የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • be ጥናት 26 ገጽ 170-ገጽ 173 አን. 4
  • ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር
  • በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስተዋጽኦ ማዘጋጀት
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • አንድ ወጥ ሆኖ የተቀነባበረ ንግግር
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • አዲስ ነገር የሚያሳውቅ፤ ግልጽ፣ የሚጨበጥ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
be ጥናት 26 ገጽ 170-ገጽ 173 አን. 4

ጥናት 26

ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር

ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ነጥቦቹ እርስ በርሳቸውም ሆነ ከመደምደሚያው ወይም ከንግግርህ ዓላማ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ በግልጽ በሚያሳይ መንገድ ትምህርቱን ማዋቀር ይኖርብሃል።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርቱን በሚጨበጥ መንገድ ካቀረብኸው አድማጮች በቀላሉ ሊረዱት፣ ሊቀበሉት እና ሊያስታውሱት ይችላሉ።

ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ለማዋቀር በመጀመሪያ አንድ ግብ ሊኖርህ ይገባል። ግብህ አንድን እምነት፣ አመለካከት፣ ባሕርይ፣ ድርጊት ወይም አኗኗር በተመለከተ የተወሰነ መረጃ መስጠት ብቻ ነው? ወይስ አንድ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን ማሳመን? ወይም ደግሞ ዓላማህ አድማጮችህ ለአንድ ነገር አድናቆት እንዲያድርባቸው ወይም ለተግባር እንዲነሳሱ ማድረግ ነው? ትምህርቱን የምታቀርበው ለአንድ ግለሰብም ይሁን ለብዙ አድማጮች ይህን ግብህን ለማሳካት አድማጮችህ ስለ ጉዳዩ ምን ያህል እውቀት እንዳላቸውና አመለካከታቸው ምን እንደሆነ ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ትምህርቱን ግብህን ለማሳካት በሚረዳ መንገድ ማዋቀር ነው።

የሐዋርያት ሥራ 9:​22 ሳውል (ጳውሎስ) በደማስቆ ስላከናወነው አገልግሎት ሲገልጽ እንዲህ ይላል:- “በደማስቆም ለተቀመጡት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደ ሆነ አስረድቶ መልስ ያሳጣቸው ነበር።” ነጥቡን መልክ ባለው መንገድ ያዋቀረው እንዴት ነው? ከጊዜ በኋላ በአንጾኪያና በተሰሎንቄ ስላከናወነው አገልግሎት በሚናገረው ዘገባ ላይ እንደተገለጸው ጳውሎስ አይሁዳውያን በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የሚያምኑና መጻሕፍቱ ስለ መሲሑ የሚናገሩትንም ነገር የሚቀበሉ መሆናቸውን እንደ መሠረት አድርጎ ተጠቅሞበታል። ከዚያም ከእነዚሁ መጻሕፍት ስለ መሲሑ ሕይወትና አገልግሎት የሚናገሩትን ጥቅሶች እየመረጠ በመጥቀስ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ከተከናወኑት ነገሮች ጋር አዛምዷል። በመጨረሻም አድማጮቹን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ወይም መሲሕ ነው ወደሚለው ግልጽ የሆነ መደምደሚያ አድርሷቸዋል። (ሥራ 13:​16-41፤ 17:​2, 3) አንተም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በሚጨበጥ መንገድ ካቀረብህ ነጥቦችህ ሰዎችን የሚያሳምኑ ሊሆኑ ይችላሉ።

ነጥቦችህን ማዋቀር። ትምህርቱን በተለያየ ዘዴ መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር ይቻላል። የተሻለ እንደሚሆን ከተሰማህ ከአንድ በላይ የሆኑትን ዘዴዎች አጣምረህ ልትጠቀምባቸው ትችል ይሆናል። ጥቂቶቹን ምሳሌዎች እንመልከት።

