-
ማስታወቂያዎችየመንግሥት አገልግሎት—1996 | ሐምሌ
-
-
ማስታወቂያዎች
◼ በሐምሌና በነሐሴ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” (በእንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ነጠላ ቅጂዎች፤ እንዲሁም ኮንትራት ማስገባት።
◼ በእጃችን ያሉ ጽሑፎች፦ አረብኛ፦ እውቀት፣ ሥላሴ፣ አምላክ ክፋትን የፈቀደው ለምንድን ነው? (ባለ 32 ገጽ ቡክሌት)፣ ዘ ታይም ፎር ትሩ ሳብሚሽን ቱ ጎድ (ባለ 64 ገጽ ቡክሌት)፣ ትራክት T-72 ታላቁ ስም። እንግሊዝኛ፦ እውቀት (5 ክሮች ያሉት አልበም)፣ የ1995 የንቁ! ጥራዝ፣ የ1995፣ የ1956ና የ1957 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች። ፈረንሳይኛ፦ የ1995 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ጥራዞች፣ ለሁሉም ሰዎች የሚሆን ምሥራች።
◼ እንደገና የመጡ ጽሑፎች፦ አረብኛ፦ ለዘላለም መኖር (ትንሹ)፣ ወጣትነትህ፣ ትራክቶች:- T-13፣ T-14፣ T-15፣ T-16። እንግሊዝኛ፦ ፍጥረት (ትንሹ)፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፣ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም ዲሉክስ (Dbi12)፣ ዲሉክስ በኪስ ሊያዝ የሚችል (Dbi25)፣ የ1987፣ 1988፣ 1989 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች። ፈረንሳይኛ፦ ፍለጋ።
-
-
አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁንየመንግሥት አገልግሎት—1996 | ሐምሌ
-
-
አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን
1 ለምናገኛቸው አጋጣሚዎች ንቁ ከሆንን በጥሩ መንገድ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው በአገልግሎታችን የምናገኛቸው ብዙ አመቺ ሁኔታዎች አሉ። (ቆላ. 4:5) ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው “እነዚህን መጽሔቶች እወዳቸዋለሁ” ሊል ይችላል። ይህ ኮንትራት እንዲገባ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ለመጠየቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው! ሌላ ሰው ደግሞ “ይህ ጽሑፍ ጥሩ ይመስላል። ይሁን እንጂ ገንዘብ የለኝም” ሊል ይችላል። በዚህ ጊዜ ሌላ ቀን ተመልሰህ ጽሑፉን አንድ ላይ ሆናችሁ እንድታነቡ ወይም ገንዘብ በሚያገኝበት ጊዜ ለመምጣት እንደምትችል ልትገልጽለት ትችላለህ።
2 አንዳንድ ጊዜ ፍላጎት ያሳየ ሰው የምናገኘው በሌላ ሰው ቤት ወይም በመንገድ ላይ ሊሆን ይችላል። ታዲያ አድራሻውን ለመቀበል ንቁዎች ነን? ቤቱ ቅርብ ከሆነ ሊያሳይህ ይችል እንደሆነ ጠይቀው። ብዙዉን ጊዜ ሰዎች የወዳጅነት ስሜት ቢኖራቸውም ጊዜ እንደሌላቸው ይናገራሉ። ይህ መጽሔት ወይም ቢያንስ ቢያንስ ትራክት በማበርከት መልእክታችንን በአጭሩ በአንድ አረፍተ ነገር ማቅረብ የምንችልበት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። በአገልግሎት ጊዜ የምትጠቀምበትን አጭር መግቢያ ቀደም ብለህ ለመለማመድ ለምን አትሞክርም?
3 ብዙ አስፋፊዎች የቤቱ ባለቤት በሩ ጋር ሲደርስ ጭንቅ ጥብብ ይላቸዋል። ይሁን እንጂ ሳትጨነቅ አንድ መግቢያ ከተናገርክ ብዙ አጋጣሚዎች ልትከፍት ትችላለህ። እንዲህ ለማለት ትችላለህ:- “ከዚህ በፊት የማያውቋቸውን ሰዎች በማየትዎ የተደናገጡ ይመስላሉ። እርግጥ ችግርዎ ይገባናል፤ በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው ከዚህ በፊት ከማያውቀው ሰው ጋር ሲገናኝ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ይተዋወቁ ያልነበሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው እንደ ጓደኛ ወይም እንደ ወንድማማች የሚተያዩበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚመጣ ብዙ ሰዎች አያውቁም። ይህን ያምናሉ?”
