የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • be ጥናት 45 ገጽ 240-ገጽ 243 አን. 1
  • ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርት አዘል ምሳሌዎች
  • በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ያለምሳሌ አይነግራቸውም ነበር”
    “ተከታዬ ሁን”
  • ተስማሚ ምሳሌዎች
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • “ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ታላቁን አስተማሪ ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
be ጥናት 45 ገጽ 240-ገጽ 243 አን. 1

ጥናት 45

ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ዘይቤዎችን፣ ታሪኮችን ወይም እውነተኛ የሕይወት ተሞክሮዎችን የንግግርህን ዓላማ ለማሳካት በሚረዳ መንገድ ተጠቀምባቸው።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ይህን የማስተማር ዘዴ በሚገባ ከተጠቀምህ ንግግርህ የዳበረ፣ የሰዎችን ሕይወት የሚለውጥ እንዲሁም የማይረሳ ሊሆን ይችላል። አላግባብ ከተጠቀምህበት ደግሞ አድማጮች የትምህርቱን ቁም ነገር እንዳያስተውሉ እንቅፋት ሊሆን ይችላል።

ምሳሌ መጠቀም ግሩም የማስተማሪያ ዘዴ ነው። ምሳሌዎች ሰዎች በትኩረት እንዲያዳምጡ የማድረግ ኃይል አላቸው። የአድማጮችን አእምሮ ያሠራሉ። ስሜትን ስለሚኮረኩሩ ልብ ሊማርኩ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ምሳሌዎች ሰዎች ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከትም ለማረም ሊረዱ ይችላሉ። ትምህርቱን ለማስታወስም ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ። በምታስተምርበት ጊዜ ምሳሌዎችን ትጠቀማለህ?

ዘይቤዎች በሰዎች አእምሮ ውስጥ ምስል የመቅረጽ ኃይል ያላቸውና ብዙውን ጊዜ አንድን መልእክት በጥቂት ቃላት ብቻ መግለጽ የሚያስችሉ ምሳሌዎች ናቸው። ተስማሚ የሆነውን ዘይቤ ከመረጥን መልእክቱን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ይሁን እንጂ አንድ አስተማሪ ነጥቡን ይበልጥ ለማጠናከር ሲል የተወሰነ ማብራሪያ ሊያክልበት ይችላል። በዚህ ረገድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ መማር ትችላለህ።

አነጻጻሪና ተለዋጭ ዘይቤዎች። ከሁሉም ቀላል የሆነው ዘይቤ አነጻጻሪ ዘይቤ ነው። በምሳሌ የማስተማር ችሎታን ለማዳበር ገና ጥረት እያደረግህ ከሆነ በዚህ ዘይቤ ብትጀምር የተሻለ ይሆናል። ይህ ዘይቤ ብዙውን ጊዜ “እንደ” ወይም “ያክል” የሚሉትን ዓይነት ማነጻጸሪያዎች ይጠቀማል። አነጻጻሪ ዘይቤ ሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚያነጻጽር ቢሆንም የጋራ ባሕርያቸውን ጎላ አድርጎ ይገልጻል። መጽሐፍ ቅዱስ ዕፀዋትን፣ እንስሳትን፣ የሰማይ ግዑዝ ፍጥረታትን እንዲሁም ሰዎችን የሚጠቅሱ ብዙ ዘይቤዎች ይዟል። በ⁠መዝሙር 1:​3 ላይ የአምላክን ቃል አዘውትሮ የሚያነብብ ሰው ‘በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ ዛፍ’ ማለትም በየጊዜው ፍሬ እንደሚሰጥና እንደማይጠወልግ ዛፍ ተደርጎ ተገልጿል። ክፉ ሰዎች ለአደን እንደ ሸመቀ “አንበሳ” ተደርገው ተገልጸዋል። (መዝ. 10:​9) ይሖዋ የአብርሃምን ዘር “እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ” እንደሚያበዛው ቃል ገብቷል። (ዘፍ. 22:​17) ይሖዋ በእስራኤል ብሔርና በእርሱ መካከል ስላለው የጠበቀ ግንኙነት ሲገልጽ “መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ” እስራኤልና ይሁዳ ከእርሱ ጋር እንደሚጣበቁ ተናግሯል።​—⁠ኤር. 13:​11

