የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በንግድ አካባቢዎች መስበክ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎት—2004 | ሐምሌ
    • በንግድ አካባቢዎች መስበክ የሚቻለው እንዴት ነው?

      1 ሰዎች በአብዛኛው እንግዶችን በደስታ በሚቀበሉበትና ብዙዎች ቤታቸው በሚገኙበት አካባቢ መስበክ ያስደስትሃል? ከጉባኤህ ክልል ሳትወጣ እንደዚህ ማድረግ ትችል ይሆናል። እንዴት? በክልልህ ውስጥ በሚገኙት የንግድ ቦታዎች በመስበክ ነው። ብዙውን ጊዜ ኪዮስኮችንና የገበያ አዳራሾችን ጨምሮ በሱቆች ውስጥ የሚሰብኩ አስፋፊዎች ጥሩ ውጤቶች አግኝተዋል።

      2 በአንዳንድ ጉባኤዎች የአገልግሎት ክልል ውስጥ የንግድ ቦታዎች ይገኛሉ። የክልል አገልጋይ የሆነው ወንድም ሰው በጣም ለሚበዛባቸው ለእነዚህ የንግድ አካባቢዎች ለየት ያለ የክልል ካርታ ሊያዘጋጅ ይችላል። በመኖሪያ አካባቢዎች የንግድ ቦታዎች በሚኖሩበት ጊዜ አስፋፊዎች የንግድ ቦታዎቹን ትተው መኖሪያ ቤቶቹን ብቻ ማንኳኳት እንዳለባቸው በአገልግሎት ክልል ካርታው ላይ በግልጽ ሊሠፍር ይገባል። በሌሎች ክልሎች ደግሞ የንግድ ቦታዎቹን ከመኖሪያ ቤቶቹ ጋር አብሮ ማንኳኳት ይቻል ይሆናል። በንግድ ቦታዎች አገልግለህ የማታውቅ ከሆነ አንዳንድ ትናንሽ ኪዮስኮችን በማንኳኳት ልትጀምር ትችላለህ።

      3 ቀለል ያለ አቀራረብ ይኑርህ፦ በሱቆች ውስጥ ስናገለግል አለባበሳችን የሚያስከብር መሆን አለበት። ከዚህም በላይ ገበያተኞች የማይበዙበትን ሰዓት መምረጥ ያስፈልጋል። የሚቻል ከሆነ ሊስተናገዱ ተራ የሚጠብቁ ደንበኞች በሌሉበት ሰዓት ወደ ሱቁ መግባት ይመረጣል። በትላልቅ መደብሮች ውስጥ ሥራ አስኪያጁን ወይም ኃላፊነት የተሰጠውን ሰው ለማነጋገር እንደምትፈልግ ተናገር። መልእክትህ አጭርና ቀጥተኛ ይሁን። ምን ብለህ ልትጀምር ትችላለህ?

      4 በሱቁ ውስጥ የሚሠራውን ሰው ወይም ሥራ አስኪያጁን በምታነጋግርበት ጊዜ እንዲህ ልትል ትችላለህ:- “ነጋዴዎች ሕይወታቸው በሥራ የተወጠረ በመሆኑ በአብዛኛው ቤታቸው አይገኙም። ወደ ሥራ ቦታችሁ የመጣሁት ለዚህ ነው። መጽሔቶቻችን በዓለም ዙሪያ የሚከናወኑ ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዳስሳሉ።” ከዚያም ከአንድ መጽሔት ላይ አጠር ያለ ሐሳብ አሳየው።

      5 ወይም ደግሞ የሚከተለውን ቀለል ያለ አቀራረብ ልትሞክር ትችላለህ:- “ብዙ ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ማወቅ ቢፈልጉም ጊዜ ግን የላቸውም። ይህ ትራክት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለተመሠረቱ ጥያቄዎችዎ መልስ ለማግኘት ስለሚያስችልዎት ነጻ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም ይገልጻል።” ከዚያም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? ከተባለው ትራክት ገጽ 4 እና 5 ላይ ያሉትን ነጥቦች አሳየው።

