የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ፍቅር በጠፋበት ትዳር ተጠምዶ መኖር
    ንቁ!—2001 | ጥር 8
    • ፍቅር በጠፋበት ትዳር ተጠምዶ መኖር

      “ፍቺ በተስፋፋበት ኅብረተሰብ ውስጥ ደስታ ርቋቸው በፍቺ የሚያከትሙ ትዳሮች ቁጥር ብቻ ሳይሆን ደስታ እየራቃቸው ያሉ ትዳሮች ቁጥርም እየጨመረ መሄዱ አይቀርም።” —⁠በአሜሪካ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተቋቋመ ምክር ቤት

      ከሕይወት የሚገኘው ደስታም ሆነ ሐዘንና ምሬት በአብዛኛው የሚመነጨው ከአንድ ምንጭ፣ ማለትም ከትዳር እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል። በእርግጥም የትዳርን ያህል ብዙ ደስታ ወይም ብዙ ምሬትና ችግር የማስከተል አቅም ያላቸው ነገሮች በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከዚህ ጽሑፍ ጋር በአባሪነት የቀረበው ሳጥን እንደሚያሳየው ትዳር የምሬትና የችግር ምንጭ የሆነባቸው ባለትዳሮች ቁጥር ቀላል አይደለም።

      ይሁን እንጂ ስለ ፍቺ የሚቀርቡ አኃዛዊ መረጃዎች የችግሩን ስፋት ሙሉ በሙሉ አያሳዩም። በፍቺ እንዳከተሙት ትዳሮች ወደ አዘቅት ባይወርዱም ማዕበል ባናወጠው ባሕር ላይ ወደፊትም ሆነ ወደኋላ መሄድ የተሳናቸው ትዳሮች በጣም ብዙ ናቸው። ከ30 ዓመት በላይ በትዳር የኖረች አንዲት ሴት “ደስታ የሰፈነበት ቤተሰብ ነበረን፣ ያለፉት 12 ዓመታት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆነውብናል” ስትል ገበናዋን ገልጣ ተናግራለች። “ባለቤቴ ስለ ስሜቴ ፈጽሞ ደንታ የለውም። በእርግጥ የእርሱን ያህል በስሜቴ ላይ ክፉ ጠላት የሆነብኝ የለም።” በተመሳሳይም 25 ዓመት ያህል በትዳር የኖረ አንድ ባል እንደሚከተለው በማለት ምሬቱን ገልጿል:- “ባለቤቴ ለእኔ ያላት ፍቅር ተሟጥጦ እንዳለቀ ነግራኛለች። እንደ ደባል ሆነን ብንኖርና በመዝናኛ ጊዜያት የየራሳችንን የተለያየ አቅጣጫ ብንከተል ምናልባት እንቻቻል ይሆናል ትለኛለች።”

      እርግጥ፣ እንዲህ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከወደቁት መካከል አንዳንዶቹ ትዳራቸውን ያፈርሳሉ። ለአብዛኞቹ ግን ፍቺ ሊታሰብ የማይችል አማራጭ ነው። ለምን? ዶክተር ካረን ካይዘር እንደሚሉት ባለትዳሮች አንዳቸው ለሌላው ያላቸው ፍቅር ተሟጥጦ ቢያልቅም በልጆቻቸው፣ ማኅበረሰቡ በሚያሳድርባቸው ጫና፣ በገንዘብ ነክ ችግሮች፣ በቤተ ዘመድ፣ በወዳጆች ወይም በሃይማኖታዊ እምነታቸውና በመሳሰሉት ምክንያቶች ተገድደው አብረው ይኖራሉ። “እነዚህ ባልና ሚስቶች በሕግ አይፋቱ እንጂ በስሜት ከፈቷቸው የትዳር ጓደኞች ጋር አብረው ለመኖር ይመርጣሉ።”

