-
ሙሉ በሙሉ የጠፋ ዓለም!መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 1
-
-
ይዟል። ይሁን እንጂ ማስረጃዎቹ እንደሚያሳዩት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንዲያው ታሪክ ብቻ አይደለም። መሬት ጠብ የማይለው ትንቢቱና ጥልቅ ጥበቡ መጽሐፉ ራሱ እንደሚለው አምላክ ከሰው ጋር የሐሳብ ግንኙነት የሚያደርግበት መስመር እንደሆነ ያመለክታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ከአፈ ታሪክ በተለየ በታሪካዊ ዘገባዎቹ ውስጥ የዘር ግንድንና የቦታ ዝርዝሮችን ጨምሮ ስሞችንና ቀናትን በትክክል ይገልጻል። ከጥፋት ውኃው በፊት ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረና መላው ዓለም በድንገት ሊጠፋ የቻለው ለምን እንደሆነ በግልጽ ይነግረናል።
የዚያ ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረ ኅብረተሰብ ችግር ምን ነበር? የሚቀጥለው ርዕስ ይህንን ጥያቄ ይመልሳል። የዓለማችን የወደፊት ዕጣ ምን ያህል ያስተማምናል ብለው ለሚያስቡ ሰዎች ይህ ጠቃሚ ጥያቄ ነው።
-
-
የጥንቱ ዓለም የጠፋው ለምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 1
-
-
የጥንቱ ዓለም የጠፋው ለምንድን ነው?
ዓለም አቀፉ የጥፋት ውኃ የተፈጥሮ አደጋ አልነበረም። ከአምላክ የመጣ ፍርድ ነበር። ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም በአብዛኛው ሰሚ ጆሮ ተነፍጎት ነበር። ለምን? ኢየሱስ እንደሚከተለው በማለት ተናግሯል:- “በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፣ [ሰዎች] ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደነበሩ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ [አላወቁም።]”—ማቴዎስ 24:38, 39፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።
በሥልጣኔ የመጠቀ ኅብረተሰብ
ከጥፋት ውኃው በፊት የነበረው ኅብረተሰብ በአንዳንድ መንገዶች ዛሬ እኛ የሌሉን አጋጣሚዎች ነበሩት። ለምሳሌ ያህል መላው የሰው ዘር አንድ ቋንቋ ይናገር ነበር። (ዘፍጥረት 11:1) ይህም የተለያየ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች የተቀናጀ ጥረት ለሚጠይቀው ሥነ ጥበባዊና ሳይንሳዊ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎ መሆን አለበት። በተጨማሪም ብዙ ሰዎች ረዥም ዘመን መኖር መቻላቸው የእውቀት ክምችታቸውን እንዲያሳድጉ ረድቷቸው መሆን አለበት።
አንዳንዶች በወቅቱ የሰው ዘር እድሜ የሚባለውን ያክል ረዥም እንዳልነበረና በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት ወራት ብቻ እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህ ትክክል ነው? እስቲ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላልኤል የሚናገረውን ተመልከት:- “መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት [“ስድሳ አምስት፣” አ.መ.ት ] ዓመት ኖረ፣ ያሬድንም ወለደ . . . መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።” (ዘፍጥረት 5:15-17) አንድ ዓመት አንድ ወር ከሆነ መላልኤል ልጅ የወለደው ገና በአምስት ዓመቱ ነው ማለት ነው! ይህ ደግሞ በፍጹም ሊሆን አይችልም። በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎች ለፍጽምና የቀረቡ በመሆናቸው የመጀመሪያው ሰው አዳም የነበረው ዓይነት ጥንካሬ ነበራቸው። በዚህም ምክንያት ለብዙ መቶ ዓመታት ኖረዋል። ታዲያ ምን አከናወኑ?
የጥፋት ውኃ ከመምጣቱ ብዙ ዓመታት ቀደም ብሎ የምድር ሕዝብ ቁጥር በጣም ከመጨመሩ የተነሣ የአዳም ልጅ ቃየን ሄኖሕ የተባለችውን ከተማ ቆረቆረ። (ዘፍጥረት 4:17) ከጥፋት ውኃው በፊት በነበሩት ዓመታት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ተቋቁመው ነበር። ‘ናስና ብረትን’ በማቅለጥ የተለያዩ መሣሪያዎች ይሠሩ ነበር። (ዘፍጥረት 4:22) እነዚህ መሣሪያዎች ለግንባታ፣ ለአናጺነት ሙያ፣ ለልብስ ስፌትና ለእርሻ ሥራዎች እንደሚውሉ ምንም ጥርጥር የለውም። እነዚህ ሁሉ የሥራ መስኮች የተጠቀሱት ስለ መጀመሪያዎቹ የምድር ነዋሪዎች በሚገልጹት ዘገባዎች ውስጥ ነው።
ይህ ዓይነቱ የእውቀት ክምችት ተከታዩ ትውልድ በሥነ ብረታ ብረት፣ ዘር በማልማት ጥናት፣ በከብት እርባታ እንዲሁም በሥነ ጽሑፍና በሥነ ጥበብ የሙያ መስኮች ችሎታውን እንዲያዳብር ረድቶት መሆን አለበት። ለምሳሌ ያህል ዩባል “በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።” (ዘፍጥረት 4:21) ሥልጣኔ ተስፋፍቶ ነበር። ሆኖም በድንገት ሁሉም ነገር እንዳልነበረ ሆነ። ምን ተፈጠረ?