በርዕስ ማዋቀር። ይህ ትምህርቱን በተለያዩ ክፍሎች ማደራጀትን የሚጠይቅ ሲሆን እያንዳንዱ ክፍል ለተነሳህበት ዓላማ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆን ይኖርበታል። እያንዳንዱ ክፍል ጭብጡን ግልጽ ለማድረግ የሚረዳ ዋና ነጥብ ሆኖ ሊያገለግል እንዲሁም አንድ የተወሰነ ነጥብ ትክክል ወይም ስህተት መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ሊይዝ ይችላል። አንዳንዶቹ ነጥቦች ከጭብጡ ጋር የሚዛመዱ ቢሆኑም አድማጮችህን ወይም የንግግርህን ዓላማ በማሰብ ልትጨምራቸው አሊያም ልታወጣቸው ትችላለህ።

እንዴት በርዕስ ማዋቀር እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ተመልከት። ስለ አምላክ ስም የሚሰጥ አጭር ማብራሪያ (1) የአምላክን ስም ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (2) የአምላክ ስም ማን ነው? እንዲሁም (3) ይህንን ስሙን ማክበር የምንችለው እንዴት ነው? የሚሉትን ነጥቦች ያካተተ ሊሆን ይችላል።

“ታማኝና ልባም ባሪያ” መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት እንዲረዱ ብሎ ያዘጋጃቸውን ጽሑፎች በማየት አንድን ትምህርት በርዕስ ማዋቀር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ብዙ ትምህርት ማግኘት ይቻላል። (ማቴ. 24:​45) እነዚህ ጽሑፎች ተማሪዎቹ መሠረታዊ ስለሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚረዱ ብዙ ርዕሶችን ይዘዋል። በመጠናቸው ከፍ ያሉት ጽሑፎች እያንዳንዱን ምዕራፍ በንዑስ ርዕስ ከፋፍለው ያስቀምጣሉ። እያንዳንዱ ርዕስ ተማሪውን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ የሚመራው ሲሆን የመጽሐፉን አጠቃላይ ሐሳብ በተሟላ መንገድ እንዲረዳው በማድረግም ረገድ የሚጫወተው ሚና ይኖራል።

ምክንያትና ውጤት። አንድን ትምህርት መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር የሚቻልበት ሌላው ዘዴ ምክንያቱንና ውጤቱን ማስረዳት ነው።

አንድ ሰው እያደረገው ያለው ወይም ሊያደርገው ያሰበው ነገር የሚያስከትለውን ውጤት በጥሞና እንዲያጤን ለማሳሰብ ስትፈልግ ይህን ዘዴ መጠቀሙን በጣም ውጤታማ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። ምሳሌ ምዕራፍ 7 ለዚህ ግሩም ምሳሌ ይሆነናል። ተሞክሮ የሌለውና ‘አእምሮ የጎደለው’ (ምክንያት) አንድ ወጣት አንዲት ጋለሞታ ሴት ተከትሎ መሄዱ ያስከተለበትን መዘዝ (ውጤት) ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል።​—⁠ምሳሌ 7:​7

ነጥቡ ይበልጥ ጎላ ብሎ እንዲታይ ለማድረግ ከይሖዋ መንገድ የወጡ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን መጥፎ ውጤት ይሖዋን የሚታዘዙ ሰዎች ከሚያገኙት በረከት ጋር እያነጻጸርክ ልትናገር ትችል ይሆናል። የእስራኤል ብሔር ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ሙሴ በአምላክ መንፈስ ተመርቶ ባደረገው ንግግር በረከትና መርገምን እያነጻጸረ ጠቅሷል።​—⁠ዘዳ. ምዕ. 28

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሁኔታውን (ውጤት) አስቀድመህ ከጠቀስህ በኋላ ለዚያ አስተዋጽኦ ያደረገውን ነገር (ምክንያት) ማስከተሉ የተሻለ ይሆናል። ይህ በአብዛኛው ችግሩንና መፍትሔውን አያይዞ ከማቅረብ ዘዴ ጋር ይዛመዳል።

ችግርና መፍትሔ። በአገልግሎት ሰዎችን ስታነጋግር በቅድሚያ የሚያሳስባቸውን ችግር ከጠቀስህ በኋላ ትክክለኛውን መፍትሔ ስትጠቁማቸው ለማዳመጥ ሊነሳሱ ይችላሉ። የምትወያዩበት ችግር አንተ ራስህ የጠቀስኸው ወይም ሰውዬው የሚያነሳው ሊሆን ይችላል።

