መዝሙር 120
ስማ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ
በወረቀት የሚታተመው
1. ክርስቶስን ሰምተን ስንታዘዘው፣
ትምህርቶቹ ብርሃን ይሆኑናል።
መስማትና ማወቅ ያስደስተናል፤
መታዘዝ ግን በረከት ያስገኛል።
(አዝማች)
አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
2. በዓለት ላይ የተመሠረተ ቤት፣
ለሰው ከለላ ’ንደሚሆንለት፣
የኢየሱስን ትምህርቶች መከተል፣
ሕይወታችንን ይጠብቀዋል።
(አዝማች)
አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
3. በውኃ ዳር እንደተተከለ ዛፍ፣
በየወቅቱ ፍሬ እንደሚሰጥ፣
እንደ ልጆቹ አምላክን ብንሰማው፣
ይሰጠናል የዘላለም ሕይወት።
(አዝማች)
አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣
ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።
(በተጨማሪም ዘዳ. 28:2ን፣ መዝ. 1:3ን፣ ምሳሌ 10:22ን እና ማቴ. 7:24-27ን ተመልከት።)