ችግሩ ምን ነበር?
ከጥፋት ውኃ በፊት የኖረው ትውልድ ጥሩ ጥሩ አጋጣሚዎች የነበሩት ቢሆንም ጅምሩ ግን መጥፎ ነበር። የሁሉም አባት የነበረው አዳም በአምላክ ላይ ዓምፆአል። የመጀመሪያዋን ከተማ የቆረቆረው ቃየን የገዛ ወንድሙን ገድሏል። ክፋት በፍጥነት መዛመቱ ምንም አያስደንቅም! አዳም ለልጆቹ ያወረሰው ብልሹ ቅርስ ያስከተለው መዘዝ እያደር እየከፋ የሚሄድ ነበር።—ሮሜ 5:12
ይሖዋ ሁኔታው በዚህ መልኩ የሚቀጥለው ለተጨማሪ 120 ዓመት ብቻ እንደሆነ ሲወስን ሁኔታዎቹ የሚደመደሙበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ግልጽ ሆኖ ነበር። (ዘፍጥረት 6:3) መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- ‘የሰው ክፋት በምድር ላይ በዛ፣ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ ሆነ። ምድርም ግፍን ተሞላች።’—ዘፍጥረት 6:5, 11
ከጊዜ በኋላ አምላክ የጥፋት ውኃ በማምጣት መላውን ሥጋ ለባሽ እንደሚያጠፋ ለኖኅ በግልጽ ነገረው። (ዘፍጥረት 6:13, 17) ኖኅ “የጽድቅ ሰባኪ” የነበረ ቢሆንም ሰዎች በዙሪያቸው ያለው ዓለም ድንገት ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከብዷቸው ሊሆን እንደሚችል ምንም አያጠራጥርም። (2 ጴጥሮስ 2:5) ማስጠንቀቂያውን የሰሙትና ከጥፋቱ በሕይወት የተረፉት ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ። (1 ጴጥሮስ 3:20) ይህ ዛሬ ለምንኖረው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ለእኛ የሚያስተላልፈው መልእክት ምንድን ነው?
የምንኖረው ከኖኅ ዘመን ጋር በሚመሳሰል ጊዜ ውስጥ ነው። በየቀኑ አሰቃቂ ስለሆኑ የሽብርተኝነት ድርጊቶች፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች፣ ስውር ዓላማ ያላቸው መሣሪያ የታጠቁ ግለሰቦች ስለሚያደርሱት የጅምላ ጭፍጨፋና አስደንጋጭ በሆነ መጠን እየጨመረ ስለመጣው የቤት ውስጥ ዓመፅ የሚገልጹ ዜናዎች እንሰማለን። ምድር እንደገና በዓመፅ ተሞልታለች። ጥንት እንደተደረገው ሁሉ ዛሬም ዓለም ስለሚመጣባት ፍርድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷታል። ኢየሱስ ራሱ በአምላክ የተሾመ ፈራጅ ሆኖ እንደሚመጣና እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ሰዎችን እንደሚለያያቸው ተናግሯል። ኢየሱስ ብቃቱን አሟልተው ያልተገኙ “ወደ ዘላለም ቅጣት . . . ይሄዳሉ” በማለት ተናግሯል። (ማቴዎስ 25:31-33, 46) ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በዚህ ጊዜ ብቸኛውን እውነተኛ አምላክ የሚያመልኩ በሚልዮን የሚቆጠሩ እጅግ ብዙ ሰዎች ከጥፋቱ ይተርፋሉ። እነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መጠን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት አግኝተው በመጪው ዓለም ውስጥ በደስታ ይኖራሉ።—ሚክያስ 4:3, 4፤ ራእይ 7:9-17
ብዙዎች ይህንን በመሳሰሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦችና ስለ ፍርድ እርምጃ በሚገልጹ ማስጠንቀቂያዎች ያፌዛሉ። የፍርድ እርምጃው እነዚህ ሐሳቦች እውነት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። ሆኖም ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደገለጸው እነዚህ ዘባቾች እውነታውን ለመቀበል አይፈልጉም። እንዲህ በማለት ጽፏል:- “በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች . . . [ይመጣሉ።] . . . እነርሱም:- የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? . . . ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውኃ ተጋጥማ በውኃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤ በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ
-