የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት
    የመንግሥት አገልግሎት—2001 | ታኅሣሥ
    • 3 በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብብ:- ቦርሳ ሳትይዝ አገልግሎት መውጣትን መሞከር ትችላለህ። የሚበረከተውን ጽሑፍ በባይንደር መጽሐፍ ቅዱስህን ደግሞ በእጅህ ወይም በኪስህ ልትይዝ ትችላለህ። ከዚያም ከአንድ ሰው ጋር ውይይት ስትጀምር ሰውዬው ሃይማኖታዊ ትምህርት ልትሰብከው እንደሆነ እንዲሰማው ሳታደርግ መጽሐፍ ቅዱስህን አውጣ። ከመጽሐፍ ቅዱስህ ጥቅስ አውጥተህ በምታነብበት ጊዜ አቋቋምህ የምታነጋግረው ሰው እያየ መከታተል በሚችልበት ሁኔታ ይሁን። ምናልባትም ራሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲያነብ ልትጋብዘው ትችላለህ። ሲነበብ ከመስማት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ራሱ ሲመለከት በጥልቅ ሊነካ ይችላል። እርግጥ ነው፣ የጥቅሱን ሐሳብ እንዲገነዘብ ለመርዳት ሐሳቡን የሚያስተላልፉትን ቃላት ማጉላት ያስፈልጋል።

      4 በአንድ ጥቅስ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ:- ራስህን ካስተዋወቅህ በኋላ እንዲህ ልትል ትችላለህ:- “ሰዎች ለሕይወታቸው መመሪያ ለማግኘት ወደ ተለያዩ ምንጮች ዞር ይላሉ። ከሁሉ የተሻለ ተግባራዊ መመሪያ የሚገኘው ከየት ነው ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህንን አባባል እንዴት ይመለከቱታል? [ምሳሌ 2:6, 7ን አንብብና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ሰብዓዊ ጥበብ ብቃት ስለሚጎድለው ብዙ ሰዎችን ወደ ተስፋ መቁረጥ እየመራቸው ይገኛል። የአምላክ ጥበብ ግን ምንጊዜም እምነት የሚጣልበትና ጠቃሚ እንደሆነ ተረጋግጧል።” ከዚያም የምታበረክተውን ጽሑፍ አውጣና ከአምላክ የሚገኘውን ተግባራዊ ጥበብ የሚያጎላ አንድ ምሳሌ አሳየው።

  • የ2002 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
    የመንግሥት አገልግሎት—2001 | ታኅሣሥ
    • 3 መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብቡ:- ብዙውን ጊዜ በቅርብ ማግኘት በምንችልበት ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስን የምንይዝ ከሆነ ያለንን ማንኛውንም ነጻ ጊዜ ለንባብ ልንጠቀምበት እንችላለን። አብዛኞቻችን በቀኑ ውስጥ በዚህ መንገድ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ጥቂት ትርፍ ደቂቃዎች ይኖሩናል። በየዕለቱ ቢያንስ አንድ ገጽ ማንበብ እንዴት ጠቃሚ ነው! እንዲህ በማድረግ ከትምህርት ቤቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ጋር እኩል መጓዝ እንችላለን።​—⁠መዝ. 1:1-3

      4 መጽሐፍ ቅዱስን ጥሩ አድርጎ የማንበብ ችሎታ የአድማጮቻችንን ልብ ለመንካትና ይሖዋን እንዲያወድሱ ለማነሳሳት ሊረዳን ይችላል። ክፍል ቁጥር 2ን የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበውን የንባብ ክፍል ጮክ ብለው በማንበብ ደግመው ደጋግመው መለማመድ ይኖርባቸዋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ክፍሉን ያቀረበውን ወንድም ያመሰግናል እንዲሁም ንባቡን ለማሻሻል የሚረዱትን ሐሳቦች ይጠቁመዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