-
ሞትከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ያሉትን ሊጐዱ ይችላሉ ከሚል ፍርሃት የመነጩ ናቸው። ነገር ግን ሙታን ሥቃይም ሆነ ደስታ ሊኖራቸው የማይችል መሆኑን የአምላክ ቃል ይናገራል። “መንፈሱ ይወጣል፤ ወደ መሬቱም ይመለሳል፤ በዚያ ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል። ” (መዝ. 146:4 አዓት፤ በተጨማሪ 2 ሳሙኤል 12:22, 23ን ተመልከት።) “ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፤ ከፀሐይ በታች በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲያ የላቸውም።”—መክ. 9:6
አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-
‘የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ይህ ብዙዎች ያላቸው እምነት ነው። እኔ ግን አምላክ ስለዚህ ነገር ምን እንደሚል መመርመሩን ጠቃሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘(ዘፍጥረት 2:17ን አንብብ።) አንድ አባት ልጁን ይህን ብታደርግ ትሞታለህ ብሎ ቢያስጠነቅቀው ልጁ ያን እርሱ የከለከለውን ነገር እንዲያደርግ አባትዬው ይፈልጋል ለማለት ይቻላል?’ (2) ‘እንግዲያው አምላክ ለሰዎች ያለው ፈቃድ ምንድን ነው? ኢየሱስ እንዲህ አለ:- “ልጅንም አይቶ [ማለትም ኢየሱስ በእውነት የአምላክ ልጅ መሆኑን አስተውሎና ተቀብሎ] በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፣ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” (ዮሐ. 6:40)’
‘ሞት ለዘላለም ይቀጥላል’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እስከ ዘመናችን ድረስ በሰዎች ላይ ሲደርስ የቆየው ይህ ሁኔታ ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ይሁን እንጂ እስቲ በራእይ 21:3, 4 ላይ (ወይም ኢሳይያስ 25:8) አምላክ የሰጠውን አስደናቂ ተስፋ ይመልከቱ።’
‘ቀንህ ከደረሰ ትሞታለህ’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ብዙ ሰዎች እርስዎ እንደሚሉት ይላሉ። ብዙዎቹ የጥንት ግሪካውያን ይህ ዓይነት አመለካከት እንደነበራቸው ያውቁ ነበር? እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል ዕድሜ እንደሚኖረው የሚወስኑ ሦስት ሴት አማልክት አሉ ብለው ያምኑ ነበር። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሕይወት የሚያቀርብልን አመለካካት ከዚህ በጣም የተለየ ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘(መክብብ 9:11ን አንብብ) ምሳሌ:- ከአንድ ሕንፃ ላይ አንድ ድንጋይ ተሸርፎ በአንድ መንገደኛ ላይ ወደቀ እንበል። ድንጋዩ በመንገደኛው ላይ እንዲወድቅ ያደረገው አምላክ ነው? ከሆነስ የሕንፃውን ባለቤት በቸልተኝነት ይህ አደጋ እንዲደርስ አደረገ ብሎ መክሰስ ትክክል ይሆናል? . . . መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ድንጋዩ በወደቀበት ጊዜ እግረኛው በዚያ ቦታ መገኘቱ ያልታሰበና ያልተጠበቀ አጋጣሚ ነበር።’ (2) ‘መጽሐፍ ቅዱስ መጥፎ አኗኗር ብናስወግድ ሕይወታችንን ልናተርፍ እንደምንችል ይነግረናል። (ምሳሌ 16:17) ወላጅ ከሆኑ ይህን መመሪያ ለልጆችዎ እንደሚጠቀሙበት እርግጠኛ ነኝ። ልጆችዎን እንዲህ ከመሰሉ ሕይወትን ሊያሳጡ ከሚችሉ ነገሮች እንዲርቁ ያስጠነቅቋቸዋል። ይሖዋም ዛሬ ለሰው ልጆች በማድረግ ላይ የሚገኘው ይህንኑ ነው።’ (3) ‘ይሖዋ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር ያውቃል። በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የእርሱን ምክር ከማይቀበሉት ሰዎች የበለጠ ዕድሜ ለመኖር እንዴት እንደምንችል ይነግረናል። (ዮሐ. 17:3፤ ምሳሌ 12:28)’ (በተጨማሪ “ዕድል” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።)
-
-
ሕልምከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ሕልም
ፍቺ:- አንድ ሰው በእንቅልፍ ላይ እያለ የሚመጣበት ሐሳብ ወይም በአእምሮ ውስጥ የሚቀረጽ ምስል ሕልም ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሯዊ ሕልሞች፣ ከአምላክ ስለሚገኙ ሕልሞችና ከምዋርት ጋር ግንኙነት ስላላቸው ሕልሞች ይናገራል።—ኢዮብ 20:8፤ ዘኍ. 12:6፤ ዘካ. 10:2
ሕልም በጊዜያችን ልዩ ትርጉም አለውን?
ተመራማሪዎች ስለ ሕልም ምን ነገር ተረድተዋል?
ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ (1984፣ ጥራዝ 5፣ ገጽ 279) “እያንዳንዱ ሰው ሕልም ያያል። አብዛኞቹ አዋቂዎች በስምንት ሰዓት የእንቅልፍ ጊዜ ውስጥ ለ100 ደቂቃ ያህል ሕልም ያያሉ” ብሏል። ስለዚህ ሕልም ተፈጥሯዊና የተለመደ ክስተት ነው።
የሐርቫርድ ሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑት ዶክተር አለን ሆብሰን እንዲህ በማለት ተናግረዋል:- “ሕልም፣ ሕልም ፈቺ ሁሉ እንደየዝንባሌው በፈለገው መንገድ ሊተረጉመው የሚችል የተወሰነ ፍች የሌለው ስሜት ቀስቃሽ ነገር ነው። የሕልም ፍች የሚወሰነው በሕልሙ በራሱ ሳይሆን በተመልካቹ ዓይን ነው” ብለዋል። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ የተባለው መጽሔት “ሳይንስ
-