      ታዲያ እንደነዚህ ያሉት የእርስ በርስ ዝምድናቸው የቀዘቀዘባቸው ባልና ሚስቶች ይህን የመሰለውን አሳዛኝ ኑሮ የግዴታ ተቀብለው መኖር አለባቸው ማለት ነውን? ከፍቺ ሌላ ያለው አማራጭ ፍቅር በጠፋበት ትዳር መኖር ብቻ ነውን? ብዙዎቹን በችግር የተዋጡ ትዳሮች ፍቺ ከሚያስከትለው ምሬት ብቻ ሳይሆን ፍቅር ማጣት ከሚያስከትለው ሐዘን ጭምር መታደግ እንደሚቻል በተሞክሮ ተረጋግጧል።

  • ፍቅር የሚቀዘቅዘው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2001 | ጥር 8
    • ፍቅር የሚቀዘቅዘው ለምንድን ነው?

      “እንደተፋቀሩ መኖር በፍቅር የመያዝን ያህል አይቀልም።”​—⁠ዶክተር ካረን ካይዘር

      ፍቅር ያጡ ትዳሮች እንደ አሸን መፍላታቸው የሚያስደንቅ ነገር ላይሆን ይችላል። ጋብቻ በጣም ውስብስብ የሆነ ሰብዓዊ ዝምድና ሲሆን ብዙዎቹ የሚገቡበት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ ነው። “የመንጃ ፈቃድ ስናወጣ መጠነኛ የሆነ ችሎታ ያለን መሆኑን እንድናሳይ እንጠየቃለን። የጋብቻ የምሥክር ወረቀት ለማግኘት ግን የሚጠየቀው ፊርማ ብቻ ነው” ሲሉ ዶክተር ዲን ኤስ ኢዴል ተናግረዋል።

      ስለዚህ እንደለመለሙ የሚኖሩና ደስታ የሰፈነባቸው ትዳሮች በርካታ ቢሆኑም ጥቂት ያይደሉ ትዳሮች ችግር ያጋጥማቸዋል። አንዱ ወይም ሁለቱም ባለትዳሮች ዘላቂ ዝምድና ለመመሥረት የሚያስችል ብቃት ሳይኖራቸው እንዲሁ ከትዳር ሕይወት ብዙ ነገር በመጠበቅ ጋብቻ መሥርተው ይሆናል። ዶክተር ሐሪ ራይስ ሲያብራሩ “ሰዎች መቀራረብ እንደጀመሩ አንዳቸው በሌላው ላይ ከፍተኛ የሆነ የመተማመን ስሜት ያድርባቸዋል” ሲሉ ገልጸዋል። ከጓደኛቸው “በስተቀር የእነርሱ ዓይነት አመለካከት ያለው ሰው በምድር ላይ እንዳልተፈጠረ” ሆኖ ይሰማቸዋል። “እንዲህ ያለው ስሜት እየሞተ የሚሄድበት ጊዜ አለ። በሚሞትበት ጊዜ ደግሞ በትዳሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።”

      የሚያስደስተው ግን ብዙዎቹ ትዳሮች እዚህ ደረጃ ላይ አይደርሱም። ይሁንና ለአንዳንድ ትዳሮች ፍቅር መቀዝቀዝ ምክንያት የሚሆኑትን ጥቂት ምክንያቶች እንመልከት።

      ብስጭት​—⁠“የጠበቅኩት ይህን አልነበረም”

      “ጂምን ባገባሁ ጊዜ” ትላለች ሮዝ “በአካባቢያችን ያሉትን በሙሉ የሚያስቀና ፍቅርና መተሳሰብ የሰፈነበት ትዳር የምንመሠርት መስሎኝ ነበር።” ከጊዜ በኋላ ግን የሮዝ ባል እንዳሰበችው ሳይሆን ቀረ። “በመጨረሻ የነበረኝ ተስፋ በሙሉ ተሟጠጠ” ትላለች።