እርጅናና ሞትን፣ የወንጀል መብዛትን ወይም በሰፊው የሚታየውን የፍትሕ መዛባት እንደ ችግር አድርገህ ልትጠቅስ ትችላለህ። እነዚህ ችግሮች መኖራቸው የታወቀ ስለሆነ ይህንን ለማስረዳት ብዙ ማብራራት አያስፈልግም። በቀጥታ ችግሩን ከጠቀስህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን የመፍትሔ ሐሳብ ተናገር።

በሌላ በኩል ደግሞ ችግሩ አንድ ነጠላ ወላጅ የሚገጥመውን ፈታኝ ሁኔታ፣ ሥር የሰደደ ሕመም የሚያስከትለውን ተስፋ መቁረጥ ወይም አንድ ሰው ከሌሎች በሚደርስበት እንግልት ምክንያት የሚያየውን መከራ የመሰለ ከግለሰብ ሕይወት ጋር የተያያዘ ችግር ሊሆን ይችላል። የተሻለ ውጤት ማግኘት ከፈለግህ በመጀመሪያ ጥሩ አዳማጭ መሆን ይኖርብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሁሉ ችግሮች በተመለከተ ጠቃሚ ሐሳብ ይዟል። ይሁን እንጂ በማስተዋል ልንጠቀምበት ይገባል። ሰውዬው ከውይይታችሁ እንዲጠቀም ከፈለግህ እውነታውን መቀበል ይኖርብሃል። እየተናገርህ ያለኸው ስለ ዘላቂ መፍትሔ ነው? ጊዜያዊ እፎይታ ስለሚገኝበት መንገድ ነው? ወይስ በዚህ ሥርዓት ምንም መፍትሔ የሌለውን ችግር ተቋቁሞ ስለመዝለቅ? ስለምን እየተናገርህ እንዳለህ ግልጽ ልታደርገው ይገባል። በሌላ አባባል የምትጠቅሰው ጥቅስና የምታቀርበው የመደምደሚያ ሐሳብ የሚጣጣም ሊሆን ይገባል። አለዚያ ሰውዬው የምታቀርበውን የመፍትሔ ሐሳብ አሳማኝ ሆኖ ላያገኘው ይችላል።

የጊዜ ቅደም ተከተል። አንዳንድ ትምህርቶች ይበልጥ ማራኪ የሚሆኑት ነጥቦቹ በጊዜ ቅደም ተከተላቸው ሲቀርቡ ነው። ለምሳሌ ያህል በዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ አሥሩ መቅሰፍቶች የተዘረዘሩት በተፈጸሙበት ቅደም ተከተል ነው። በ⁠ዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በእምነታቸው ምሳሌ የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶችን የዘረዘረው የኖሩበትን ዘመን ቅደም ተከተል ጠብቆ ነው።

ስላለፉት ነገሮች የምትናገረው በጊዜ ቅደም ተከተል ከሆነ አድማጮችህ አንዳንዶቹ ሁኔታዎች ሊከሰቱ የቻሉት ለምን እንደሆነ ግልጽ ይሆንላቸዋል። በዘመናችንም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የተከናወኑትን ነገሮች ስትዘረዝር በዚህ ዘዴ ልትጠቀም ትችላለህ። በዚህ መንገድ በጊዜ ቅደም ተከተል ላይ የተመሠረተውን አቀራረብ ከምክንያትና ውጤት አቀራረብ ጋር አቀናጅተህ ልትጠቀምበት ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት ይፈጸማሉ የሚላቸውን ነገሮች ስትዘረዝር የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀህ ብትናገር አድማጮችህ በቀላሉ ሊከታተሉህና በኋላም ነጥቦቹን ሊያስታውሱ ይችላሉ።

ነጥቦቹን የጊዜ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ማዋቀር ሲባል ሁልጊዜ ከመጀመሪያ መጀመር አለብህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ አጓጊ የሆነውን የታሪኩን ክፍል በመጥቀስ መጀመሩ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ያህል አንድ ተሞክሮ ስትናገር ግለሰቡ ለአምላክ ያለው ታማኝነት ፈተና ላይ የወደቀበትን ጊዜ መጥቀስ ትፈልግ ይሆናል። በዚህ መልኩ ልባቸውን ካንጠለጠልህ በኋላ ታሪኩን ከመጀመሪያ ጀምረህ በቅደም ተከተል ልትነግራቸው ትችላለህ።