ተለዋጭ ዘይቤም በሁለት በጣም የተለያዩ ነገሮች መካከል ያለውን ተመሳሳይነት የሚያጎላ ዘይቤ ነው። ሆኖም ይህ ዘይቤ ይበልጥ ገላጭ ነው። ይህ አንድን ነገር በሌላ ነገር በመመሰል የአንዱን ባሕርይ ለሌላው አሳልፎ የሚሰጥ ዘይቤ ነው። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ብሏቸዋል። (ማቴ. 5:​14) ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ያልተገታ አንደበት የሚያስከትለውን ጉዳት ሲገልጽ “አንደበትም እሳት ነው” ብሏል። (ያዕ. 3:​6) ዳዊት ‘ይሖዋ ዓለቴ አምባዬ ነው’ በማለት ዘምሯል። (2 ሳሙ. 22:​2) ታስቦበት የተመረጠ ተለዋጭ ዘይቤ ብዙውን ጊዜ ምንም ማብራሪያ ላያስፈልገው ይችላል። ይበልጥ ኃይል የሚኖረው እጥር ምጥን ያለ ሲሆን ነው። በተለመደ ዓረፍተ ነገር ከምትገልጸው ይልቅ በተለዋጭ ዘይቤ የምትገልጸው ሐሳብ ይበልጥ በአድማጮችህ አእምሮ ውስጥ ይቀረጻል።

ግነት ዘይቤ በጥበብ ካልተጠቀምንበት አድማጮች በተሳሳተ መንገድ ሊረዱት የሚችሉ ዓይነት ዘይቤ ነው። ኢየሱስ “በወንድምህም ዓይን ያለውን ጕድፍ ስለ ምን ታያለህ፣ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?” ብሎ በጠየቀ ጊዜ ይህንን ዘይቤ ተጠቅሞ በአድማጮቹ አእምሮ ውስጥ የማይጠፋ ምስል ቀርጿል። (ማቴ. 7:​3) ይህንንም ሆነ ሌሎች ዘይቤዎችን ለመጠቀም ከመሞከርህ በፊት አነጻጻሪና ተለዋጭ ዘይቤዎችን በጥሩ መንገድ መጠቀምን መማር ይኖርብሃል።

ምሳሌዎችን ተጠቀም። በምታስተምርበት ጊዜ ዘይቤዎችን ከመጠቀም ይልቅ የፈጠራ ታሪኮችን ወይም እውነተኛ ታሪኮችን እንደ ምሳሌ መጠቀም ትመርጥ ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ምሳሌዎች በምትጠቀምበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል። በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነጥብ የሚደግፉ ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም አድማጮች ታሪኩን አስታውሰው ትምህርቱን እንዳይረሱት በአቀራረብህ ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል።

ሁሉም ምሳሌዎች እውነተኛ ታሪኮች መሆን አለባቸው ማለት ባይሆንም በገሃዱ ዓለም ያለውን አስተሳሰብ ወይም ሁኔታ የሚያንጸባርቁ መሆን ይኖርባቸዋል። ኢየሱስ ንስሐ ለሚገቡ ኃጢአተኞች ሊኖረን ስለሚገባው አመለካከት ሲያስተምር ጠፍታበት የነበረችውን በግ በማግኘቱ ስለተደሰተ ሰው ምሳሌ ተናግሯል። (ሉቃስ 15:​1-7) ኢየሱስ ባልንጀራህን ውደድ የሚለው ትእዛዝ ምን ትርጉም እንዳለው ማስተዋል የተሳነው አንድ ሰው ላቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ስለ አንድ ሳምራዊ የሚገልጽ ታሪክ ተናግሯል። ታሪኩ በወንበዴዎች ጉዳት የደረሰበትን ሰው አንድ ካህንና ሌዋዊ አይተው እንዳላዩ ሲያልፉት ሳምራዊው እንደረዳው ይገልጻል። (ሉቃስ 10:​30-37) አንተም የሰዎችን አስተሳሰብና የሚያደርጓቸውን ነገሮች የምታስተውል ከሆነ ይህን የማስተማር ዘዴ በጥሩ መንገድ ልትጠቀምበት ትችላለህ።