      6 ባለሱቁ ሥራ የበዛበት ከመሰለህ አንድ ትራክት ከሰጠኸው በኋላ እንዲህ ልትለው ትችላለህ:- “ብዙም ሥራ በማይበዛብዎት ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ። ስለ ትራክቱ የሚሰማዎትን ሊነግሩኝ ይችላሉ።”

      7 ፍላጎት ያሳዩትን ተመልሰህ ጠይቅ፦ በንግድ አካባቢዎች ጥናት መምራትም ትችል ይሆናል። አንድ ልዩ አቅኚ ለአንድ ነጋዴ አዘውትሮ መጽሔቶች ይወስድለት ነበር። ግለሰቡ ለሚያነባቸው ነገሮች አድናቆት እንዳለው ሲገልጽ አቅኚው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚቻል አሳየው። ሰውየው በሚሠራበት ቦታ ጥናት ተጀመረ። አቅኚው ሁኔታዎቹን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥናቱ ከ10 ወይም ከ15 ደቂቃ በላይ እንዳይወስድ አደረገ። እኛም እንዲሁ በንግድ ቦታዎች በመስበክ ምስራቹ የሚገባቸውን ሰዎች መፈለጋችንን እንቀጥል።

  • የሚያዝያ የአገልግሎት ሪፖርት
    የመንግሥት አገልግሎት—2004 | ሐምሌ
    • የሚያዝያ የአገልግሎት ሪፖርት

      አማ.  አማ. አማ.  አማ. 

      ብዛት:- ሰዓት መጽሔ. ተ.መ.   መ/ቅ.ጥ.

      ልዩ አቅኚ 265 126.7 22.4 86.8 6.8  

      አቅኚ 690 70.4 9.8 31.3 2.2  

      ረዳት አቅኚ 1,196 51.9 6.3 14.8 1.0  

      አስፋፊ 5,115 13.2 2.0 5.5 0.4  

      ጠቅላላ 7,266    አዲስ ከፍተኛ ቁጥር!

  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎት—2004 | ሐምሌ
    • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?

      መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1

      “አንዳንድ ሃይማኖታዊ መሪዎች የሰብዓዊውን ኅብረተሰብ ሕይወት ለማሻሻል በሚል በፖለቲካ ጉዳዮች ይካፈላሉ። ከዚህ በተቃራኒ ኢየሱስ ሰዎች ሊያነግሱት በፈለጉ ጊዜ ምን እንዳደረገ ልብ ይበሉ። [ዮሐንስ 6:​15ን አንብብ።] ኢየሱስ ትኩረት ያደረገው ለሰዎች ዘላቂ ጥቅም በሚያስገኘው ነገር ላይ ነበር። ይህ መጽሔት ዘላቂው መፍትሔ ምን እንደሆነ ይገልጻል።”

      ንቁ! ግንቦት 2004

      “ብዙዎች በሥራ ቦታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። አንዳንዶቹም በሥራ ባልደረቦቻቸው ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ያሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት የሚያስችል ምክር እንደሚሰጥ ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 15:​1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በሥራ ቦታችን ከሌሎች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ለማድረግ የሚረዱን ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦች ይዟል።”

      መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15

      “ሰዎች በምድር ላይ የሚያደርጓቸው ነገሮች በአምላክ ስሜት ላይ ለውጥ ያመጡ እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ ጥቅስ የምናደርጋቸው ነገሮች አምላክን ሊያስደስቱት እንደሚችሉ ያሳያል። [ምሳሌ 27:​11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክን ልብ ደስ ያሰኙ ሰዎችን ምሳሌ የሚጠቅስ ከመሆኑም በላይ እኛም እንደዚህ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።”

      Awake! May 22

      “የሕክምናው ሳይንስ በሽታን በመዋጋት ረገድ አስደናቂ እድገት አድርጓል፤ ሆኖም በሽታ ከዓለም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚወገድበትን ጊዜ ለማየት የምንታደል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በኢሳይያስ 33:​24 ላይ ያለው ትንቢት ሲፈጸም በምድር ላይ የሚኖር ሁሉ የተሟላ ጤንነት እንደሚኖረው ይናገራል።” [ከዚያም ጥቅሱን አንብብ።]

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