-
ሕይወትከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ዘ ኢንሳይክሎፔድያ አሜሪካና እንዲህ ይላል:- “[እኛ ከምንገኝበት ሶላር ሲስተም ውጭ] ሌላ ፕላኔት ሊገኝ አልቻለም። ይሁን እንጂ ከሶላር ሲስተም ውጭ ፕላኔት ከተገኘ በዚህ ፕላኔት ላይ ተጀምሮ ወደ ከፍተኛ ሥልጣኔ ያደገ ሕይወት የሚኖርበት አጋጣሚ ይኖራል።” (1977፣ ጥራዝ 22፣ ገጽ 176) (ከዚህ መግለጫ መረዳት እንደሚቻለው ይህ በውጭ ዓለማት ውስጥ ሕይወት ይኖር እንደሆነ ለማወቅ የሚደረገው ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ምርምር የሚካሄድበት ዋነኛ ዓላማ ዝግመተ ለውጥን ማለትም ሰው በአምላክ እንዳልተፈጠረና በዚህም ምክንያት በአምላክ ዘንድ ተጠያቂነት እንደሌለበት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለማግኘት ይሆን?)
መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት የሚገኘው በዚህ ምድር ላይ ብቻ እንዳልሆነ ይገልጻል። በእውቀታቸውም ሆነ በማሰብ ችሎታቸው ከሰው እጅግ በጣም የሚበልጡ መንፈሳዊ አካላት ማለትም አምላክና መላእክት አሉ። እነርሱም ሕይወት የተገኘው ከየት እንደሆነና በዓለም ላይ ለተጋረጡት ከባድ ችግሮች መፍትሔው ምን እንደሆነ ለሰው ልጆች አሳውቀዋል። (“መጽሐፍ ቅዱስ” እና “አምላክ” የሚሉትን ዋና ዋና ርዕሶች ተመልከት።)
-
-
ጋብቻከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ጋብቻ
ፍቺ:- ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ በሰፈረው ሥርዓትና ደንብ መሠረት ባልና ሚስት ሆነው በአንድነት ለመኖር የሚመሠርቱት ውህደት ነው። ጋብቻ መለኮታዊ ተቋም ነው። በትዳር ጓደኞች መካከል የፍቅር መንፈስ ስለሚኖርና አንዱ የትዳር ጓደኛ ለሌላው አሳቢነት ለማሳየት ቃል የገባ ስለሆነ ጋብቻ በባልና በሚስት መካከል መተማመን ያለበትና የተቀራረበ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል። ይሖዋ ጋብቻን ያቋቋመው የወንድ ማሟያ የምትሆን የቅርብ ጓደኛ ለማስገኘት ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ዝግጅት አማካኝነት ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች እንዲወለዱ ሲል ነው። በሚቻልበት ቦታ ሁሉ የክርስቲያን ጉባኤ የሚቀበለው ማንኛውም ጋብቻ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ እንዲሆን ይፈለጋል።
ከአገሩ ሕግ ጋር የሚስማማ ጋብቻ መመሥረት አስፈላጊ ነውን?
ቲቶ 3:1:- “ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ . . . እንዲሆኑ አሳስባቸው።” (ሰዎች እነዚህን መመሪያዎች ሲያከብሩ የተጋቢዎቹ ስም ከነቀፋ ይጠበቃል። የሚወለዱትም ልጆች ሕጋዊ ጋብቻ ከሌላቸው ወላጆች በሚወለዱ ልጆች ላይ ከሚደርሰው ነቀፋ ይድናሉ። በተጨማሪም ጋብቻን ሕግ በሚጠይቀው መንገድ ማስመዝገብ ከትዳር ጓደኛሞች አንዱ በሞት በሚለይበት ጊዜ የቤተሰቡን የንብረት ባለቤትነት መብት ለማስጠበቅ ይጠቅማል።)
ዕብ. 13:4:- “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።” (በሕጋዊ መንገድ መጋባቱ ጋብቻው “ክቡር” እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው። ለ“ሴሰኝነት” እና ለ“ምንዝር” በምንሰጠው ትርጉም ላይ በቲቶ 3:1 ላይ የተጠቀሰውን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል።)
1 ጴጥ. 2:12–15:- “ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፣ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፣ በሚጐበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፣ ከሁሉ በላይ ነውና፤ ለመኳንንትም ቢሆን፣ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ። በጎ እያደረጋችሁ፣ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና።”
አዳምና ሔዋን አብረው መኖር ሲጀምሩ “ሕጋዊ ሥርዓት” ተፈጽሞ ነበረን?
ዘፍ. 2:22–24:- “እግዚብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ:- ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህም ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፣ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (አዳምንና ሔዋንን አንድ ላይ እንዲኖሩ ያደረገው የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ ይሖዋ አምላክ ራሱ እንደሆነ ልብ በል። አንድ ወንድና አንዲት ሴት ስለ ሕጋዊ ባለ ሥልጣን ሳይጨነቁ አብረው ለመኖር አልወሰኑም። የጋብቻ አንድነት ዘላቂ መሆን እንዳለበት አምላክ ጠበቅ አድርጎ የተናገረውንም ልብ በል።)
ዘፍ. 1:28:- “እግዚአብሔርም [አዳምንና ሔዋንን] ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው:- ብዙ፣ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት፣ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” (እዚህ ላይ የመጨረሻው ከፍተኛ ሕጋዊ ባለ ሥልጣን ጋብቻውን ባርኮታል። ሩካቤ ሥጋ እንዲፈጽሙ የተፈቀደላቸው ሲሆን ለሕይወታቸውም ትርጉም የሚሰጥ ሥራ ሰጣቸው።)
አንድ ሰው የአካባቢው ሕግ የሚፈቅድለት ከሆነ ከአንድ ሚስት በላይ ሊኖረው ይችላልን?
1 ጢሞ. 3:2, 12:- “ኤጲስ ቆጶስ [“የበላይ ተመልካች” አዓት ]
-