ነቢዩ ናታን ንጉሥ ዳዊትን ለመገሰጽ በሄደበት ጊዜ ከራሱ ያፈለቀውን አንድ ታሪክ ተጠቅሟል። ይህ ታሪክ ለሁኔታው በጣም ተስማሚ ስለነበር ዳዊት ድርጊቱን አቅልሎ የመመልከት ሐሳብ እንኳ ጭራሽ አልመጣበትም። ታሪኩ ብዙ በጎች ስላሉት አንድ ባለጠጋ ሰውና ተንከባክቦ ያሳደጋት አንዲት ጠቦት ብቻ ስላለችው ድሃ ሰው የሚገልጽ ነበር። ዳዊት ራሱ እረኛ ስለነበር የዚህች ጠቦት ባለቤት ምን ሊሰማው እንደሚችል አሳምሮ ያውቃል። ይህ ድሃ ሰው የነበረችውን አንዲት ጠቦት ከጉያው ነጥቆ በወሰደው ባለጠጋ ድርጊት ዳዊት እጅግ ተቆጣ። ከዚያም ናታን “ያ ሰው አንተ ነህ” ሲል በቀጥታ ነገረው። ዳዊት ልቡ ስለተነካ እውነተኛ ንስሐ ገብቷል። (2 ሳሙ. 12:​1-14) ልምድ እያገኘህ ስትሄድ የሰዎችን ስሜት የሚነኩ ጉዳዮችን በጥበብ መያዝ ትማራለህ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተመዘገቡት ታሪኮች መካከል ለማስተማር የሚረዱ ብዙ ግሩም ምሳሌዎችን መጥቀስ ትችላለህ። ኢየሱስ “የሎጥን ሚስት አስቡአት” በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ታሪክ ለማስተማር ተጠቅሞበታል። (ሉቃስ 17:32) ሥልጣኑን እንደያዘ የሚጠቁሙትን ምልክቶች ሲዘረዝር ‘የኖኅን ዘመን’ ጠቅሷል። (ማቴ. 24:​37-39) ሐዋርያው ጳውሎስ በ⁠ዕብራውያን ምዕራፍ 11 ውስጥ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ 16 ወንዶችና ሴቶችን በስም ጠቅሷል። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን በደንብ እያወቅህ ስትሄድ በውስጡ የተጠቀሱትን ሰዎችና ክንውኖች እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ጥሩ አድርገህ ማስተማር ትችላለህ።​—⁠ሮሜ 15:​4፤ 1 ቆሮ. 10:​11

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በዚህ ዘመን የተፈጸሙ እውነተኛ ታሪኮችን በመጥቀስ ትምህርቱን ማጠናከሩ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ይህንን ስታደርግ የምትጠቅሰው ታሪክ እውነተኝነቱ የተረጋገጠና በአድማጮች መካከል ያሉትን አንዳንድ ሰዎች የማያሸማቅቅ መሆን ይኖርበታል። ወይም በአድማጮች አእምሮ ውስጥ ከርዕሱ ጋር የማይገናኝ አወዛጋቢ ጥያቄ እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆን የለበትም። ደግሞም ተሞክሮውን ስትጠቅስ አንድ ዓላማ ይዘህ መሆን እንዳለበት አትዘንጋ። ከንግግርህ ዓላማ የሚያዘናጉ አላስፈላጊ ዝርዝር ጉዳዮችን መተረክ የለብህም።