      ብዙ ፊልሞች፣ መጻሕፍትና ተወዳጅ ዘፈኖች ፍቅርን ስለው የሚያቀርቡበት መንገድ በገሐዱ ዓለም የሌለ ነው። አንድ ወንድና ሴት ለጋብቻ በሚጠናኑበት ወቅት ሕልማቸው በሙሉ እውን የሆነላቸው መስሎ ሊሰማቸው ይችላል። ከጥቂት ዓመታት የትዳር ኑሮ በኋላ ግን በእውነትም እውን ሊሆን በማይችል ሕልም ውስጥ ነበርኩ ብለው ያስባሉ። ትዳራቸው በልብ ወለድ ታሪኮች ያነበቡትን ዓይነት ካልሆነ ያልተሳካ ሆኖ ይታያቸዋል።

      እርግጥ ከጋብቻ ሊጠበቁ የሚገባቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ከትዳር ጓደኛ ፍቅር፣ ትኩረትና ድጋፍ ለማግኘት መጠበቅ ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ እንኳን ሳይገኙ ሊቀሩ ይችላሉ። በሕንድ የምትኖረውና ወጣት ሙሽራ የሆነችው ሚና “እንዳገባሁ ሆኖ አይሰማኝም። ብቸኛና የተጣልኩ እንደሆንኩ ይሰማኛል” ብላለች።

      አለመጣጣም​—⁠“አንድም የምንመሳሰልበት ነገር የለም”

      አንዲት ሴት “እኔና ባለቤቴ በሁሉም ነገሮች ላይ ማለት ይቻላል፣ 180 ዲግሪ የተራራቅን ነን” ብላለች። “ለምን አገባሁት ብዬ ሳልፀፀት ያሳለፍኩት አንድም ቀን የለም። ፈጽሞ ልንጣጣም የማንችል ሰዎች ነን።”

  • ተስፋ ለማድረግ የሚያበቃ ምክንያት ይኖር ይሆን?
    ንቁ!—2001 | ጥር 8
    • ተስፋ ለማድረግ የሚያበቃ ምክንያት ይኖር ይሆን?

      “ውጥረት የነገሠባቸው ትዳሮች ካሉባቸው ችግሮች አንዱ ሁኔታው ሊሻሻል አይችልም የሚል አፍራሽ አስተሳሰብ ማሳደራቸው ነው። እንዲህ ያለው እምነት ማንኛውንም ዓይነት ገንቢ ጥረት ለማድረግ እንዳትነሳሳ ስለሚያደርግ ትልቅ እንቅፋት ይሆናል።”​—⁠ዶክተር አሮን ቲ ቤክ

      ከባድ ሕመም ስለሚሰማህ ምርመራ ለማድረግ ወደ ሐኪም ሄደሃል እንበል። በጣም አሳስቦሃል። ጤንነትህ፣ ሕይወትህም ጭምር አደጋ ላይ ወድቆ ይሆናል። ይሁን እንጂ ሐኪሙ አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኋላ ያጋጠመህ ችግር በቀላሉ የሚታይ ባይሆንም በሕክምና ሊረዳ የሚችል እንደሆነ ቢነግርህስ? እንዲያውም ሐኪሙ ጤናማ የሆነ የአመጋገብና የአካላዊ እንቅስቃሴ ልማድ ብትከተል ሙሉ በሙሉ ልትድን እንደምትችል ነገረህ እንበል። ትልቅ የእፎይታ ስሜት እንደሚሰማህና ምክሩን በደስታ እንደምትቀበል አያጠራጥርም!

