መዝሙር 61
ምን ዓይነት ሰው መሆን አለብኝ?
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ አምላኬ፣ እንዴት ልክፈልህ?
ለሰጠኸኝ ሕይወት በምን ላመስግንህ?
ቃልህ መስታወት ነው ውስጤን የማይበት፤
እርዳኝ ልመልከት ራሴን በሐቀኝነት።
አንተን ለማገልገል ገብቻለሁ ቃል፤
የማደርገው ሁሉ አይደለም ለይምሰል።
ሙሉ ልቤን ላንተ እሰጥሃለሁ፤
አንተን ማስደሰት እፈልጋለሁ።
2. ልመርምረው ውስጤን ልወቀው ልቤን፤
የምትፈልገውን ዓይነት ሰው መሆኔን።
ታማኞችህን ሁሌ ትባርካለህ፤
እኔም እንደ ወዳጆችህ ላስደስትህ።
(በተጨማሪም መዝ. 18:25፤ 116:12፤ 119:37ን እና ምሳሌ 11:20ን ተመልከት።)