አድማጮች በቀላሉ ይረዱታል? የምትጠቀምበት ምሳሌ ምንም ዓይነት ይሁን ምን የሚያከናውነው አንድ ዓላማ ሊኖር ይገባል። ምሳሌው እየተወያያችሁበት ካለው ርዕስ ጋር ምን ዝምድና እንዳለው ባታስረዳቸው አድማጮችህ ራሳቸው ሊያዛምዱት ይችላሉ?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ “የዓለም ብርሃን” እንደሆኑ ከተናገረ በኋላ ሰዎች መብራትን እንዴት እንደሚጠቀሙበትና ይህም ለደቀ መዛሙርቱ ምን ትርጉም እንዳለው በአጭሩ ገልጿል። (ማቴ. 5:​15, 16) ስለጠፋችው በግ ከተናገረው ምሳሌ በኋላ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ምን ያህል ደስታ እንደሚሆን ገልጿል። (ሉቃስ 15:​7) ስለ ደጉ ሳምራዊ ታሪክ ከተናገረ በኋላም ያዳምጠው ለነበረው ሰው አንድ ግልጽ ጥያቄ በማቅረብ እርሱም እንደዚያው እንዲያደርግ ቀጥተኛ ምክር ሰጥቶታል። (ሉቃስ 10:​36, 37) በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ ስለተለያዩ የአፈር ዓይነቶችና በማሳው ውስጥ ስለተዘራው እንክርዳድ የሚገልጹትን ምሳሌዎች ትርጉም የማወቅ ጉጉት ለነበራቸው ጥቂት አድማጮቹ አብራርቶላቸዋል። (ማቴ. 13:​1-30, 36-43) ኢየሱስ ከመሞቱ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ነፍሰ ገዳይ ስለሆኑ የወይን አትክልት ገበሬዎች ምሳሌ ተናግሯል። ምሳሌው ግልጽ ስለነበር ምንም ማብራሪያ መስጠት አላስፈለገውም። ‘የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተውለው ነበር።’ (ማቴ. 21:​33-45) ስለዚህ አንድ ምሳሌ ከጠቀስክ በኋላ ከጉዳዩ ጋር ለማዛመድ ተጨማሪ ማብራሪያ የመስጠቱን አስፈላጊነትም ሆነ የማብራሪያውን ርዝማኔ የሚወስነው የምሳሌው ዓይነት፣ የአድማጮች አመለካከትና ምሳሌውን የጠቀስክበት ዓላማ ነው።

ምሳሌዎችን ጥሩ አድርጎ የመጠቀም ችሎታን ማዳበር ጊዜና ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም በውጤቱ ትደሰታለህ። ምሳሌው በደንብ የታሰበበት ከሆነ የአድማጮችን አእምሮና ልብ ይማርካል። እውነታውን እንዲሁ ተናግሮ ከማለፍ ይልቅ በምሳሌ አስደግፎ ማስረዳት መልእክቱ ይበልጥ ኃይል እንዲኖረው ያደርጋል።

ተስማሚ ምሳሌ መምረጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረህ አንብብ፤ ምሳሌዎቹን ልብ በል፤ ምን መልእክት እንዳዘሉ አሰላስል።

  • በአካባቢህ የሚከናወኑትን ነገሮች በትኩረት በመከታተል የሰዎችን አመለካከትና የሚያደርጓቸውን ነገሮች ከንግግርህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በሐሳብህ ለማዛመድ ሞክር።

  • ጥሩ ምሳሌዎች ስታገኝ እየሰበሰብህ በፋይል አስቀምጣቸው። እነዚህ ምሳሌዎች ስታነብብ፣ ንግግር ስታዳምጥ ወይም በአካባቢህ ያሉ አንዳንድ ነገሮችን በማስተዋል ያገኘሃቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ወደፊት ልትጠቀምባቸው ስለምትችል በደንብ አስቀምጣቸው።

መልመጃ፦ በሚከተሉት ጥቅሶች ላይ ያሉትን ምሳሌዎች አንድ በአንድ መርምር:- ኢሳይያስ 44:​9-​20፤ ማቴዎስ 13:​44፤ ማቴዎስ 18:​21-​35። እያንዳንዱ ምሳሌ ያዘለው መልእክት ምንድን ነው? ተስማሚ ምሳሌ ነው የምትለውስ ለምንድን ነው?

ሳስተምር ልጠቀምባቸው የምፈልጋቸው ዘይቤዎች

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

ወደፊት ልጠቀምባቸው የምፈልጋቸው እውነተኛ የሕይወት ታሪኮች

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․․

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