አግባብ ያላቸውን ነጥቦች ብቻ ምረጥ። ትምህርቱን የምታዋቅርበት መንገድ ምንም ይሁን ምን የምትጠቀምባቸው ነጥቦች አግባብ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። የትምህርትህ ጭብጥ የምትመርጣቸውን ነጥቦች ይወስናል። አድማጮችህ እነማን እንደሆኑም ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል። በአንድ አካባቢ ላሉ አድማጮች በጣም አስፈላጊ የሆነው ነጥብ በሌላ አካባቢ ላሉት ብዙም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። በተጨማሪም የምታካትታቸው ነጥቦች በሙሉ የንግግርህን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ሊሆኑ ይገባል። አለበለዚያ ግን አቀራረብህ ለአድማጮች ማራኪ ቢሆንም የተፈለገውን ውጤት ላያስገኝ ይችላል።

ምርምር ስታደርግ ከንግግርህ ጋር የሚስማሙ ብዙ ጥሩ ነጥቦች ታገኝ ይሆናል። ታዲያ ልትጠቀምባቸው የሚገባው ምን ያህሉን ነው? የምትጠቅሰው ነጥብ በጣም ከበዛ ግብህን ከዳር ማድረስ አትችልም። አድማጮችህ በጥድፊያ ከሚቀርቡ ብዙ ነጥቦች ይልቅ በደንብ የተብራሩ ጥቂት ነጥቦችን ማስታወስ ይቀላቸዋል። ይህ ማለት ግን እግረ መንገድህን አንዳንድ ጥሩ ሐሳቦች መጥቀስ አትችልም ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ ዋናውን የንግግርህን ዓላማ እንዲያደበዝዙብህ መፍቀድ የለብህም። በ⁠ማርቆስ 7:​3, 4 እንዲሁም በ⁠ዮሐንስ 4:​1-3, 7-9 ላይ እንዲህ ያሉት ዝርዝር ነጥቦች እንዴት በጥበብ እንደተጠቀሱ ልብ በል።

አድማጮችህ ለመከታተል እንዳይቸገሩ ከአንዱ ነጥብ ወደሌላው በድንገት መሸጋገር የለብህም። ነጥቦቹ እርስ በርስ የተሳሰሩ እንዲሆኑ አንዱን ሐሳብ ከሌላው ጋር ማያያዝ ሊያስፈልግህ ይችላል። የምትጠቀምበት ማያያዣ በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ያለውን ዝምድና የሚያሳይ ሐረግ ወይም አንድ ሙሉ ዓረፍተ ነገር ሊሆን ይችላል። በብዙ ቋንቋዎች አንድ አዲስ ሐሳብ ከፊቱ ካለው ሐሳብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳየት ቀላል የማያያዣ ቃላትን ወይም ሐረጎችን መጠቀም ይቻላል።

አግባብ ያላቸውን ነጥቦች ብቻ መጠቀምና መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር የንግግርህን ዓላማ ለማሳካት ይረዳሃል።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ:-

  • ዓላማዬ ምንድን ነው?

  • እያንዳንዱ ዋና ነጥብ ከዚህ ዓላማ ጋር በግልጽ የሚዛመድ ነውን?

  • ነጥቦቼን ስመርጥ አድማጮቼን ግምት ውስጥ አስገብቻለሁን?

  • ትምህርቱን ያዋቀርሁት አድማጮች በነጥቦቹ መካከል ያለውን ዝምድና በቀላሉ እንዲያስተውሉ በሚያስችል መንገድ ነውን?

መልመጃ፦ ይህንን ምዕራፍ ካነበብህ በኋላ የእያንዳንዱ አንቀጽ ፍሬ ነገር ምን እንደሆነ እያገናዘብህ ሳትጣደፍ ከልሰው። እያንዳንዱ አንቀጽ የጠቅላላውን ምዕራፍ ዓላማ በማሳካት ረገድ ምን ሚና እንደሚጫወት ልብ በል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