎች ትዳርን የሰመረ ለማድረግ ይረዳሉ ብለን በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። ይሖዋ አምላክ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል እንዲህ በማለት ተናግሯል:- “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።”—ኢሳይያስ 48:17, 18

      በአንተና በትዳር ጓደኛህ መካከል የነበረው ፍቅር እየቀዘቀዘ እንደመጣ ተሰምቶሃል? ፍቅር በጠፋበት የትዳር ሕይወት እንደታሰርክ ይሰማሃል? በትዳር ዓለም 26 ዓመታት ያሳለፈች አንዲት ሚስት እንዲህ ብላለች:- “እንዲህ ያለው የትዳር ሕይወት የሚያስከትለውን የስሜት ስቃይ በቃላት መግለጽ ያስቸግራል። ስቃዩ እፎይታ የሌለው ከመሆኑም በላይ ውስጥ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ነው።” ሊሻሻል አይችልም ብለህ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ለምን በትዳርህ ላይ ሕይወት ለመዝራት ቆርጠህ አትነሳም? የሚቀጥለው ርዕስ ባልና ሚስት ትዳራቸውን የሰመረ በማድረግ ረገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መመሪያ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል እንመለከታለን።

  • የጋብቻን ሰንሰለት ማጠናከር የሚቻለው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መስከረም 15
    • የጋብቻን ሰንሰለት ማጠናከር የሚቻለው እንዴት ነው?

      ለረጅም ጊዜ እድሳት ሳይደረግለት በመቅረቱ በጣም ያረጀ ቤት በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት። ቀለሙ ተላልጧል፤ ጣሪያው ተበሳስቷል እንዲሁም ግቢውን ሣርና ሙጃ ወርሶታል። ቤቱ ለብዙ ዓመታት ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቁበት እንደቆየና ምንም እድሳት እንዳልተደረገለት ያስታውቃል። ይህንን ቤት ከናካቴው ማፍረስ ይሻላል ወይስ ማደስ? መሠረቱ ጠንካራ ከሆነና መዋቅሩም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ከሆነ የግድ መፍረስ አያስፈልገውም። እድሳት ተደርጎለት ወደ መጀመሪያ ይዞታው ሊመለስ ይችላል።

      የዚህ ቤት ሁኔታ ስለ ትዳርህ አስታውሶህ ይሆን? ለበርካታ ዓመታት የተለያዩ ዓይነት ከባድ ችግሮች በትዳርህ ላይ ተፈራርቀውበት ሊሆን ይችላል። ከሁለት አንዳችሁ ወይም ሁለታችሁም ትዳራችሁን በተወሰነ መጠን ቸል ብላችሁ ሊሆን ይችላል። አንተም ለ15 ዓመታት በትዳር ዓለም እንደቆየችው እንደ ሳንዲ ይሰማህ ይሆናል። እንዲህ ብላለች:- “እኔና ባለቤቴን ያስተሳሰረን ባልና ሚስት የሚለው መጠሪያ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ብቻውን በቂ አልነበረም።”

      ያንተም ትዳር እዚህ ደረጃ ላይ ቢደርስ እንኳን መፍትሔው ፍቺ ነው ብለህ ለመደምደም አትቸኩል። የጋብቻህን ሰንሰለት ማጠናከር ትችላለህ። ይህ በአብዛኛው የተመካው አንተም ሆንክ የትዳር ጓደኛህ ቃል ኪዳናችሁን ለመጠበቅ ባላችሁ ቁርጠኝነት ላይ ነው። ቃል ኪዳንህን ለማክበር ያለህ ቁርጠኝነት ችግሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜም እንኳን ትዳርህን ከመፍረስ ሊጠብቀው ይችላል። ይሁን እንጂ ቃል ኪዳንን ለማክበር ቁርጠኛ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው?

      ቃል ኪዳን ግዴታ ያስከትላል

      አንድ መዝገበ ቃላት በሰጠው ፍቺ መሠረት ቃል ኪዳን “ግዴታ ወይም ኃላፊነት ውስጥ መግባት” ተብሏል። አንዳንድ ጊዜ ቃሉ ከጋብቻ ውጪ እንደ ንግድ ስምምነት ላሉ ሌሎች ግንኙነቶችም ይሠራል። ለምሳሌ ያህል አንድ የሕንጻ ተቋራጭ አንድን ቤት ለመሥራት የገባውን ውል የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት ይሰማው ይሆናል። ቤቱን የሚያሠራውን ግለሰብ ግን በግል ላያውቀው ይችላል። ቢሆንም የገባውን ቃል የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት ይገነዘባል።

      ምንም እንኳን ጋብቻ ምንም ስሜታዊ ትስስር የሌለው የንግድ ስምምነት ባይሆንም ቃል የተጋቡት ግለሰቦች ቃላቸውን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው። አንተና የትዳር ጓደኛህ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