4 በተመሳሳይ መንገድ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ከሚያጋጥሙት የተለመዱ ሁኔታዎች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። አንዲት ሴት ልብስ እያጠበች ይሆናል። እያከናወነች ላለችው ሥራ አድናቆትህን ከገለጽክ በኋላ ለአምስት ደቂቃ ያህል ሥራዋን አቋርጣ አንድ አስደሳች የሆነ ነገር እንድትሰማ ሐሳብ አቅርብላት። አንድ ወላጅ ከልጁ ጋር ሆኖ ታገኘው ይሆናል። የልጁን እድሜ ጠይቅና ይህ ልጅ ትልቅ በሚሆንበት ጊዜ ዓለማችን ምን ሊመስል እንደሚችል ጥያቄ አቅርብ። ወይም አንድ ወጣት በሩን ይከፍት ይሆናል። እድሜው ስንት እንደሆነ ወይም ስለ ትምህርቱ ሁኔታ፣ በሕይወቱ ውስጥ ስላለው ዓላማ ጠይቅና በዚህ ዘመን አንድ ወጣት በቀላሉ ደስታ ማግኘት ስለ መቻሉ ወይም ደስታ ማግኘት ቀላል ስለ መሆኑ ጠይቀው። እረፍት ላይ ያለ አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ይኖር ይሆናል። በዛሬው ጊዜ አእምሮአችን ስለ ተለያዩ ችግሮች ማውጠንጠን እንደሚቀናው ከገለጽክለት በኋላ አንተ ግን የሄድከው አእምሮ በአስደሳች ሐሳቦች ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ እንደሆነ ልትጠቅስ ትችላለህ።
5 አጋጣሚዎች እንዲያመልጡህ አትፍቀድ። የቤቱን ባለቤት ማግኘት ባትችልም ልታነጋግረው የምትችል ሌላ እንግዳ እቤት ይኖር ይሆናል። አንዳንድ እንግዳዎች ምሥራቹ ካልተዳረሰበት ክልል የመጡ ናቸው! ወይም አንድ ሰው ስታነጋግር ሁለተኛ ሰው መጥቶ ሊሰማ ይችላል። ሁለቱንም አነጋግርና የቤቱ ባለቤት ማን እንደሆነ ጠይቅ። አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ እንድትሆን ይሖዋ እንዲረዳህ ጠይቀው። አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ! እንዲህ ካደረግህ የጥረትህን ዋጋ ታገኛለህ!
-
-
በአቅኚነት አገልግሎት ተጨማሪ ወንድሞች ያስፈልጋሉየመንግሥት አገልግሎት—1996 | ሐምሌ
-
-
በአቅኚነት አገልግሎት ተጨማሪ ወንድሞች ያስፈልጋሉ
1 ጳውሎስ “የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ” በማለት አበረታቷል። (1 ቆሮ. 15:58) ይህም ለብዙዎች በአቅኚነት አገልግሎት መጠመድን የሚጠይቅ ነው። ባለፈው መስከረም ከ90 የሚበልጡ ተጨማሪ አቅኚዎች ተገኝተዋል!
2 በአሁኑ ጊዜ በእዚህ አገር አቅኚ ሆነው ከሚያገለግሉት መካከል ብዙዎቹ እህቶች ናቸው። (መዝ. 68:11 አዓት) ተጨማሪ ወንድሞች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ቢካፈሉ ለጉባኤ ምን ያህል ደስታ ያመጣ ይሆን! (መዝ. 110:3 አዓት) ብዙ ወንድሞች ከባድ የሆነ ሥጋዊ ሥራና የቤተሰብ ኃላፊነት እንዳላቸው ግልጽ ነው። ሌሎች ደግሞ የጉባኤውን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት ጠንክረው ይሠራሉ። ለመንግሥቱ ሲሉ የሚደክሙትን እንደነዚህ ያሉትን ወንዶች እናደንቃቸዋለን።— 1 ጢሞ. 4:10
3 ቢሆንም ግን ከእናንተ መካከል ተጨማሪ ወንድሞች በአቅኚነት አገልግሎት መካፈል ይችሉ ይሆን? ሚስትህ አቅኚ ከሆነች አንተም አብረሃት አቅኚ መሆን ትችላለህ? ጡረታ የወጣህ ከሆንክ ጊዜህን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከማዋል የበለጠ የሚያስደስት ነገር የለም ቢባል አትስማማም? በቅርብ ጊዜ ትምህርት የጨረስክ ከሆንክ ለተጨማሪ መብቶች መሸጋገሪያ ድልድይ እንዲሆንልህ አቅኚ ለመሆን በጥንቃቄና በጸሎት አስበህበታል?— ኤፌ. 5:15-17
4 አንድ ወንድም ጥሩ ገቢ የሚያስገኝለትን የንግድ ሥራውን ከሸጠ በኋላ አቅኚ መሆን አንዲችል የትርፍ ሰዓት ሥራ ያዘ። ቀዳሚ ሆኖ በማገልገሉ ምክንያት ከአራቱ ልጆቹ መካከል ሦስቱ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ አቅኚ ሆኑ። አራተኛውም አብሯቸው አቅኚ የሚሆንበትን ጊዜ በጉጉት እየተጣባበቀ ነበር። ይህ ወንድምና ቤተሰቡ ብዙ በረከቶች አግኝተዋል።
5 ትልቅ በር ተከፍቷል፦ የአቅኚነት አገልግሎት “ሥራ የሞላበት ትልቅ በር” ሊከፍት ይችላል። (1 ቆሮ. 16:9) አቅኚ የሆኑ ወንድሞች በጉባኤ ውስጥ ብዙ ሥራዎችን ሊያከናውኑ ይችላሉ። ቅንዓት የሞላበት አገልግሎት መንፈሳዊ ጉልምስናቸውና ቲኦክራሲያዊ እድገታቸው ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ ያደርጋል። አቅኚ መሆን ለተጨማሪ የአገልግሎት መብቶች በር ሊከፍት ይችላል። ልዩ አቅኚ ለመሆን ወይም ለቤቴል አገልግሎት መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆን ይችላል። ለአንድ ዓመት በአቅኚነት ከተሳተፉ በኋላ በአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት የመካፈል በረከት አለ። ነጠላ የሆኑ የጉባኤ አገልጋዮችና ሽማግሌዎች በአገልጋዮች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለመካፈል ሊጣጣሩ ይችላሉ። አዎን፣ አቅኚ ሆኖ ማገልገል በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ባሉት በእነዚህ ታላላቅ መብቶች ለመካፈል በር ይከፍታል።
6 በዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ለመካፈል ሁኔታቸውን ያስተካከሉ ወንድሞች ብዙ መስጠት የሚያስገኘውን ታላቅ ደስታ ሊቀምሱ ይችላሉ።— ሥራ 20:35
-