      ይህንን ሁኔታ ከተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ ጋር አነጻጽር። በትዳርህ ውስጥ አንዳንድ ችግሮች መከሰት ጀምረዋልን? እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ትዳር ቢሆን ችግሮችና አለመግባባቶች ያጋጥሙታል። ስለዚህ በዝምድናችሁ መካከል አልፎ አልፎ አስቸጋሪ ወቅቶች ቢከሰቱ በትዳራችሁ ውስጥ ፍቅር ጠፍቷል ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ የተፈጠረው ችግር ለሳምንታት፣ ለወራት እንዲያውም ለዓመታት ቢቀጥልስ? ይህ በቀላሉ የሚታይ ነገር ስላልሆነ ሊያሳስባችሁ ይገባል። እንዲያውም ጠቅላላ ሕይወታችሁ፣ የልጆቻችሁ ሕይወት ሳይቀር በትዳራችሁ ሁኔታ ሊነካ ይችላል። ለምሳሌ በጋብቻ ውስጥ የሚከሰት ችግር ለመንፈስ ጭንቀት፣ ለምርታማነት መቀነስ፣ ለልጆች በትምህርት መድከምና ለመሳሰሉት ችግሮች ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። ይሁን እንጂ በዚህ ብቻ አያበቃም። ክርስቲያኖች ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ያላቸው ዝምድና ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና ጭምር ሊነካባቸው እንደሚችል ይገነዘባሉ።​—⁠1 ጴጥሮስ 3:​7

      በአንተና በትዳር ጓደኛህ መካከል ችግሮች መከሰታቸው ተስፋ ከሌለው ሁኔታ ላይ መድረሳችሁን አያመለክትም። አንድ ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ ችግር ማጋጠሙ የማይቀር መሆኑን መገንዘባቸው የችግራቸውን ትክክለኛ ገጽታ እንዲመለከቱና መፍትሄ ለማግኘት ጥረት እንዲያደርጉ ሊረዳቸው ይችላል። አይዚክ የተባለ አንድ ባል እንዲህ ብሏል:- “ባልና ሚስት በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ የሚከፉበትም ሆነ የሚደሰቱበት ጊዜ መኖሩ የማይቀር መሆኑን አላውቅም ነበር። የኛ ትዳር አንድ ዓይነት ችግር ሳይኖረው አይቀርም ብዬ አስብ ነበር!”

      የትዳራችሁ ሁኔታ በጣም ተበላሽቶ ፍቅር የጠፋበት እስከመሆን ቢደርስም ከመፍረስ ሊድን ይችላል። እርግጥ የተናጋ ዝምድና፣ በተለይ ችግሩ ለዓመታት የቆየ ከሆነ የሚያስከትለው ቁስል በቀላሉ ሊሽር እንደማይችል የታወቀ ነው። ያም ሆኖ ግን ተስፋ ለማድረግ የሚያበቃ ጠንካራ ምክንያት አለ። ወሳኙ ነገር በቁርጠኝነት መነሳት ነው። ትዳራቸው በእጅጉ የተናጋባቸው

  • ትዳራችሁን መታደግ ትችላላችሁ!
    ንቁ!—2001 | ጥር 8
    • ትዳራችሁን መታደግ ትችላላችሁ!

      መጽሐፍ ቅዱስ ባሎችንም ሆነ ሚስቶችን ሊጠቅሙ በሚችሉ ተግባራዊ ምክሮች የተሞላ ነው። ይህ ደግሞ ሊያስደንቀን አይገባም። ምክንያቱም የጋብቻ መሥራች መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈሱ ያስጻፈው አምላክ ነው።

      መጽሐፍ ቅዱስ ትዳርን ሥሎ የሚያቀርብበት መንገድ ከእውነታው ያልራቀ ነው። ባልና ሚስቶች “መከራ” ወይም ኒው ኢንግሊሽ ባይብል እንደሚለው “ሥቃይና ሐዘን” እንደሚያጋጥማቸው ሳይሸሽግ ይናገራል። (1 ቆሮንቶስ 7:​28) ይሁን እንጂ ጋብቻ ደስታ እንዲያውም የስሜት እርካታ ሊያስገኝ እንደሚችልና ማስገኘትም እንዳለበት ይናገራል። (ምሳሌ 5:​18, 19) እነዚህ ሁለት ሐሳቦች እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ አይደሉም። አንድ ባልና ሚስት ከባድ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም የጠበቀና ፍቅር የሰፈነበት ዝምድና

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